Sunday 27 March 2016

መፃጉዕ - ለአገሬ፥ ሰው የሚሆንላት ማን ይሆን!?

    
 ዜመኛው ቅዱስ ያሬድ የዓቢይን ጾም ሳምንታት በሰየመበት ስያሜው፥ ይህን ሳምንት መፃጉዕ ብሎ ሰይሞታል፡፡ ትርጓሜው በቁሙ ሲፈታ “ጐባጣ” ማለት እንደሆነ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ(አለቃ) መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በሚለው መዝገበ ቃላቸው ገጽ 605 ላይ ፈትተውታል፡፡ ለስያሜው መሰጠት ምክንያቱ ደግሞ ቅዱስ ያሬድ የአጽዋማቱን ሳምንታት ስያሜዎች ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲወርሰው አድርጎታል፡፡ ይህ ስያሜም በምን ምክንያት ከጌታ ጋር እንደተገናኘ ሲናገር እንዲህ አለ፦
“በሰንበት ቀን ኢየሱስ ታላላቅ ተአምራትን ያደርግ ነበር፡፡ ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ ያደረገውንም እናገራለሁ፡፡ ጭቃ ደህናውን ዓይን ያጠፋል፣ እርሱ ግን በምድር ላይ ተፍቶ ጭቃ አድርጎ ዕውር ሆኖ የተወለደውን አዳነ፡፡ ይህ ግሩም ምስጢር ነው፡፡”

Friday 25 March 2016

ቀሲስ የ“ክብረት ልጅ”፥ ምነው በስድብ ቃል በጣም ጮኸ?!

 የክብረት ልጅ እይታዎቹን በሚያቀርብበት ብሎጉ፥ “ፓትርያርኩ፦ ለኢትዮጲያ የደኅንነት ፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት” በሚል አንድ ጽሁፍ፥ ዛሬ አስነብቦ ድንገት ያየ ሰው ጠቆመኝና ወደጡመራው መድረኩ ገብቼ አነበብኩት፡፡ ዳንኤል በዚህ ጽሁፉ “100% ማኅበረ ቅዱሳን ሊያዘጋጀው ከጫፍ የደረሰውን ዐውደ ርእይ የከለከሉት ፤ ያስከለከሉት ፓትርያርኩ ናቸው”፥ ብሎ ደምድሞ አስቀምጦታል፡፡ የዐውደ ርእዩ ባለቤት ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ፥ በዋናው ጸሐፊው አቶ ተስፋዬ ቢኾነኝ በኩል ትላንት ማምሻውን ለጋዜጠኞች በሰጠው ጋዜጣዊ “መግለጫ”፥ “ለመታገዱ ፓትርያርኩ እንደሌሉበትና በመንግሥት አካላት መመሪያ መታገዱን”ይፋዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ 

Wednesday 23 March 2016

“ከአሜን ባሻገር”፥ ባንሻገርስ!?




ከእግዜር እያፋቱ
ለዝሙት አዲስ በር እየከፋፈቱ
ዘረኝነት “ጠልቶ”
በሰው ልብ አዲስ ዘር ለማብቀል ኮትኩቶ

Monday 21 March 2016

እስኪ አምጡ ዝምታ!!!


የሰባ መሥዋዕት
ለቁጥር ‘ሚታክት
ያማረ እህል ቁርባን
በኵሩ መልከ መልካም ...

Saturday 19 March 2016

ባለፉት ሦስት አመታት ...

   

     ባለፉት ሦስት ዓመታት ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ ከእግዚአብሔር ቃል አንጻር ወቅታዊ ጽሁፎችን ስብከቶችን ትምህርቶችን ግጥሞችን ...ከተወሰኑት ጊዜያት መቋረጥ በቀር በተከታታይ ለማቅረብ ጥሬያለሁ፡፡ በእነዚህ ሦስት ዓመታት ውስጥ ለእግዚአብሔርና ለቃሉ እንጂ ወደማንም እንዳላደላሁ ሕሊናዬ ይመሰክርልኛል፡፡ ከእግዚአብሔር በቀር ማንንም ደስ ለማሰኘትም ሆነ በከንቱ ለመውቀስ እንዳልተጋሁም እንዲሁ፡፡

Tuesday 15 March 2016

ወርሰን ያንተን ደስታ

                                           
                                                 Please raed in PDF

ያኔ …
ሥላሴ በስድስተኛው ቀን
ፈጥሮ ፤ ፈጽሞ አረፈ እረፍትን ፤

Thursday 10 March 2016

ክርስቲያን ያልሆኑት ኦርቶክሳውያን ወይስ ምህረተ አብ?! (የመጨረሻ ክፍል)

የኦርቶዶክስ የት መጣ
    “ኦርቶዶክስ” የሚለው ስም ስያሜ ዋና መሠረቱ ትምህርተ ክርስትና [1] ነው፡፡ ቅድመ ኒቂያና ድኅረ ኒቂያ (pre Nicene) ማለትም፥ ከ300-325 ዓ.ም ገደማ እና ድኅረ ኒቂያ (post Nicene) ከሌሎቹ መናፍቃን ይልቅ አርዮስ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ላይ ጠንካራ የክህደት ትምህርቱን አሰማ፡፡ በ325 ዓ.ም ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ የቤተ ክርስቲያን አባቶች አርዮስን [2] በክህደቱ ባወገዙበት ወቅት አርዮስን ያወገዙበትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርታቸውን “ኦርቶዶክስ” ብለው ሰየሙት፡፡

Saturday 5 March 2016

ጌታ ኢየሱስ ከሰማያት የወረደው አምላክነትን ሊሾም አይደለም!

   Please read in PDF

  የዓቢይ ጾም ፊተኛው ሳምንት መጠርያ ዘወረደ ይባላል፡፡ ይህም ክርስቶስ ኢየሱስ ከሰማየ ሰማያት የሰው ልጆችን ለማዳን በእርሱ ፤ በአባቱና በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ መምጣቱን ቤተ ክርስቲያን በአምልኮዋ ትዘክረዋለች፡፡ እርሱ የወረደው እኛን ለማዳን ነው፡፡ ምክንያቱም ከሰው ወገን ወይም ከፍጡር ወገን ማንም እኛን ማዳን ስላልተቻለው አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ በገዛ ፈቃዱ ሊያድነን መጣ፡፡  ዛሬ ይህ እኛን ለማዳን ከሰማያት የወረደው ጌታ፥ ስለመውረዱእየተነገሩ ያሉ ብዙ ክህደቶች አሉ፡፡
     ከግኖስቲካውያን እስከ ዶሴቲክስ ፤ ከአርዮስ እስከ ንስጥሮስ ፤ ከሞርሞናውያን እስከ ኦንሊ ጂሰሶች ፤ ከይሖዋ የመንግሥት አዳራሽ ምስክሮች እስከ ዘመነኞቹ የአዲሱ ትውልድ እንቅስቃሴ (New age Movement) ፤ የእምነት እንቅስቃሴ (Faith Movement) እና Biblical Unitarian እስከሚባሉት ድረስ ለዘመናት መናፍቃን መልካቸውን እየቀያየሩ በጌታ ኢየሱስ ላይ እጅግ አጸያፊ ክህደቶችን አውርደዋል ፤ አሁንም አላባሩም፡፡ ከሚያደርሱትና እያደረሱ ካሉት ጥፋት አንጻር ግን ቤተ ክርስቲያን ሥራዋን በአግባቡ እየተወጣች ነው ለማት አያስደፍርም፡፡