Wednesday 27 February 2019

Tuesday 19 February 2019

“ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ” (ማቴ. 12፥41)

     Please read in PDF
    የአይሁድ መሪዎችና ሕዝቡም የክርስቶስን መሲሕነት ለማረጋገጥ ምልክትን [ተአምራትን] በተደጋጋሚ ጠይቀውታል። የጠየቁት መሲሕነቱን ለማመንና እርሱን ለመከተል አይደለም፣ ይልቁን መሲሕነቱን ለማወቅ የመጡበት መንገድ ጠማማና ያለማመን መንገድ ነው። በዚህ በማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 12 ላይ ብቻ እንኳ ሊፈታተኑ በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበዋል፤ (ቁ. 2፤ 14፤ 24፤ 38)፤ ፍጹምና ጻድቅ የኾነውን መሲሕ ሊፈትኑት እርሱ የሚያሳየውን ምልክት በተደጋጋሚ ጠይቀዋል። የፈለጉት ተአምራት በጉልህ የሚታይና አሁን በሰማያት ላይ የሚደረገውን ነበር፤ (ሉቃ. 11፥16)።
ምልክቱን የፈለጉት ራሳቸው እንደሚሹት ነው እንጂ ሊታነጹበትና እግዚአብሔርን የተአምራት ድንቅ አምላክ ብለው ለማመስገንና ለማምለክ አይደለም፤ ይልቁን ሊነቅፉት፣ ሊፈትኑት፣ በእርሱም ላይ ሊሳለቁ ነበር። በቀጥታ ንግግራቸውም ኢየሱስ ተአምራትን ያደርግ የነበረው በሰይጣን ኃይል እንደ ኾነ በግልጥ በመናገር ንቀታቸውን አሳይተዋል። በዚህ ንግግራቸው ይህን ብቻ የሚያደርጉ አይደሉም። እግዚአብሔር የዘለላም አምላክ መኾኑን የሚቃወሙ ናቸው። ምክንያቱም እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን የሠራቸው ሥራዎቹ፣ ተአምራቶቹ፣ ምልክቶቹ የሚያረጁና የሚያልፉ አይደሉምና። ይህን ባለማስተዋል በፍጹም ስተዋል።

ኢትዮጲያ በግልጥ ኢየሱስን ለመከተል ከአስቸጋሪ አገራት መካከል ስትመደብ!

Please read in PDF

 ምድራችን ኢትዮጵያ ኢየሱስን በግልጥ ለመከተል አስቸጋሪ ከኾኑት ከዓለማችን አገራት 29ኛ ደረጃ ላይ መገኘቷን ያውቃሉ? አዎን ምድራችን ብዙ ሃይማኖተኛ ሕዝብ ቢኖራትም ነገር ግን ለክርስቶስ ኢየሱስና ለኢየሱስ አማኞች ምቹ ምድር አይደለችም፡፡ ምድራችን ኢየሱሳውያንን፣ በኢየሱስ የሚያምኑትንና ስሙን ወደው የሚጠሩትን ታሳድዳለች፣ ታንገላታለች፣ የመንቀሳቀስ ነጻነታቸውን ትነፍጋለች፣ ትደበድባለች፣ ንብረት የማፍራት መብታቸውን ትነፍጋለች፣ ኢየሱሳውያን[የኢየሱስ ትውልዶች] መከራቸው ዛሬም አለ፡፡

Sunday 17 February 2019

አርባ ምንጭና ተሰሎንቄአዊ ልቧ

በኹለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው፣ ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ ወንጌል በመመስከር ካለፉባቸው ከተሞች አንዷ ተሰሎንቄ ናት፤በአንፊጶልና በአጶሎንያም ካለፉ በኋላ ወደ ተሰሎንቄ መጡ፥ በዚያም የአይሁድ ምኵራብ ነበረ።” (ሐዋ. 171) እንዲል፣ ወደ ተሰሎንቄ እንደ ገቡ ያደረጉት እንደ ልማዳቸው ከቅዱሳት መጻሕፍት እየጠቀሱ ወንጌልን ማስተማር ነበር። የቅዱስ ጳውሎስና ሲላስም የምስክርነታቸው ማዕከልይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነውየሚል ነው፤ ምክንያቱምክርስቶስ መከራ እንዲቀበልና ከሙታን እንዲነሣ ይገባው ነበርና

Monday 11 February 2019

ቤተ ክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (የመጨረሻ ክፍል)


1.10.    የዘፋኞችንና የአለማውያንን ዝናና ዕውቅና “መቀላወጥ”
      ቤተ ክርስቲያን ከአስተማሪዋ መንፈስ ቅዱስ የተማረችው አንድ ትልቅ እውነት “ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞትን በመካድ … ራስዋን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን መኖርን” ነው (ቲቶ 2፥12-14)።  “እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ እንጂ፥ በእኛ መልካም ሥነ ምግባር አለመዳናችንንም አውቀን” (ቲቶ 3፥5) መዳናችንን በመልካም ሥራ መገለጽ እንዳለበት ጸጋን አደላዳዩ መንፈስ ቅዱስ ያስተምረናል። ምክንያቱም ትክክለኛ የኾነ ሥነ ምግባር ምንጩ ትክክለኛ ትምህርት ነውና።

Tuesday 5 February 2019

ዘመነኛ “አገልጋዮችን” ሳስብ ትዝ የሚለኝ እንዲህ ነው!


  ጌታ አትረፍርፎ ባርኮኛል፣ ዲታና ቱጃር አድርጐ¡ እንዴ ጌታ ቢባርከኝ አይደል እንዴ የ10 ሚሊየን ብር መኪና ለራሴ፣ የ12 ሚሊየን ብር መኪና ለባለቤቴ መግዛቴ?¡ ጌታማ ልዩነት ያደርጋል፣ እንኳን በማያምኑትና በእኔ፣ በሚያምኑትና በእኔ መካከል ራሱ ልዩነት ያደርጋል፣ አዎን ያደርጋል፣ ስለሚያደርግም ነው፣ የ200 ሚሊየን ብር መኖሪያ ቤት የሰጠኝ፤ ደግሞ ባርኮቱ እጅግ በጣም ስለተትረፈረፈልኝ፣ ከሰሞኑ ደግሞ የ600 ሚሊዮን ብር ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላሠራ ነው፤ ገና ደግሞ በእስቴዲየም ደረጃ የወንጌል ማገልገያ አዳራሽ እናሠራለን፤ ለወንጌልማ ሰማይ ጠቀስ ሕንጻ ሊገነባለት ይገባል¡¡¡  ለምን ብለን በየመንደሩ፣ ለምን ብለን በየቀዬው፣ ለምን በየገበያው፣ ለምን በየወንዛ ወንዙ እየሄድን እንደ ኢየሱስና ጳውሎስ እንደ ቀደሙት ደቀ መዛሙርት ለምን “ሳይመቸን እየተንዘላዘልን” እንሰብካለን?¡ ኢየሱስ ራሱ፣ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ …” ማለቱ ትክክል አይደለም፤ እርሱ ዞሮ ያልሰበሰበውን ሕዝብ እኮ እኛ ይኸው ተቀምጠን በቀላሉ ሰብስበን አይደለም ወይ? የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ባይኾኑም የእኛ ምርጥ ደቀ መዛሙርት ናቸውና ደስ ይለናል?