Friday 20 August 2021

ማርያም፤ ሰባት ጊዜ ሞታ ተነሣች?

Please read in PDF

በኦርቶዶክስና በካቶሊክ ስለ ማርያም ሞት፣ “ትንሣኤና ዕርገት” የማያልቁ አእላፍ ተረቶች አሉ፡፡ ምሳሌ፦ ነገረ ማርያም በግልጥ፣ የማርያምን ስም ትርጉም ሲያብራራ እንዲህ ይላል፣ ማርያም በገሃነም ያሉ ኀጢአተኞችን ባየች ጊዜ፣ “እርሷም እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እነዚህ ነፍሳት ዘለዓለም በገሃነመ እሳት ወርደው ሲቀሩስ እንኳን አንድ ጊዜ ፯ ጊዜ ልሙት ብላ ሙታለች ኋላም ለፍጥረቱ ኹሉ መጽደቂያ ሁና ተገኝታለችና ወኀብት(ስጥውት) አላት፡፡”[1] ማርያም ለኀጢአተኞቹ ራርታ ሰባት ጊዜ ልሙትላቸው ብላ ሰባት ጊዜ ሞታላቸዋለች! ከዚህም የተነሣ መጽደቂያቸው ኾናለች! መጽሐፍ ቅዱስ ግን፣ “አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥ እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤” (ሮሜ 3፥21-22) በማለት የምንጸድቀው በክርስቶስ ብቻ እንደ ኾነ ይነግረናል!

Thursday 19 August 2021

ዕረፉ[አድቡ]! (መዝ. 46፥10) - ክፍል ፪

Please read in PDF

አንፈራም

የሚሰማው፣ የሚታየው፣ የሚነገረው፣ ጠላት በብሩ የሚጎስመውና የሚያጓራው ማጓራቱ እጅግ ጠንካራና አስፈሪ ነው፤ ነገር ግን እኛ አንፈራም፤ የማንፈራበት ምክንያት የማንፈራ ኾነን አይደለም፤ ነገር ግን ፍርሃትንና የፍርሃትን ምንጭ የሚሽር አምላክ ስላለን እንጂ። የማንፈራበት ምክንያት፦

1.   የሰራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፦ ይህ ቃል በዝማሬው ወስጥ እንደ አዝማጅ ተደጋግሞ ተጠቅሶአል (ቊ. 7፡ 11)፤ እርሱ “አምላካችን”፣ የሰራዊት አምላክ”፣ የያዕቆብ አምላክ” ነው። እርሱ በመግቦቱ ለያዕቆብ ወይም ለእስራኤል የተለየ ፍቅር አለው፤ በእርሱ ታምነዋልና። ስለዚህም የእርሱ ከእነርሱ ጋር መኖር ለእነርሱ ክብርና ሞገስ፤ መወደድም እነጂ የፍርሃት ምልክት አይደለም። እርሱ ከእነርሱ ጋር ስለኾነም ለዘላለም መጠጊያና ኀይላቸው፣ በመከራቸው ኹሉ የቅርብ ረዳታቸው (ቊ. 1)፣ መጠጊያቸው (ቊ. 7)፣ ከለላቸው ነው።

Wednesday 18 August 2021

የደብረ ታቦሩ የስንፍና ጸሎት

 please Read in PDF

በአዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ፣ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቀረቡ አያሌ ጸሎቶችን እናነባለን። ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቀረቡ አንድ መቶ ሰማንያ ሦስት የሚጠጉ ጸሎቶች መካከል አንዱ ጸሎት፣ “መምህር ሆይ፥ በዚህ መኾን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ” (ማር. 9፥5) በማለት ቅዱስ ጴጥሮስ ያቀረበው ጸሎት ነው።

