Monday 11 March 2013

ኃጢአት ያንቺ ዕድሜ


Please read in PDF


አይዘከር ግብርሽ
አይታወስ ስምሽ
ውሃ እያራሰ እንዲያው ያለቅልቅሽ
አይቁምልሽ ሐውልት መታሰቢያ ቅጥር
 አፀድሽ ይነቀል
          መሠዊያሽ ይቃጠል


አያጣፍጥ ጨውሽ
           አያስማ ሙቀትሽ፡፡
መሠረትሽ ይናድ የቤትሽ ምሰሶ
እኔ ግን ልነሣ በንስሐ ልቅሶ
የቆረጥኩት መልካም ይለምልም አብዝቶ
እንደ ወይን ፍሬ ተውቦ ጎምርቶ
ልቁም ሙሉ ሆኜ በልቤ ታድሼ
በማይጥለኝ ጌታ በጸጋው ጎልምሼ
ያንቺ ቤት ግን ዳግም:-
በጅማሬ ይቁም አያግኝ ፍጻሜ
ቀጥ ይበል አይርዘም
ኃጢአት ያንቺ ዕድሜ፡፡

3 comments: