Monday, 30 December 2024

በተሰቀለው ክርስቶስ ወንጌል አናፍርም!

 Please read in PDF

እናውቃለን፤ ዕርቃንና ወንጀለኛ በሚሰቀልበት መስቀል ላይ መሰቀል፣ ልዕለ ኃያል አምላክ ሲኾን በፍጡራን እጅ መያዙና ፍጹም መከራን ፈቅዶና ወድዶ በ“ሽንፈት” መቀበሉ ውርደት ነው፤ በሰው ዓይንም ሲታይ፣ የሚያሳፍር እንጂ የሚያኰራ አይደለም። እንዲህ ያለውንም ነገር “የምሥራች!” ብሎ መናገር ተቀባይነትና ተከታይን የሚያስገኝ ነገር አይደለም። ቅዱስ ጳውሎስ ይህን በሕዝብ ዘንድ እምብዛም ተቀባይነት የሌለውን ወንጌል በይፋ፤ በድፍረት ሰበከ!

Wednesday, 4 December 2024

የቄሣር ኮሪደር!

Please read in PDF 

በአጭር ቃል፣ በ58 ዓ.ም አከባቢ ነግሦ የነበረው የሮም ቄሣር ኔሮን፣ የሮምን ከተማ ከግማሽ በላይ በእሳት አነደዳት። ያነደበበት ምክንያቱ ከተማይቱ ስለ ደበረችው፣ ሌላ አዲስ ከተማ መገንባት ያመቸው ዘንድና ቃጠሎውን በክርስቲያኖች በማላከክ በኋላ በዚህ ሰበብ፣ ክርስቲያኖችን ለማሳደድና ለመግደል ይመቸው ዘንድ ነው። አባ ጎርጎርዮስ እንዲህ በማለት ይገልጹታል፣

“ … ብዙ ወንጌል መልእክተኞችን የፈጀው ኔሮን ቄሳር ነው።ለነገሩ መነሻ ያደረገው የሮምን መቃጠል ነው። ርግጥ በዘመነ መንግሥቱ አጋማሽ ላይ የሮም ከተማ በእሳት ጋይታለች። ያቃጠለው ማን እደ ኾነ አልታወቀም። ክርስቲያኖችን አሳጥ ለማጥፋት ኔሮን ራሱ ነው ያደረገው የሚሉ አሉ።”

Friday, 29 November 2024

በኢየሱስ አንደራደርም!

 Please read in PDF

ኢየሱስ የማናፍርበት ወንጌላችን ነው፤ ወንጌል ክርስቶስ ባይኖርበት “የምሥራች!” ተብሎ ሊሰበክ አይችልም፤ የቆምነው፤ ያለነው፤ የምንኖረው፤ የምንንቀሳቀሰው… እግዚአብሔር በክርስቶስ ካትረፈረፈው ጸጋ የተነሣ ነው፡፡ ያለ ክርስቶስ ምንም ነን፤ ርሱ በምንም ነገራችን ውስጥ የገባ ምሉዕ አምላክና ሰው ነው፡፡

Thursday, 28 November 2024

ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ¡? – (የመጨረሻ ክፍል)

 Please read in Pdf

መጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣኑ “ሲገሰስ”!

መጽሐፍ ቅዱስ የክርስትና ዋና ማዕከልና የትምህርቶቹም ኾነ የልምምዶቹ መሠረት ነው። ይህ እንዲኾን ያደረገው ዋናው ምክንያት ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊው ሥልጣን ራሱ እግዚአብሔር ስለ ኾነ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የትኛውንም ትምህርት ወይም መጽሐፍ ይዳኛል፤ ይመዝናል እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ከርሱ ውጭ በኾነ ትምህርትም ኾነ መጽሐፍ ፈጽሞ አይመዘንም፤ አይመረመርም።

Wednesday, 27 November 2024

ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ¡? - ክፍል አንድ

 Please read in PDF

የምዩጣኑ ጥርስ ያገጠጠ ውሸት!

መንደርደሪያ

ጃንደረባው የተባለ ሚድያ የሠራውን ቪድዮ፣ ተመልክቼአለኹ፤ አሰላስዬዋለኹም። ብዙ ሰዎች ደውለውልኝ የምጽፍበትን መንገድ ሲያመላክቱኝ፣ ከነገሩኝ ሰዎች ተጽዕኖዎች ነጻ ልወጣ እንዲገባኝ ከራሴ መክሬአለሁ። በተለይም ደግሞ አንዳንድ ነገሮች፣ በቀጥታ ከእኔ ጋር የሚያያዙ በመኾናቸው ይህን ጽፌአለሁ። እጅግ በጣም አስነዋሪ ውሸቶችን ደግሞ ለማጋለጥ ስል፣ በግል የተደረጉ የውይይት ቅጂዎችን ለመጠቀም ተገድጄአለኹ።

Tuesday, 12 November 2024

ጳጳሳቱና መታደስ የሚያስፈራቸው “ኦርቶዶክሳውያን”!

