Thursday 20 May 2021

የእውነት ቃል አገልግሎትና የእምነት እንቅስቃሴ ተመሳሳይነት!

 Please read in PDF

የእውነት ቃል አገልግሎት፣ የእምነት እንቅስቃሴ አጋፋሪ ትምህርት ነው። የእምነት እንቅስቃሴ ትምህርቶቹ ኹሉ ሰውንና ራስን ወደ ማላቅ፤ ሰውን አምላክና አንዳች ልዩ ኃይል በውስጡ እንዳለ የሚያሞኙ፣ የሚያጃጅሉ፣ በምኞት የሚያስጎመጁና የሚያነኾልሉ “የከንቱ ከንቱ፤ ከንቱ ከንቱ ስብከቶችና ትምህርቶችን” የታጀለ አስተምህሮ ነው። ትምህርቶቻቸው ማዕከሉ ክርስቶስ መዳረሻውና ፍጻሜው የእግዚአብሔር መንግሥት መስፋት አይደለም።



Wednesday 19 May 2021

ጌታ ኢየሱስ ነቢይም ነው!

 Please read in PDF

ሊቀ ነቢያት ሙሴ እስራኤልን በተናገረው የስንብት ንግግሩ፥ “አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል እርሱንም ታደምጣለህ” (ዘዳግ. 18፥16) በማለት፥ ለጊዜው ከእርሱ በኋላ ለሚነሱ ለሌሎች ነቢያት ሲናገር በፍጻሜው ግን በትንቢት መልክ ስለሚመጣው መሲሕና ትንቢቱ በእርሱም የተፈጸመ መኾኑን እናያለን። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ አምስት ሺህ ወንዶችን ባሳመነበት (ሐዋ. 4፥4) የኢየሩሳሌም ስብከቱ በጌታ ኢየሱስን ትንቢቱ በትክክል መፈጸሙን ጠቅሶ አብራርቶታል።

Saturday 15 May 2021

መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፰)

 Please read in PDF

 ካለፈው የቀጠለ …

 እምነት፦ ሰው፣ በእግዚአብሔር ላይ ያለውን መደገፍ ከሚገልጥበት መንገድ አንዱና ተቀዳሚው እምነት ነው። እግዚአብሔር ለዘላለም እርሱም፤ ቃሉም ታማኝ ነው (2ጢሞ. 2፥13፤ ቲቶ 3፥8)። አማኝ እግዚአብሔር በተናገረው ቃሎቹ ላይ ፍጹም መደገፉ እርሱ እምነት ነው። እኛ በእግዚአብሔር ላይ ጥገኞች ነን፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር የፍጥረቱ አካል አይደለም፤ ይልቅ ፍጥረቱን ብቻውን ፈጥሮአልና እርሱ ከፍጥረቱ እጅግ የተለየና ምጡቅ ነው። ፍጥረት በእርሱ ይደገፋል፣ የእርሱን መግቦት ይጠባበቃል፤ እግዚአብሔር ግን በፍጥረቱ ፈጽሞ አይደገፍም።


Wednesday 12 May 2021

ከኦርቶዶክስ ውጭ ያለ መጤ ነው?

Please read in PDF

ከንቱ ትምክህት!

ማኅበረ ቅዱሳንና አንዳንድ የኦርቶዶክስ ሰባክያን፣ ስለ ክርስትና ሲያወሩ፣ ክርስትናን ራሳቸው ጠፍጥፈው የሠሩትና ለዓለም የናኙት ይመስላሉ። እነርሱ በግብዝነት የሚመኩትን ያህል ክርስትና የሰበኩት፣ የመንግሥቱን ወንጌል ለዓለሙ የናኙት የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት እንኳ እንደ እነርሱ ፈጽሞ አይመኩም፤ አይገበዙምም። እጅግ በጣም የሚያስደንቀው ነገር፣ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ አባ ሰላማ፣ ኢትዮጵያዊ  እንዳልኾነ የሚያውቁ እጅግ ጥቂቶች ናቸው። እንዲያውም ከታወቁት የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፍት አንዱ፣ ቅዱስ ማቴዎስ የተገደለው በኢትዮጵያ ምድር እንደ ኾነ ይነግረናል። ክርስትና አገር በቀል ቢኾን፣ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ምድር ባልተገደለ!


