Sunday 5 May 2024

በእውነት አገኘችው!

 

በድኑን በሽቱ ልትቀባው ሽታ

በብርቱ ስትፈልግ ተርባ ተጠምታ

አጽንታ በትጋት በድቅድቅ ጨለማ

የሴትነት ፍርሃት ኹሉን ተቋቁማ ...

ባልጠና ማስተዋል በድካም ብትኾንም

ልክ እንደ ተራ ሰው ፍለጋ ብትመጣም

ጌታ ግን አለፈ ድካሟን ረዳና

"ማርያም" ብሎ ጠራት በሚያጽናና ቃና!

የመጊዶል ማርያም ...!

ሳትበገር ቆማ ሳትረታ ጸንታ

በእውነት አገኘችው የትንሣኤን ጌታ!

No comments:

Post a Comment