 Please read in PDF

ከኦርቶዶክሳውያን ጥቂት ጳጳሳትና መምህራን መካከል፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ጠንከር ያሉ የተሐድሶ ድምጾች በተለያየ መንገድ እየተሰሙ ነው። በባለፉት ወራት ፓትርያርክ አባ ማትያስ እንደ ተናገሩት፣

ምዕመናን ገንዘባቸውን የሚሰጡት ለሃይማኖት ማስፋፊያ እንጂ ለዘረፋ አይደለም።

በማለት የሙስናና የገንዘብ መውደድ ነገር ሥር የሰደደ መኾኑን ጠቁመዋል። በመቀጠልም ጳጳስ አብርሃም እንዲህ አሉ፣

ቤተ ክርስቲያን የሙሰኞች ዋሻ ኾናለች የሚለው ዘርፈ ብዙ ፍርጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እንጂ ሲቀንስ አይታይም … ይህን አስነዋሪ ድርጊት እያወገዝን እውነትን ተላብሰን ከሙሰኞች የጸዳችና የከበረች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለተተኪው ትውልድ ልናስተላልፍ ይገባል።

በማለት ጠንከር ያለ ድምጽ አሰምተዋል።

Friday, 8 November 2024

“መናፍቅ በመባሌ እጅግ ደስ ይለኛል”

 Please read in PDF

“… በሥጋ ካየነው ያናድዳል፤ የሞተልንን አምላክ በመከተል፣ ቅዱስ ጳውሎስ “እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔም ምሰሉ” ባለው መንገድ ከሄድን ያስደስታል፡፡ ምክንያቱም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ … በአባቱ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ተዋርዶአል፡፡ … ርሱ ምን የልተባለው ነገር አለ? ዋናው ክሱ እኮ በሃይማኖት ነው፤ በሃይማኖት መከሰስ ማለት መናፍቅ ነው ተብሎ ነው፡፡ … ሰንበትን ሻረ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ አለ፣ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካከለ ብለው ነው፤ ያ ለነርሱ መናፍቅነት ነበረ … ርሱ ያልተባለው ምን አለ? … ቅዱስ ጳውሎስ ምን ያልተባለው አለ? አስቀድሞ የብሉይ ኪዳን ዋና ጠበቃ ነበረ … ኋላ መንፈስ ቅዱስ አገኘውና ቀየረው፣ ጌታም ምርጥ ዕቃዬ አለው፡፡ እነዚያ ግን መናፍቅ ነው ያሉት … በተለይ በነገረ ድኅነት እንዲህ መባሌ እጅግ ደስ ይለኛል፡፡”

 (ብጹዕ አቡነ በርናባስ ከመለሱት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ)

Tuesday, 5 November 2024

የእግዚአብሔር መሰደብ ይሰማህ ይኾን?

 Please read in PDF

የእውነተኛ ዓቃብያነ እምነት ሕመም!

በራሳችን ድካምና የኀጢአት ውድቀት የሚደርስብንን መናቅና ስድብ መታገሥ አንድ ነገር ነው፤ ነገር ግን ስለ እግዚአብሔርና ስለ ስሙ መታገሥና መከራ መቀበል እጅግ ሌላ ነገር ነው። ዓለሙ በክፉ እንደ ተያዘ ለሚያውቅ አማኝ (1ዮሐ. 5፥19)፣ ከእግዚአብሔር ጋር በመወገኑ ብቻ ለዓለሙና ለወገኖቹ መሳለቂያ ሊኾን ይችላል።ዘማሪው እውነተኛ ጻድቅ ነውና፣ ለሕዝቡ ኀጢአት ለማልቀስ ማቅ በለበሰ ጊዜ፣ እየተዘባበቱ ስቀውበታል (69፥11)፤ “በአደባባይ የሚቀመጡት ያሙኛል፤ ሰካራሞች በዘፈን ይሰድቡኛል” (ቊ. 12) እንዲል።

Wednesday, 16 October 2024

ኤርምያስ፤ ፍርድና ተስፋን ተናጋሪ ነቢይ!

 Please read in PDF

የእስራኤልን ወደ ባቢሎን መማረክ፣ ፊት ለፊት ከተናገሩት ነቢያት መካከል ቀዳሚው ነቢዩ ኤርምያስ ነው። ነቢዩ ዘመኑን በእንባና በልቅሶ ያሳለፈና አብዝቶ ከማልቀሱም የተነሣ “አልቃሻው ነቢይ” የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው ነው። የኤርምያስ ዘመኑ ብቻ ሳይኾን ሕይወቱም ጭምር አሳዛኝና በሕመም፤ በሰቆቃ የተሞላ ነበር።

Friday, 4 October 2024

“አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” (ማቴ. 16፥16)

Please read in PDF

ጌታችን ኢየሱስ፣ በምድርም ኾነ በሰማይ ካለ ከየትኛውም ፍጡር፣ ባህልና ልምምድ፤ ከየትኛውም የዓለም ሥርዓትና አስተዳደር ጋር አይወዳደርም! ቅዱስ ጴጥሮስ ይህን በማስተዋል ነው፣ የተገለጠለትን እውነት የመሰከረው። ይህ ቅዱስ ምስክርነት፣ ክርስትና ተንጣልሎ የተመሠረተበት ሕያውና ዘላለማዊ መሠረት ነው። የቤተ ክርስቲያን ሕይወት፣ ተልእኮ፣ ታላቅ ተስፋና ዘላለማዊነት የተወሰነውና የሚጸናው፣ ይህን ታላቅ ምስክርነት በመቀበልና በማመን ብቻ ነው።

Thursday, 3 October 2024

“ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ” (ፊል. 4፥4)

 Please read in PDF

የፊልጵስዩስ ቤተ ክርስቲያን፣ በኹለተኛው የቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያዊ አገልግሎት የተወለደች ቤተ ክርስቲያን ናት። ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ኹለተኛው ሐዋርያዊው ጉዞው፣ ብዙ መከራና እንግልትን ተቀብሎአል። የመጀመሪያው ሐዋርያዊው ጉዞው ብዙ መከራ የሌለበትና ቀለል ያለ ነበር፤ ኹለተኛው ግን ጠንካራና በብዙ መገፋት ውስጥ ያለፈበት ነው።

Sunday, 29 September 2024

ኢየሱስ “ከሃይማኖተኝነት” ይበልጣል!

"... ወደ የትኛውም ሃይማኖት ዛሬ ተነስታችኹ ለመግባት ትችላላችሁ። ጴንጤ ለመኾን ግን መመረጥ ያስፈልጋል" (በጋሻው ደሳለኝ)

“ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።” (ኢየሱስ ክርስቶስ - ዮሐ. 10፥16)

Monday, 23 September 2024

የቤተ ክርስቲያን ሌላኛው ተግዳሮት!

 Please read in PDF

የትምህርትም፤ የምግባርም ውድቀት፣ የቤተ ክርስቲያንን ኹለንተናዊ መልክ ከሚያበላሹ መካከል ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ። ትምህርቱ እንደ ኑፋቄ ያለ ሲኾን፣ ምግባራዊ ውድቀቱ ደግሞ እንደ ሰዶማዊነትና ዓለማዊነት ያሉ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲከሰቱ እጅግ ጆሮን ጭው ያደርጋሉ። እኒህን ተግባራት የሚፈጽሙ ሰዎች አንዳንድ[?] በ“ሃይማኖት” ጥላ ሥር ያሉ ሰዎች ስለ መኾናቸው ብዙዎቻን እማኝ ነን።

Saturday, 14 September 2024

ዘነበ ወላ(ጋሽ)ና ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ!

Please read in PDF

ዘነበ ወላ፣ ሰሞኑን ሥራና ምናኔን አስመልክቶ የሰጠው አስተያየት በብዙ ኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ጥርስ አስነክሶበታል። ብዙ ኦርቶዶክሳውያን የሰላ ትችት ሲሰነዘርባቸው፣ ችግሮቻቸውንና ስህተቶቻቸውን ከማረቅ ይልቅ፣ ቤተ ክርስቲያንን ለማዋረድ የሚነገር አድርጎ ማሰብ፣ “ልጅ እናቷን ምጥ አታስተምርም” የሚል አጉል ፈሊጥ መጥቀስ፣ ዛሬ መጥታችኹ ቤተ ክርስቲያንን ወንጌል ልትሰብኳት፣ ችግሯን ልታመለክቱ አትችሉም … የሚሉ አያሌ አሉታዊ ምላሾች ይቀርባሉ። ይህን ስንል ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማዋረድ የሚሠሩ የሉም ማለት አልችልም። ይኹንና ደግመን ደጋግመን መናገር የምንፈልገው፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ወደ እውነተኛ የወንጌል ጐዳና እስክትመለስና በመካከልዋ ያለውን “ዕድፍና ጉድፍ” እስክታስወግድ ድረስ “የተሐድሶ ድምጽ” ማሰማታችንን አናቆምም!

Wednesday, 11 September 2024

ዘመን የተጨመረልን በመግቦቱ ነው!

 Please read in PDF

የእግዚአብሔር መግቦት እጅግ አስደናቂ ነው። ጌታ ፍጹም መጋቢ ስለ ኾነ በፍጥረት መካከል አድልዎ ሳያደርግ የሚተገብራቸው አያሌ መግቦቶች አሉ፤ ቅዱሳት መጻሕፍትን ዋቢ አድርገን ምሳሌ ብንጠቅስ፦ “ርሱ[እግዚአብሔር] በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።” (ማቴ. 5፥44)፣ እንዲኹም እግዚአብሔር አምላክ ጋብቻን ባርኮ ለመላለሙ በአምላካዊ መግቦቱ መስጠቱን እናስተውላለን፤ (ዘፍ. 2፥24፤ ማቴ. 19፥4-5)።

Wednesday, 4 September 2024

የቁባቱን በድን የቆራጠው ካህን! (መሳ. 19-20)

 Please read in PDF

በእስራኤል ልጆች ታሪክ ውስጥ አያሌ አስከፊ ተግባራት ተከናውነዋል፤ ዛሬ የምናየው ይህ አንዱ ነው፤ “በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ በሌለበት ጊዜ በተራራማው በኤፍሬም አገር ማዶ የተቀመጠ ሌዋዊ ነበረ፤” (መሳ. 19፥1) ይላል፣ በመሳፍንት መጽሐፍ ውስጥ ከተቀመጡት የብንያም ሰዎችን የሥነ ምግባር ብልሹነትና በምላጭ ጫፍ ላይ መቆማቸውን ከሚያሳዩት ታሪኮች አንዱን ለመተረክ ሲነሳ።

በርግጥ ሌዋዊው ካህን ቁባቱን ፍለጋ ከኤፍሬም ወደ ቤተልሔም መሄዱ፣ ከአንድ ሚስት በላይ ማግባቱን ያሳያል፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ያለው ተግባር አልነበረም፤ በተጨማሪም፣ እግዚአብሔር ለእስራኤል ልጆች መሳፍንትን የሰጠው፣ ርሱ ብቻውን በነርሱ ላይ ሊነግሥ ነበር። ነገር ግን ለጌታ ከመታዘዝ ይልቅ፣ የሃይማኖት መሪዎቿ ድካምና ኃጢአት እያየለባቸውና እየባሰባቸው ሲሄድ በተደጋጋሚ እንመለከታለን።

Saturday, 31 August 2024

“ኑ ወደ ኦርቶዶክስ ተመለሱ!” ለምትሉን!