Saturday 8 May 2021

ግንቦት ልደታና የሕይወት ትዝታዬ!

 Please read in PDF

የዛሬ አሥራ ሰባት ዓመት ገደማ፣ ነፍሴ ከግንቦት አንድ አምላኪያን እጅ ያመለጠችበት ቀን ነው። በዚያን ቀን፣ በአርሲ ነጌሌ ሶጊዶ ማርያም ቤተ ክርስቲያን በዓለ ንግሡ ላይ ላገለግል ተጠርቼ በዚያ ነበርኩ። “የተሸሸገ ጣዖት” በሚል ርዕስ፣ የያዕቆብ ሚስት ራሔል ጣዖትን መሸሸጓንና በዚህም የደረሰባትን በማንሳት አንስቼ አገለገልሁ፤ እኛም ይህን ማድረግ እንደሌለብን ብርቱ ማስጠንቀቂያ በማኖር ጭምር። ነገር ግን በዚያን ቀን ሳስተምር፣ ከታቦቱ ጎን ትምህርቴን ቆሞ ይሰማ የነበረ፣ የገጠር ከተማይቱ ጠንቋይ ደም በሰረበ ዓይኖቹ ይመለከተኝ ኖሯል።

Thursday 6 May 2021

ይድረስ እንደ እኔ ለነበራችሁ ኹሉ!

Please read in PDF

እኔ!

በአጭር ቃል፣ እኔ ትላንትና የክርስቶስን መካከለኝነት ነቅፌ የማርያምን መካከለኝነት አስተምር ነበር፤ የክርስቶስን መካከለኝነት ያስተምሩና ይሰብኩ የነበሩትን ነቅፍ፣ ሰድብ፣ በብርቱ ቃል ተች፣ አዋርድ ነበር። እኔ በማደርገው ንግግርና ድርጊት ሰዎች እስኪሸማቀቁ ድረስ ለብዙዎች የመሰናከልና የመውደቅ ምክንያት ነበርኩ። ማርያምን በዝማሬ አምልኬአለሁ፤ ወደ እርሷ ጸልይ፤ በስሟም እማጠን፣ አማልጂኝ ብዬም እለምናት ነበር። ለስእሏ እሰግድ፣ ለስሟም ስዕለት አስገባ፣ በመላእክት፣ ቅዱሳን ተብለው በሚጠሩ ፍጡራን ሰዎችና ቊሳት ኹሉ ስም አምልኮ እፈጽም፣ እግዚአብሔር ሩቅ እንደ ነበር፣ መዳንን በግል ጥረት ማግኘት እንደሚቻል ለዚህም ገዳም ለገዳም እንከራተትም … ነበር።

Saturday 1 May 2021

የሕማም ሰው

Please read in PDF

ነቢዩ ኢሳይያስ ስቁዩንና መከራ ተቀባዩን መሲሕ፣ “ደዌን የሚያውቅ የሕማም ሰው” ብሎ ይጠራዋል (ኢሳ. 53፥3)። መሲሑ መከራን የማይቀበልና ሕመም ተጠያፊ አይደለም፤ ይልቁን ሐዋርያው ጳውሎስ፣ “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ መኾኑን” (ፊልጵ. 2፥8) በግልጥ ተናገረ። መሲሑ ለመታመም የፈቀደ፣ ለመድቀቅ የወደደ፣ ለመዋረድ ክብሩንና ጥቅሙን ኹሉ በፈቃዱ የተወ፣ እግዚአብሔር ነፍሱ የተደሰተችበት ጻድቅ ባሪያ ነው (ኢሳ. 53፥11)።