Monday 31 July 2023

ቅልወጣ የማይርቀው “ሃይማኖታችን”ና ፖለቲካ

 Please read in PDF

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሐዳስያን ከምትወቀስባቸው “ወቀሳዎች” አንዱ፣ ከፖለቲካው ወይም ከቤተ መንግሥት ጋር የነበራት ግንኙነት ነው። ላለፉት 1600 ዓመታት ያህል ቤተ ክርስቲያኒቱና ቤተ መንግሥቱ ሊነጣጠሉ እስከማይችሉ በሚመስል መንገድ አንድ ላይ ነበሩ። ይህ ሊስተባበል የማይችል ሐቅ ነው፤ በረጅም ዘመን ታሪኳ ሳትከፋፈልና ወንጌልና “በመስበክ” መቆየትዋ እየደነቀን፣ ለብዙዎቻችን እግዚአብሔርን ለማክበርም፤ ብሎም ብዙ ዕድፏን እያየን ደግሞ አንገት ለመድፋት፤ ለመተከዝ የተገደድንበት ብዙ ጊዜም አለ!

Tuesday 25 July 2023

ከእሳት የሚያድን፤ በእሳት የሚጠብቅም አምላክ አለን!

 Please read in PDf

እሳት በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ዓይነት መንገድ ተገልጦአል። ለኹላችንም ግልጥ የኾነው እሳት፣ ሰዎች ለመሥዋዕት አገልግሎት (ዘሌ. 6፥13፤ 1ነገ. 18፥38፤ 2ዜና. 7፥1-3)፣ ለምግብ ማብሰያ (ዮሐ. 21፥9)፣ ለብረት ማቅለጫና (ዘጸ. 32፥24) ለሌሎችም አገልግሎት የሚውል ነው። ይህን እሳት ዓላውያን ነገሥታት አንዳንድ ጊዜ በእነርሱ ላይ ለተነሣሱባቸው ሰዎች፣ የፍርድ መቀጣጫ አድርገው ይጠቀማሉ። ንጉሥ ናቡከደነጾር፣ ለእርሱ ምስል ወይም ጣዖት አልሰግድም ያሉትን ሦስቱን ወጣቶች፣ “… ያስሩ ዘንድ፥ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ። (ዳን. 3፥20)።

ነገር ግን ሦስቱን ወጣቶች የእስራኤል አምላክ ያህዌ ኤሎሂም ታደጋቸው፤ አዳናቸውም፤ ከእስራኤል አምላክ ከቅዱሱ እግዚአብሔርም በቀር ሌላ የሚያድን አምላክ እንደሌለ፣ ያ ዓላዊ ንጉሥ እንዲህ ሲል ምስክርነቱን ሰጠ፤ እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለም (ዳን. 3፥29)፤ በእርግጥም ከእሳት የሚያድን ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ እንደሌለና በእሳትም ስለሚያከናውናቸው ተግባራት ቅዱሳት መጻሕፍት በምልአት ይመሰክራሉ፤



Thursday 20 July 2023

የ“አነቃቂዎቹ” ድንዛዜ!

Please read in PDF

ዶክተር ወዳጄነህ መሐረነ “አነቃቂ” ንግግር ያቀርባሉ ከሚባሉ ሰዎች መካከል አንዱ ነው። በአነቃቂዎች ዙሪያ በተደጋጋሚ ለመጻፍ ዐስብና ብዙዎች መልስ በስላቅ፣ በቅኔ፣ በድራማ፣ በ“አሽሙር”፣ በስዕላዊ መንገድ፣ በወግ … መልስ ስለ ሰጡበት ብዙም መናገር አልፈለግኹም። በእርግጥ “አነቃቂ” እንደ ኾኑ የሚያስቡ አካላት፣ እጅግ በሚያደንቅ መልኩ የሕይወት ምሳሌነት የሌላቸው (ኹሉም በሚያስብል መልክ ትዳራቸው በፍቺ የተጠናቀቀ፣ ጾታዊ ግንኙነታቸው አኹንም እንኳ ጤናማ ያልኾነ)፣ ነገረ መለኮታዊ ዕሳቤያቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ የማይገጥም፣ ከነባራዊው እውነትና ከማኅበረ ሰቡ መልካም እሴቶች ጋር ፈጽሞ የማይጣጣም፣ ግለኝነትን የሚያበረታታና መንፈሳዊና ማኅበረ ሰባዊ አንድነትን የሚንድ … አመለካከቶችን በውስጡ ያጨቀ ነው።

Sunday 16 July 2023

መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፳፬)

 Please read in PDF

ለባለፉት ጥቂት ወራት ያረጋል አበጋዝ የተባለ ሰው በጻፈውና “መድሎተ ጽድቅ” በተባለው መጽሐፉ ላይ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሾችን እየሰጠን መኾናችን ይታወሳል፤ ዛሬም የዚያን ተከታዩን ክፍል እናቀርባለን። በባለፉት ጊዜያት፣ የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን በተደጋጋሚ የሚቃወምበትንና የሚጥስበትን መንገድ እያሳየን መቆየታችን ይታወሳል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ተቀባይ ቢመስልም፣ ነገር ግን በሌላ ትምህርት ደግሞ ያንኑ የተቀበለውን እውነት መልሶ ሲክድና በሌላ ትምህርት ሲቃወም እንመለከተዋለን፤ ለምሳሌም፦