 Please read in PDF

ኦርቶዶክሳዊው ተሐድሶ እያየለና በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነትን እያገኘ ሲመጣ፣ በቃላት በማባበል፣ በጥቅምና በክብር በማማለል፣ መልሰን አናወግዛችሁም በሚል የተስፋ ቃል በመስጠት … እየቀረበልን ያለው ጥያቄ፣ “ኑ! ወደ ኦርቶዶክስ ተመለሱ!” ሚል ነው። ከዚህ በታች የምናስቀምጣቸው ጠንካራ ምክንያቶች የመመለስና ያለ መመለስን ጥያቄ ትርጕም ይሰጡታል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወደ ኋላ ስለ መመለስ በማስጠንቀቂያ አዘል ከተጻፉ መልእክቶች አንዱ፣ የዕብራውያን መልእክት ነው። የሐዋርያት ሥራን መጽሐፍ ስናጠና እንደምናስተውለው፣ አስቀድሞ ክርስትናን ለተቀበሉ አይሁድ የመጀመሪያዎቹ የቤተ ክርስቲያን ዓመታት እጅግ አስቸጋሪዎች ነበሩ። በእነዚህ ጊዜያት ክርስትና በአጭሩ የአይሁድ ሃይማኖት ኾኖ ነበር። ከ120ው የጌታ ቤተ ሰቦች (ሐ.ሥ. 1፥15) ጀምሮ ኹሉም በአንድነት ያመልኩና ያገለግሉ የነበረውም በአይሁድ ቤተ መቅደስ ውስጥ ነበርና፤ (ሐ.ሥ. 2፥46፤ 3፥1፤ 5፥42)።

Sunday, 18 August 2024

የ“ታቦር” ስብከቴን ቀይሬአለኹ!

 Please read in PDF

ጌታችን ኢየሱስ ክብረ መንግሥቱን የገለጠበት፤ ማንነቱን ለደቀ መዛሙርቱ ያሳየበት የክብሩ ተራራ እውነት እጅግ አስደናቂ ነው። ጌታ፣ በፊልጶስ ቂሣርያ፣ “ለብቻውም ሲጸልይ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩና፦ ሕዝቡ እኔ ማን እንደ ኾንሁ ይላሉ? ብሎ ጠየቃቸው።” (ሉቃ. 9፥18) ደቀ መዛሙርቱ ሲመልሱ፣ የነቢያትን ስም በመጥራት እንዲኹም ከነቢያት አንዱ ነህ ይላሉ ብለው መለሱ። ቀጥሎም፣ “እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።” (ሉቃ. 9፥20) “ጴጥሮስም መልሶ፦ ከእግዚአብሔር የተቀባህ ነህ አለ።”ቅዱስ ጴጥሮስ ይህን ታላቅ እውነት በመመለሱ፣ “ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።” (ማቴ. 16፥17) በማለት የጴጥሮስን ዕድለኝነት ጌታችን መሠከረለት።

Wednesday, 31 July 2024

ለእውነተኛ ተሐድሶ ኦርቶዶክስን አይጠቅማትም!

 Please read in PDF

ከጥቂት ዓመታት ወዲህ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከተደረጉ “ፖለቲካዊ የቤተ ክርስቲያን ውሳኔዎች” አንዱ፣ ሰዎች በቋንቋቸው ወንጌል ሊማሩ ይገባል የሚል ነበር፤ በዚህ ዐሳብ ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ “በወንጌል ልብ” በተደጋጋሚ ይጠይቁ ከነበሩ ሰዎች መካከል አንዱ በመኾኔ፣ በጥያቄው ፍጹም እስማማለኹ። ነገር ግን መልሱ የተሰጠውና በተግባር ላይ የዋለው ፍጹም መንፈሳዊ ባልኾነ መንገድ ባለ መኾኑ ሳዝን ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት እጽናናለኹ!


Sunday, 28 July 2024

የፓሪስ ኦሎምፒክ ሴሰ*ኝነት፣ ሰዶ*ማ*ዊነት፣ በጌታ እራት ሲሳ*ለቁ!

 

“ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥”
(ሮሜ 1፥22)

በዘመናት መካከል ዓለምና ሥርዓትዋ፤ ሰይጣንና ሠራዊቱ ለእግዚአብሔርና ለሥራው ኹሉ ጠላትነታቸውን ደብቀው አያውቁም። ቅዱሱ መጽሐፍ፣ የዚህ ዓለም ሰዎች፣ “... የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት እየ ለወጡ ...”(ሮሜ 1፥25) በጥበባቸው ደንቆሮዎች እንደ ኾኑ በግልጥ ይናገራል።


Friday, 19 July 2024

ስለ ኦርቶዶክስ በልቤ ያለ ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት!

 Please read in PDF

ከልጅነቴ ያደግኹት በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነው፤ የተጠመቅኹት፤ የቆረብኹት፤ በቅንአትና በትጋት ያገለገልኹት … በዚያ ነው። በዚያ የነበረኝ አገልግሎት በዕውቀትም በቅናትም እንደ ነበር ብዙዎች ምስክሮቼ ናቸው። የክብሩንና የትንሣኤውን ወንጌል በትክክል ስረዳና ስመሰክር ግን ብዙዎች ተቃወሙኝ፤ እናም አብረኸን ልትኾን አይገባም ሲሉኝና ሲገፉኝ ወጣኹ።

Friday, 5 July 2024

ወርቅ ሲደብስ!

 

ጳጳሱ ቅዱሳት መጻሕፍትን አላነበቡምን?

ጳጳሱ ለማርያም ያላቸው አስተምኅሮ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ በተቃራኒ የቆመ ነው፤ እንዲህ ያለ ነገር በርግጥ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ “የታወቁ መምህራን” የሚናገሩት ነው፤ ከዚህ ቀደም ዲያቆን ኃይሌ፣ “እመቤታችን ማማለድ አይደለም አፍርሳን መሥራት ትችላለች” ብሎ መናገሩንና ለዚህም ምላሽ መስጠታችን ይታወሳል፡፡ ለምን ኾን ብለው ማርያምን በማግነንና በማስመለክ፣ እግዚአብሔርንና ስሙን መሳደብ እንደሚፈልጉ አላውቅም፤ እግዚአብሔርንና እግዚአብሔር በልጁና በመንፈሱ የሠራውን ሥራ ባለማወቃቸውም እጅግ እደነቃለሁ!

Tuesday, 2 July 2024

ጌታ ኦርቶዶክስን በወንጌል ሊጎበኝ እያሰበ ቢኾንስ?

