Thursday 27 June 2019

ሰዶማዊነት - መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ! (የመጨረሻው ክፍል)


የሰዶማውያን ስውር ደባ
    በግልጥ ማንነታቸው ቢመጡ የሚቀበላቸው እንደሌለ ያውቁታል፤ ስለዚህም ስውርና ሰዎች ቀስ በቀስ ወይም በድንገት እንዲላመዱ የሚያደርጉባቸው መንገዶች አሏቸው፤ ለምሳሌ፦ የታወቁ የፊልም አክተሮችን በዋና ተዋናይነት ማጫወት፣ በሕጻናት ፊልሞች ውስጥ ሰዶማዊነትን መሰንቀር [ስንቶቻችን ለሕጻናቶቻችን ፊልሞችን አስቀድመን አይተን መርጠን እናቀርብላቸዋለን?]፣ በአኹን ሰዓት ከክርስቲያን ፊልሞች በቀር በማናቸውም ፊልሞች ላይ እጅግ በአብላጫው የሰዶማውያንን ሃሳብ እናያለን፣ ቀስ በቀስ ያላምዱናል፣ በቀዝቃዛ ውኃ ጥደውን ቀስ አድርገው እሳቱን እያነደዱ መቀቀልና መፍረስን ያላምዱናል፤ ምልክቶቻቸውን በተቃውሞ መልክ እንድናሠራጭ ይቈሰቁሳሉ፤ በዚህ ረገድ የአገራችን የቅርቡ ኹኔታ በሚገባ ተሳክቶላቸዋል፡፡

Friday 21 June 2019

ሰዶማዊነት - መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ! (ክፍል አንድ)

   እግዚአብሔር አምላክ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ከወጡ በኋላ፣ ወደ ተስፋይቱ ምድር በተቃረቡ ጊዜ በተደጋጋሚ የተናገራቸው ቃል ቢኖር እንዲህ የሚል ነው፤ “… ዛሬ እኔ አንተን የማዝዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን ሥርዓቱንም ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ፤” (ዘዳግ. 8፥11፤ 4፥9፤ 6፥25)። የታዘዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን ሥርዓቱንም ሊረሳ የሚችልባቸውን ምክንያቶችንም ሲያስቀምጥ እንዲህ ይዘረዝራቸዋል፤

   “ከበላህና ከጠገብህ በኋላ፥ መልካምም ቤት ሠርተህ ከተቀመጥህበት በኋላ፥ የላምና የበግ መንጋ ከበዛልህ በኋላ፥ ብርህና ወርቅህም ያለህም ሁሉ ከበዛልህ በኋላ፥ ልብህ እንዳይጓደድ፤ ከግብፅም ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን፥ እባብና ጊንጥ ጥማትም ባለባት፥ ውኃም በሌለባት፥ በታላቂቱና በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራህን፥ ከጭንጫ ድንጋይም ውኃን ያወጣልህን፥ በመጨረሻም ዘመን መልካም ያደርግልህ ዘንድ ሊፈትንህ ሊያዋርድህም አባቶችህ ያላወቁትን መና በምድረ በዳ ያበላህን አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ፤ በልብህም፦ ጉልበቴ የእጄም ብርታት ይህን ሀብት አመጣልኝ እንዳትል። ነገር ግን ዛሬ እንደሆነ ለአባቶችህ የማለውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ፥ ሀብት ለማከማቸት እርሱ ጉልበት ሰጥቶሃልና አምላክህን እግዚአብሔርን አስብ።” (ዘዳግ. 8፥12-18)

