Saturday 27 April 2013

ሆሳዕና ለርሱ

Please read in PDF

ከብርሃናት ዙፋን የአህያ ጀርባ
ከወርቅ ምንጣፍ ይልቅ መናኛ ዘንባባ
ከሊቃውንት ይልቅ የህፃናት አፍላ
ወዶ የመረጠ እንደ ማር ወለላ
ዝቅ ዝቅ ብሎ ውርንጫይቱን ሽቶ
ባማረ ሰገነት መቀመጥን ትቶ
ሠላማዊ ነቢይ የሰላም አለቃ
በሚጠቡ ህፃናት ለመመስገን በቃ፡፡

የሌሊቱ ደቀመዝሙር

Please read in PDf

አካሉ ቢተኛም ልቡ ግን በንቃት
በቀንና ማታ ሳያውቅ መሰልቸት
መልካሙን በመግፋት ሞት እንዳያገኘው 

Thursday 18 April 2013

ማየቴ አያምንም


Please read in PDF


ከመቃብር ፤ ከተማሰው ጉድጓድ ማዶ
ከሚታየው ፤ ከዚህ ዓለም ትንሽ ጎጆ
ከጨለማ ወዲያ ከሞትም ባሻገር
ተስፋዬ እዛ ነው ከሰማያት አገር፡፡
ተስፈኛ አይደለሁም ከፍጡር እንጀራ
ከትዳር ከሀብቱ ከስልጣኑ ተራ

Sunday 14 April 2013

ምንድን ነው መክሊት ቀበራ?


 Please read in PDF

ተሹመህ በብዙ ጸጋ
እንድትጠቅም እንድትረባ
አሽተህ እንድታፈራ
መንጭተህ እንድታረካ
በቃሉ መነጽርነት
አቅርበህ የሩቅ ሚስጢራት
ወደ ህይወት የእውነት  መዲና
ተቃንተህ እንድታቀና

Friday 12 April 2013

እንገባ ዘንድ አለን


Please read in PDF

ምድሪቱ ያልተነካች የማርና ወተት
በረከቷ ብዙ የሚያጠግብ ሕብስት
ተስፋው፥ ከግንብ ይልቅ የጸና

Tuesday 9 April 2013

መንፈሱና ሙሽራይቱ


Please read in PDF


ደግ ሰው አልቆ ጉብዝናም ሠሎ
መተማመን ክብርዋ ጎድሎ
ፍቅር ቀዝቅዛ
ጽድቅ አዘቅዝቃ

Thursday 4 April 2013

አለቀሰ አሉኝ


Please read in PDF


ነፍርቆ አለቀሰ አሉ ፣ሐበሻ ተነቅሎ ወጥቶ
አይኑን እያረጠበ ፣እንባ በእንባ ተራጭቶ
አነባ ደረቱን ደቅቶ ፣ተክዞ አመድ ነስንሶ
ማቅ ለብሶ የእዬዬ ሲቃ፣ የሐዘን ግድቡን ጥሶ
ከአልጋው ወረደ አሉ ፣ይህ ህዝቤ ከምንጣፍ ሊውል
ቤቱንም ትቶታል አሉ፣ ከድንኳን ሄዶ ለማደር
ጮኸ አሉ ባ'ደባባዩ፣ ልቅሶውን እያጋጋመ
ስንወድህ ስንናፍቅህ ፣መሪያችን የት ሄድክ? እያለ፡፡

Tuesday 2 April 2013

የኢየሱስ ጽድቁ


Please read in PDF


በአብ አንድ ልጁ
ያመኑት ተዋጁ
ሲዖል ድል መንሣትህ
ሞት የዜማ ዕቃህ
ወዴት አለ ዛሬ
ኃጢአት ያንቺ ፍሬ?