Please read in PDF

“የስብከተ ወንጌል”ና “የመንፈስ ቅዱስ ቀን”

በኹለቱ ተቋማት ዕይታ!

በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማርቆስ አማካኝነት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ሰኔ 24ን “የስብከተ ወንጌል” ቀን ብላ ሰይማለች፤ ዓላማውንም ጳጳሱ እንዲህ ብለው ያስረዳሉ፣ “የስብከተ ወንጌል ቀን ሲባል ስብከተ ወንጌል የሌለበት ቀን የለም። የወንጌልን ቀን ማክበር የተፈለገበት ዕውቅናን ለመስጠት ነው፤ ይበልጥ በትውልዱ አእምሮ … ዛሬ የወንጌል ቀን ብሎ እንዲያዘክረው እንዲያከብረው … ሕፃናት ጭምር እንዲያውቁት ነው ትልቁ ዓላማው።” መሪ ቃሉም፣ “በወንጌል ተልእኮ ትውልዱን መታደግ” የሚል እንደ ኾነ ተጠቅሶአል።




Sunday, 9 June 2024

ሰኔ 16 ቃለ አዋዲ፤ ሰኔ 23 ማኅበረ አኀው አይቀርም!

 

“ዘወትር እየተገናኘን ርስ በርሳችን እንበረታታ እንጂ አንዳንዶች ማድረግ እንደ ለመዱት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም የጌታ መምጫ ቀን መቃረቡን እያስታወሳችሁ ይህን ነገር በይበልጥ አድርጉ።” (ዕብ. 10፥25)

የዕብራውያን አማኞች፣ መንፈሳዊ ኅብረትን ስደትን ከመፍራት የተነሣ ተወት አድርገው ነበር፤ እናም ብዙዎች ወደ መንፈሳዊ ኅብረቶች ከመሄድ ይልቅ፣ በየቤቶቻቸው ተቀምጠው ነበር። ሌሎች ደግሞ አይሁድና አሕዛብ በአንድነት ኅብረት ሊያደርጉ አይገባቸውም የሚለውን ትችትና ነቀፋ በመፍራት ኅብረት ከማድረግ አፈግፍገው ነበር። ነገር ግን እኒህና ሌሎች በቂ የሚመስሉ ምክንያቶች ቢኖሩም፣ ከመንፈሳዊ ኅብረት መታጎል ወይም መቅረት ፍጹም ትክክል አይደለም።



Jajjabina isa Waaqayyoo (kutaa 1ffaa)

 

Sunday, 2 June 2024

ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፲፪)

 Please read in PDF

ካለፈው የቀጠለ …

2.   ጹም ፍቅርእግዚአብሔርም[ሥላሴ] ፍቅር ነው (1ዮሐ. 4፥16)፤ ይህ ፍቅር፣ ፍጥረት ከመፈጠሩ በፊት በሥላሴ ዘንድ ያለ ነው፤ ጌታችን ኢየሱስ፤ “ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ … ።” (ዮሐ. 17፥24) ብሎ ሲናገር፣ አብና ወልድ ከዘላለም ጀምሮ ይዋደዱ እንደ ነበርና አብም ለወልድ የሚሰጠው ክብር እንዳለ ያሳየናል። “አባት ልጁን ይወዳል” እንዲል (ዮሐ. 3፥35)።



Wednesday, 29 May 2024

የድል መንገድ!

 Please read in PDF

መስቀልና ትንሣኤ ሊነጣጠሉ የማይቻላቸው፣ የክርስትና የአንድ ሳንቲም ኹለት ገጽታዎች ናቸው። መስቀሉ ውርደትን፣ ሽንፈትን፣ አለልክ ዝቅ ማለትን በውስጡ የያዘ ቢኾንም፣ ድል መንሣትን፣ ሙሉ ለሙሉ የተፈጸመ ወይም የተጠናቀቀ የኅጢአት ክፍያን (ዮሐ. 19፥30)፣ ጠላትን ጠርቆ ከመንገድ ማስወገድን ኹሉ (ቈላ. 2፥14) አጭቆ የያዘ፣ የክርስትና እጅግ አስደናቂ መንገድ ነው።

Sunday, 19 May 2024

ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፲፩)

 Please read in PDF

ገረላሴንጥናታችንስተምረናል?

1.   ሥሉሳዊ አንድነትበሥላሴ ዘንድ ፍጹም አንድነት አለ፤ አንድነታቸውም ፍጹም የኾነና እንከን አልባ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ፣ የጌታችን ኢየሱስን ንግግር ሲናገር እንዲህ አለ፤ “እኔና አብ አንድ ነን።” (ዮሐ. 10፥30)። ጌታችን ኢየሱስ ይህን ሲናገር፣ አብ በእርሱ፤ እርሱም በአብ በማይለያይ ዘላለማዊ መለኮታዊ አንድነት አብረው መኖራቸውን ማስተዋል ይቻላል።



Sunday, 5 May 2024

በእውነት አገኘችው!

 

በድኑን በሽቱ ልትቀባው ሽታ

በብርቱ ስትፈልግ ተርባ ተጠምታ

አጽንታ በትጋት በድቅድቅ ጨለማ

የሴትነት ፍርሃት ኹሉን ተቋቁማ ...

Saturday, 4 May 2024

Fiixaan Baheera!

 Fannoo irra nuuf oolu isaatiin gatiin cubbuu keenyaa guututti kafalameera; foon uffatee nuuf du'u isaatiin hamannaan seexanaa kammiyuu nurraa ka'eera; dadhabaa fakkaatee fannoo irratti mul'atuus inni Gooftaan keenya Yasuus du'a fi awwaala mo'achuun hunda Goonfateera! Ameen!



Friday, 3 May 2024

የታመመ፤ የተሰቀለ!