Sunday 16 June 2019

አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ

Please read in PDF

   ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል ከተነሣ በሃምሳኛው ቀን፣ ወደ ሰማያት ባረገ ደግሞ በአሥረኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ገባላቸው ተስፋ ቃል ከአባቱ ዘንድ በመላክ የቤተ ክርስቲያን ልደት አብስሮአል።
   ከግሪኩ “ፓራክሊቶስ” ወይም ከዕብራይስጡ “ፕራቅሊጥ” ከሚለው ግስ የተገኘው፣ “ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል ትርጉሙ፦ “አማላጅ፣ አስታራቂ፣ አፍ፣ ጠበቃ፣ ትርጁማን፣ አምጃር፣ እያጣፈጠ የሚናገር፣ ስብቅል ካፉ ማር ጠብ የሚል።…፤ ናዛዚ፣ መጽንዒ፣ መስተፈስሒ፤ መንፈስ ቅዱስ” በማለት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ተርጉመውታል። [1]

Monday 10 June 2019

ይድረስ ለውድ እህቴ ዘርፌ ከበደ … !

ይህ ጽሑፍ ዘማሪት ዘርፌ ወደ ስሑት መምህራን ጐራ ባለችበት ወቅት የተጻፈ ነበር፤ ነገር ግን ጽሑፉን ከተመለከቱ ወንድሞች መካከል ጥቂቶች አስተያየቶችን ስለ ሰጡኝ ለጊዜው ከማውጣት አዘግይቼዋለሁ፤ ዘርፌ ግን አኹንም ከፊተኛ ስህተትዋ የሚብስ፣ እንኳን ለመንፈሳዊነት ለአመክንዮ የማይመጥን “ከኦርቶዶክስ የለቀቅሁበት ምክንያቴ” የሚል ርእስ ሊሰጠው የሚችል ምስለ ወድምጽ(Video) ሠርታ ለቅቃለች።

አንዳንድ አገልጋዮች የራሳቸውን አገልግሎት ትክክል ለማድረግ ሲሉ ብቻ፣ አእላፋት በኹለንተናቸው ዋጋ ከፍለው የሚያገለግሉትን ደገኛ አገልግሎት፣ ጥላሸት ለመቀባት ሲዳዱ ማየት እየተለመደ መጥቷል፤ አለመታደል! እንዲህ ከማድረግ ልከኛ የአገልጋይ ጠባይ ይዘን ብናገለግል እጅግ መልካም ነበር፤ ከአገልግሎት በፊት አገልጋይ መኾን ይቀድማልና፤ ሽብርቅና ድምቅ ያሉ አገልግሎቶች ኹሉ አገልግሎት እንዳይደሉ፣ ሰው እንጂ ክርስቶስ እንዳይከብርበት በአጭር ዕድሜዬ አይቻለሁ።
እናም ምንም ሳይለወጥ ጽሑፉን ማውጣት አስፈላጊ መስሎ ስለ ታየኝ ጽሑፉን እንዳለ እንዲህ አውጥቼዋለሁ፤ መልካም ምንባብ …

Thursday 6 June 2019

“እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ” (ሐዋ. 1፥9)

Please read in PDF
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ፣ “አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው” (ሐዋ. 1፥3)። የጌታችን ትንሣኤ እውነታነቱ በታሪክ ማስረጃም ጭምር ያሸበረቀ ነው፤ ታሪክ ሊክደው በማይችለው መልኩ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል ሰውነቱን ሳይጥል ተነሥቶአል። መነሣቱንም ለደቀ መዛሙርቱ በብዙ ማስረጃዎች አስረግጦ አሳይቶአል፤ ለድንጉጥ፣ ለተጠራጣሪ፣ ተስፋ ቆርጠው ወደ ገዛ መንገዳቸው ላዘነበሉት፣ በሃዘን ለተሰበሩት፣ ብዙ ጊዜ በመፍራትና በመስጋት ወደ ኋላ ለመመለስ ያመነቱ ለነበሩት ደቀ መዛሙርት ባለ ብዙ ምሕረት ኢየሱስ ሳይታዘባቸውና ሳይጠየፋቸው ፍጹም በተደጋጋሚ ተገልጦ ታያቸው፤ ራሱንም ገለጠላቸው።