Sunday 15 August 2021

ዕረፉ[አድቡ]! (መዝ. 46፥10) - ክፍል ፩

Please read in PDF

መግቢያ

በዚህ ምዕራፍ፣ መዝሙረኛው የሚዘምረው መዝሙር፣ የቆሬ ልጆችን መዝሙር ነው። የቆሬ ልጆች ከቆሬ ወገን የኾኑ ሌዋዊ መዘምራን ናቸው። በንጉሥ ዳዊት የተሾሙና በዳዊትም ዘመን የቆሬ መዘምራን አለቃ ኤማን የተባለ ሰው ያገለግል የነበረ (1ዜና. 6፥31-47) ሲኾን፣ በቅዳሴ ሥርዓት እግዚአብሔርን በአንድነት ያገለግላሉ። በዳዊት መዝሙር ውስጥ፣ በቆሬ ልጆች ከተሰየሙት ሰባት[1] መዝሙሮች መካከል፣ አንደኛው ዝማሬ ይህ ዝማሬ ነው። ዝማሬው የጽዮን ዝማሬ ነው፣ ዝማሬውን የሚዘምሩትም ደናግላን በደናግል የዜማ ስልት ነው። መዝሙሩ የሚዘመረው በኅብረት፣ የመዘምራን አለቆችም እየመሩት ነው።

መዘምራኑ እየዘመሩ በሰልፍ ወደ ቤተ መቅደሱ ሲሄዱ፣ ደናግላኑ ከበሮ እየመቱ በማጀብ ይከተሉአቸዋል። እጅግ ውብና እግዚአብሔርን በሕዝብ ኹሉ ፊት ከፍ የሚያደርጉበት፣ በእርሱ መታመናቸውንም በአደባባይ የሚገልጡበት ዝማሬ ነው።

Saturday 7 August 2021

መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፲፫)

Please read in PDF

ሥራ

ካለፈው የቀጠለ …

ሰዎች ኹሉ ሊድኑ የተጠሩት በክርስቶስ የመስቀል ላይ ሥራ ብቻ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ግልጥና የማያወለዳ ትምህርቶቹን እንዲህ ያስተምራል፤

ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።” (ኤፌ. 2፥8-9)

ኹሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በኾነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።” (ሮሜ 3፥23-24)

እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፤” (ሮሜ 9፥30)

Friday 6 August 2021

የክርስቶስ ትንሣኤና የማርያም “ትንሳኤ”

 Please read in PDF

የኦርቶዶክስና የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት የማርያምን፣ “በሦስተኛው ቀን” ሳይኾን፣ በጥር ሞታ ነሐሴ “መነሣቷን” ከዶግማ ትምህርቶቻቸው አንዱ አድርገው ይቀበላሉ። ማርያምን “ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች”ና ፍጹም መካከለኛ አድርገው ለመቀበላቸውም ከሚያቀርቡት ማስረጃዎች አንዱ ይህን፣ “ከሞት ተነሥታለች” የሚለውን ትምህርት በዋቢነት በመጥቀስ ነው።

Thursday 5 August 2021

መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፲፪)

Please read in PDF

ካለፈው የቀጠለ …

ሥራ

የክርስትና ትምህርት ጤናማና መዳን የሚገኝበት ቃል ወይም ትምህርት ተብሎ ተነግሮአል (ሐዋ. 13፥26፤ 1ጢሞ. 6፥3፤ 2ጢሞ. 1፥13፤ 2ጢሞ. 3፥15)፤ ትምህርቱ ጤናማ ከኾነ የኑሮ ዘይቤና ጠባዩም ፍጹም ጤናማ መኾኑ አያጠራጥርም። ጤናማው ትምህርት ለእግዚአብሔር ክብር (Orthopraxy) በሚያመጣ እውነተኛ ሕይወት እንድንመላለስ ያደርገናል፤ ይህ ጤናማ ትምህርት ደግሞ ርትዕት ከኾነች እምነት (Orthodoxy) ጋር ፈጽሞ ሊነጣጠል የሚቻለው አይደለም። ሕይወት የሚቀዳውና የሚመነጨውም ከእውነተኛ ትምህርትና ከእውነተኛ ፍቅር (Orthopathy) ነውና።