 Please read in PDF

መላለሙን የፈጠረው አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ድል ነሺና አሸናፊ፤ የነገሥታት ንጉሥ ነው። ኹሉ ከእርሱ በታች ያለና የተገዛለትም ነው። ያለ እርሱ የኾነ ምንም እንደሌለ እንዲኹ፣ ያለ እርሱ ኹሉም ነገር ከንቱና እርባና ቢስ ነው። “የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢኾኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል”። እርሱ ከኹሉ በላይ አምላክና ገዥ ነው።

Sunday, 28 April 2024

Hoosa'inaa!

"Hoosaanaa! " kan maqaa Gooftaatiin dhufu eebbifamaa dha! "Mootiin Israa'eli eebbifamaa dha."

 

Friday, 12 April 2024

በብልጽግና ወንጌል የተለከፈ …

 Please read in PDF

በእግዚአብሔር ጸጋ ፍጹም አምናለሁ፤ ዳሩ ግን በ”ብልጽግና” ወንጌል አንዴ የተለከፉትን፤ እነርሱን በንስሐ ማደስ እጅግ ከባድ ነው፡፡ ምክንያቱም ትምህርቱ፣ የቀደሙትን ሰዎች አዳምና ሔዋንን እንዳሳተው አሳች፣ አንተን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስተካክል አጋንንታዊ ትምህርት ነውና፡፡ ለዚህ ነው ዶክተር ተካልኝ “የጸሎት-ንግድ ቤት” በሚለው መጽሐፉ እንዲህ በማለት የሚጠይቀውና የሚመልሰው፣

“… በእግዚአብሔር ማመንን ወደ “እንደ እግዚአብሔር ማመን” ቀይሮ ክርስትና የሚባል እምነት ይኖራልን? ፈጽሞ፤ … የትምህርቱ ኹሉ ነገር እምነት በሚባል አስገዳጅ ኃይል እግዚአብሔርን ጨምሮ ነገሮችን ኹሉ ለሰው ጥቅም ማስገዛት እና ማስገበር ነው፡፡” (ገጽ 60) ይላል፡፡



Monday, 8 April 2024

Monday, 1 April 2024

እባክህን ማረን !

 Please read in PDF

አገር ትድኻለች በረሃብ እንፉቅቅ

ትውልድ ይራኮታል በዋይታና በጭንቅ

Friday, 29 March 2024

“በእግዚአብሔር ቤት መኖር” (መዝ. 27፥4)

 Please read in PDF

ንጉሥ ዳዊት የገዛ ቤተሰቡ ማለትም አቤሴሎም ልጁ ሳይቀር፣ ከሥልጣን ሊያወርዱት በክፋት አሲረውበታል፤ ፍጹም ካሴሩበት ሰዎች እግዚአብሔር እንዴት ባለ ታላቅ ትድግና እንደሚያድነው በመተማመን ያቀረበው የጸሎት ክፍል ነው። ጸሎቱ የኪዳኑን አምላክ በማሰብና በመታመን (2ሳሙ. 7) የቀረበ ሲኾን፣ በጌታ ላይ ያለውን ጽኑ እምነትም በይፋ የሚመሰክርና የሚያውጅ ጸሎት ነው። ጠላቶቹ የቱንም ያህል ጠንካራና ብርቱዎች ቢኾኑም፣ ለመዝሙረኛው ግን እግዚአብሔር ብርሃንና የኹሉ ነገር ምንጭ፤ ሰላምና መታመኛው ነው።

Tuesday, 26 March 2024

ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፲)

 Please read in PDF

ካለፈው የቀጠለ …

  1. ስሞቹ አጠራርና አጠቃቀም ረገድ የሚያመጣው ተፋልሶ የለም።

የሥላሴን ትምህርት በትክክል የማይረዱ ሰዎች ከሚሠሯቸው ስህተቶች መካከል አንዱ፣ በስሞቻቸው አቀማመጥ መሠረት የሥልጣን ተዋረድና የማቀዳደም ሥራ መሥራታቸው ነው። በማቴዎስ ወንጌል አጠቃቀም ውስጥ፣ “አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ” ብሎ (ማቴ. 28፥19) መጥራት የተለመደና በብዙዎች ዘንድ “ተቀባይነት” ያለው አጠራር ነው።

Sunday, 24 March 2024

ምኩራብ

 Please read in PDF

አይሁድ በምርኮ ዘመን መሥዋዕት የሚያቀርቡበት መቅደስ ስለ ፈረሰባቸውና፣ ወደ አገራቸውም ተመልሰው መሥራት ስላልተቻላቸው፣ በየጊዜው የሚገናኙበትንና ቃሉን በማንበብ፣ በመተርጐም የሚተጉበትን ምኵራብን መሥራት ጀመሩ። በምኩራብ ራቢ ወይም መንፈሳዊ መሪ ያለ ሲኾን፣ ሌሎች ደጋፊ ሰዎች ወይም ሠራተኞችን በተካተቱበት የሚመራ አነስተኛ ጉባኤ ነው።

Sunday, 17 March 2024

የ“ነቢይ” ጥላሁን ነገረ ማርያም!

 Please read in PDF

የ“ነቢይ” ጥላሁንን የተወሰኑ ስብከቶችን የማድመጥ ዕድል አጊኝቼ አውቃለሁ፣ በኋላ ግን እርሱም “በግሉ” ወደ “ቸርች ከፈታ” ሲያዘነብል ተደንቄ ራቅኹት። ከሰሞኑ ደግሞ ስለ ማርያም የተናገረውን አይቼ፣ የነዶክተር ወዳጄነህንና የነፓስተር ቸሬን መንገድ ለመከተል ምን አደከመው? ብዬአለሁ። በስብከቱ መካከል ማርያምን (የጌታ ኢየሱስን እናት) “እየሰበከ” በመካከል እንዲህ ይላል፣

 " ... የወንጌላውያን ጸሐፊዎች [አራቱ ወንጌላትን ማለቱ ነው] የማርያምን ኹኔታ ስላላወቁና እርሷም ምናልባት አብራርታ ስላልነገረቻቸው እንጂ ... መለኮት ልትወልጂ ነው ሲላት …" ይላል፡፡


Tuesday, 12 March 2024

እኔ ነኝ አድራሻው!

