Wednesday 20 November 2019

ንቀት (ክፍል ፫)

Please read in PDF
ጌታ ኢየሱስ ማንንም አልናቀም!
  “… በተስፋ የተጠበቀው መሲሕ ሌላ ዐይነት ክብር፣ ማለትም የትሕትናን ክብር ለብሶ ነበር በመካከላቸው የተገኘው። አባ ኔቪል ፈጊስ የተባሉ ካህን እንደ ተናገሩት፣ ‘እግዚአብሔር ታላቅ ነው የሚለው የሙስሊሞች እወጃ እውነትነቱ ጉልህ በመሆኑ ያለልዕለ ተፈጥሮአዊ ህልው እገዛ ሰው ሊረዳው ይችላል። እግዚአብሔር ትንሽ ነው የሚለውን ግን ኢየሱስ ለሰው ልጆች ያስተማራቸው እውነት ነው’ …”[1]
   ጌታ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበት መንገድ እጅግ አስደናቂና ልብን በመደነቅ የሚመላ ነው። የመጣበት መንገዱና ዓላማው ለብዙዎች የሚጥምና የሚጣፍጥ አይደለም፤ በአዲስ ኪዳንም አገላለጥ ጠባብ መንገድ፣ የግመል መርፌ ቀዳዳ ታህል፣ እስከ መስቀል ሞት መታዘዝ፣ የራስ ክብርንና መብትን መተው፣ ባልንጀራን እንደ ራስ መውደድ … በሚል ውብ ሕይወትና ዝንባሌዎች የተመላ ነው።

Wednesday 13 November 2019

ንቀት (ክፍል ፪)

Please read in PDF
እግዚአብሔር አይንቅም!
   እግዚአብሔር አምላክ በክብር የተከበበና በፍቅር የተትረፈረፈ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር ፍጥረትንም ሲፈጥረው በድንቅና በግሩም ክብር ነው፤ “ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።” (መዝ. 139፥14) እንዲል፣ ሰው በግሩም፤ በድንቅ አድናቆት ተመልቶ የተፈጠረ ነው። መዝሙረኛው እንዲህ ሲል የፈጠርከውን ሰው የምታውቀው አንተ ነህ፤ እኔንም የፈጠርኸኝ አንተ ነህና በሚገባ ታውቀኛለህ፤ ምክንያቱም በእናቴ ማኅፀን ያበጃጀኸኝና በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ ንቁ ኾነህ የተንከባከብኸኝ አንተ ነህ እያለ ነው፣ ያህዌ ኤሎሂምን!

Friday 8 November 2019

አቤንኤዘር

Please read in PDF

አቤንኤዘር አቤንኤዘር መዝሙራችን
ድል አይተናል ተዋግቶልን ረዳታችን
ቅኔ አምጡ ተንጓደዱ በምስጋና
ከሳሽ ወድቋል ጌታ ቀኙን ልኳልና

Monday 4 November 2019

ንቀት (ክፍል ፩)

Please read in PDF
መግቢያ

    ቅዱስ ጳውሎስ ዘርዝሮ ካልጨረሳቸው(ገላ. 5፥19-21) እና ተዘርዝረው ከማያልቁት የሥጋ ሥራዎች አንዱ ንቀት ወይም ሰዎችን መናቅ ነው፤ የሥጋ ሥራዎችን እንዘርዝራቸው ብንል ዳርቻው ኹሉ እንደማይበቃቸው እናውቃለን፤ ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀሉ ኃይል እኒህንና ሌሎችንም ኃይላት ደካማ በሚመስል መንገድ ሰብሮና በመስቀሉ ጠርቆ አስወግዶአቸዋል። አለቅነት፣ ሥልጣን፣ ኃይል፣ ጌትነት ኹሉ በክርስቶስ ጌትነትና ኃይል ተሽሮአል፤ (ኤፌ. 1፥20-21፤ 3፥10፤ ፊልጵ. 2፥9)። ክርስቶስ በመስቀል ሞቱ የተወደደና ቅዱስ ሕይወት እንኖር ዘንድ በደሙ ፉጨት ጠርቶናል።