Please read in PDF

 ጌቶችና አለቆች  ገናና ክቡራን

በሰው ፊት ታላላቅ የኾኑ ኃያላን

ለምድር ለከበዱ ታዋቂ ምሑራን

ለግብዝ አስመሳይ ለሚወዱ ዓለምን …

Friday, 8 March 2024

ኢየሱስ እስኪመጣ - ላለፉት አሥራ አንድ ዓመታት!

 

የማይዋሸውና (ቲቶ 1፥2) በምሕረቱ ባለጠጋ የኾነ እግዚአብሔር (ኤፌ. 2፥4)፣ ነፍሴም ሕያው ወደ አደረጋት ሕያው አምላክዋ ሳትመለስ (መክ.12፥7) ኢየሱስ እስኪመጣ ድረስ ዕንኾ፣ አሥራ አንድ ዓመታት በብሎግ(በጡመራ መድረክ) አገልግሎት በጌታ ፊት አለኹ! በዚህ አጭር ዘመኔ ከእርሱ በቀር የረዳኝ፣ ያጸናኝ፣ ከፍ ከፍ ያደረገኝ፣ ሞገስ የሰጠኝ፣ ብርሃኑን ያበራልኝ፣ ስጠወልግ ያለመለመኝ፣ ስደክም መንገድ አቋርጦና አሳብሮ መጥቶ ያበረታኝ፣ እጆቼን ይዞ “አይዞህ!” ያለኝ ከጌታ በቀር ማንም የለም፤ ክብር ይኹንለት!

Thursday, 7 March 2024

መንፈሳዊውን ጾም እንጹም!

Please read in PDF

ጾም፣ በብሉይም ኾነ በአዲስ ኪዳን አማኞች ዘንድ፣ በጐላ መልኩ ሲተገበር የነበረ ደግሞም ያለ መንፈሳዊ ልምምድ ነው። ጾም በአማኞች ሕይወት እንደ መለኮታዊ ተግሳጽ የሚፈጸም መንፈሳዊ አምልኮም ነው። በብሉይ ኪዳን ንስሐ ሲገቡ (1ሳሙ. 7፥6)፣ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ፣ ከእግዚአብሔር ዕርዳታ ለመፈለግ (ዘጸ. 34፥28፤ ዕዝ. 8፥21-23)፣ ራስን በመንፈሳዊ ተግሳጽ ለመገሰጽና የኀጢአት ኑዛዜ በእግዚአብሔር ለማቅረብ መንፈሳውያን ሰዎች በግል (2ሳሙ. 12፥22) ወይም በማኅበር (መሳ. 20፥26፤ ኢዩ. 1፥4) በእግዚአብሔር ፊት ይጾሙ ነበር!

Tuesday, 5 March 2024

ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፱)

Please read in PDF

ካለፈው የቀጠለ …

  • ንፈስ ቅዱስ፦ መንፈስ የኾነ (ዮሐ. 4፥24)፣ ፍጥረትን በመፍጠርና በውበት በማጌጥ (ዘፍ. 1፥2)፣ ከርሱ በመወለድና አዲስ ልደትን ለአማኞች የሚሰጥ (ቲቶ 3፥5)፣ ኃይልን በማልበስና የጸጋ ስጦታን ለቤተ ክርስቲያን በመስጠት ወይም በማከፋፈል (ዘካ. 4፥6፤ የሐ.ሥ. 1፥8፤ 1ቆሮ. 12፥7-11) በጽደቅ ፍሬዎች በመሙላትና በመቀደስ በአማኞች ሕይወት ውስጥ የሚኖር (ዮሐ. 14፥17፤ 1ቆሮ. 3፥16፤ 6፥19፤ ገላ. 5፥22-23፤ ኤፌ. 2፥22)፣ አብሮን በጸሎት የሚቃትት (ሮሜ 8፥26)፣ ቅድስት ድንግል ወልድን በተለየ አካሉ በሥጋ እንድትፀንስ በፈቃዱ ወድዶ የመጣ (ማቴ. 2፥11) የዘላለም እግዚአብሔር ነው፤ (ዕብ. 9፥14)።

Friday, 1 March 2024

ድንግል ማርያም የአሚናዳብ ሠረገላ?

Please read in PDF

“የዛሬን አያድርገውና” ዲያቆን ትዝታው ሳሙኤል፣ ለድንግል ማርያም “ከዘመራቸው ዝማሬዎች” መካከል “የአሚናዳብ ሠረገላ” የሚል ይገኝበታል። ብዙ አገልጋዮች ከኦርቶዶክስ አገልጋይነታቸው ራሳቸውን አግልለው ወደ ወንጌል እውነት ሲመለሱ፣ አስቀድሞ “ለፍጡራን በግልጥ የዘመሩትን ዝማሬ” በትክክል ስህተት መኾኑን አምነው፣ ንስሐ ሲገቡ አላየኹም፤ ምናልባት የገቡ ካሉና መግባታቸውም እንደ ዝማሬያቸው አደባባያዊ ከኾነ እንዴት መልካም ነበር!

Monday, 26 February 2024

እግዚአብሔር ለአሕዛብም ግድ ይለዋል!

Please read in PDF

እግዚአብሔር የሰማይና የምድር ፈጣሪ ነው፤ “እነሆ፥ ሰማይ ሰማየ ሰማያትም፥ ምድርም በእርስዋም ያለው ሁሉ የአምላክህ የእግዚአብሔር ነው።” (ዘዳግ. 10፥14) እንዲል፣ ከእግዚአብሔርና ለእግዚአብሔር ያልኾነ ፍጥረት ፈጽሞ የለም። በአዲስ ኪዳንም፣ “እርሱ[እግዚአብሔር] በክፎዎችና በበጐዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።” (ማቴ. 5፥44-45) በሚለው ንግግሩ እግዚአብሔር ለመላለሙ ግድ ይለዋል።

Tuesday, 13 February 2024

ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፰)

Please read in PDF

ካለፈው የቀጠለ …

5.2. ሥላሴ ምግባራዊ ሦስትነት (Economic Trinity) አላቸው

በሌላ ንግግር አብ ከወልድ ወይም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለውን ዐይነት ግንኙነት፣ ከፍጥረት ጋርም እንዲያ ያለ ግንኙነት የለውም። በሥላሴ መካከል ያለውን ኅብረትና አንድነት የሚያመለክተው ግንኙነት፣ ምግባራዊ ሦስትነት (Economic Trinity) ተብሎ ይጠራል። በዚህ ረገድ የሥላሴ እያንዳንዱ አካል በመለኮታዊ ማንነቱ ፍጥረትን በመፍጠር፣ በመመገብ፣ በልዕልና በመምራት፣ በሥልጣን፣ በአገዛዝ፣ በማዳን በሚሠሩት መለኮታዊ ሥራዎች ያላቸውን ፍጹም አንድነት የሚያመለክት ነው።

Friday, 19 January 2024

“እያጠመቃችኋቸው፥ … እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤” (ማቴ. 28፥20)

 Please read in PDF

ለቤተ ክርስቲያን ከተሰጡ ሐዋርያዊ ተልእኮዎች ውስጥ፣ ቀዳሚውና የዘወትር ተግባር “አማኞችን ደቀ መዛሙርት ማድረግ” ነው። እንደ ጌታችን ትምህርት፣ አማኞች ደቀ መዛሙርት የሚኾኑት፣ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሲጠመቁ፣ ጌታ ያዘዘውን ኹሉ እንዲጠብቁ ሲማሩ፣ እንዲሁም በመታመን እርሱን ለመከተል ደቀ መዛሙርት በሕይወት ሲኾኑ ነው።

Thursday, 18 January 2024

“ከእኛ ጋር ለምን አስተካከልሃቸው?” (ማቴ. 20፥11)

 Please read in PDF

ጌታችን ኢየሱስ መንግሥተ ሰማያት ምን እንደምትመስል በሰጠው ውብ ምሳሌ፣ እግዚአብሔርን የወይኑ እርሻ ባለቤት አድርጎ ያቀርበዋል። የእርሻው ባለቤት በአትክልቱ ስፍራ ሰውን ለመቅጠር ፈልጎ ጥሪ አቀረበ። በጥሪው መሠረት ሠራተኞቹ፣ አንድ ዲናር ሊከፈላቸው ተስማምተው ወደ እርሻው ቦታ መጡ። የሥራው ሰዓትም ከማለዳ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓት ነበር።

Wednesday, 17 January 2024

ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፯)

 Please read in PDF

ካለፈው ቀጠለ …

   5. የቅድስት ሥላሴ ትምህርት ምስጢር ነው!

ትምህርተ ሥላሴ ምስጢር ነው ስንል፣ ምን ማለታችን ነው? ብንል፣ ለሰው ያልተገለጠ ብዙ ትምህርት ወይም ብዙ ነገር አለ ማለታችን ነው። ኾኖም ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ሦስቱን አካላት ለማጥናት ብዙ ትምህርት እንዳለ ልንዘነጋ አይገባም። በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ትምህርቶች ምስጢር ተብለዋል፤ ለምሳሌ፦ ጌታችን ኢየሱስ፣ ለደቀ መዛሙርቱ፣ “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፥ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።” ሲል (ማቴ. 13፥11)፣ ምሳሌዎቹ የተነገሩት በሕዝቡ ኹሉ ፊት ቢኾንም፣ ትርጕማቸው ወይም ምስጢሩ ግን የተነገረው ለደቀ መዛሙርት ብቻ ነው።



Thursday, 11 January 2024

Sagantaa Addaa Ayyaana Yaadannoo Dhaloota Kiristoos!

" ... Ishiini ilma deetti; atis maqaa isaa Yesuus jettee moggaafta; inni saba isaa cubbuu isaanii irraa ni fayyisaatii." (Matt. 1:22)

 

Saturday, 6 January 2024

ከባሪያዪቱ የተወለደ ንጉሥ!

 Please read in PDF

የክርስትና ትምህርት ከደመቀበትና ከተንቈጠቈጠበት ቀዳሚው እውነት አንዱ፣ የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ የሚያምኑትን ኹሉ በጸጋ የእግዚአብሔር ልጆች ያደርግ ዘንድ የሰው ልጅ መኾኑ ነው። እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ኾኖ፣ ዓለማትን የፈጠረና ደግፎም የያዘ ወይም ዓለሙ ተያይዞ የቆመው (ዮሐ. 1፥3፤ ቈላ. 1፥17፤ ዕብ. 1፥3) በእርሱ በታላቁ አምላክ ቢኾንም፣ በተለየ አካሉ  ከባሪያዪቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም (ማቴ. 1፥21፤ ዮሐ. 1፥14) ሥጋን ነሥቶ ተወለደ።

Monday, 1 January 2024

መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፳፯)

 Please read in PDF

ካለፈው የቀጠለ …

ባለፈው “የመድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ (Exegesis) ሳይኾን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ (Eisegesis) እንደሚተረጕም አንድ ምሳሌ አንስተን ነበር። ዛሬ በድጋሚ ኹለተኛ ምሳሌ በማንሳት በዚህ ርዕስ ሥር ያለውን ዐሳብ እንቋጫለን።