Wednesday 30 October 2013

ይሟገትልኛል



መታጠቂያውን ታጥቆ
በስጦታ ብዛት አፉን ስሎ
ሊራገም ሊያራኩት
እዚያው ቀልጦ ሊያስቀር በምድረ በዳው ውስጥ
በምዋርት በአስማቱ
ጉዟቸውን ሊያደርግ ራዕይ አልባ ገልቱ
በለአም በባላቅ ተመክሮ ተዘክሮ
ማለዳ ተነስቷል ሊያስቀር አቅልጦ
እንደቅጠል ሊያረግፍ በእንጭጩ አምክኖ፡፡

Friday 25 October 2013

ጸሎት - "አቤቱ! ዋጋዬን ለባርያህ ግለጥልኝ "

                           ሺህ ……   1,000?
እልፍ ……   10,000?
አዕላፍ ……   100,000?
አዕላፋት ….    1,000,000?
ትዕልፊት ……    10,000,000?
ምዕልፊት  ….     100,000,000?
አዕላፈ አዕላፋት .…     100,000,000,000?
አዕላፈ ትዕልፊት ……      1,000,000,000,000?
ትዕልፊት አዕላፋት ……     10,000,000,000,000?
ምዕልፊት አዕላፋት ……      100,000,000,000,000?
.?
.?
.?

.?




Monday 21 October 2013

ለምን ከደካማው ጋር?



   የሰማዩን አለም ቅዱስና ፍጹም ያደረገው በዚያ ያሉ ሁሉም ለስሙና ለፈቃዱ ብቻ ስለሚገዙ ነው፡፡ በቀንና በሌሊት ሳያርፉ የሰማዩን ዓለም በምስጋና ችቦ የሚያፈኩት በፊታቸው የተገለጠች በጎ ፈቃዱን መቀደስ ምግባቸው ፣ማመስገን እረፍት ሆኖላቸው ነው፡፡በእርግጥም የእግዚአብሔር ፈቃዱ በሰማይ የተገለጠች ናት፡፡"ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነችእንዲል ታላቁ የህይወት መዝገብ፡፡(ማቴ.6÷10)
          ምድር ግን መልካምነትና በጎነት የበዛበት ይህን ፈቃዱን ፣ከማለዳ እስከማለዳ የተዘረጋ ቅዱስ ምሪቱን በኃጢአትዋ ከመካከልዋ አሰደደችው፡፡ስለዚህም በክፉዎችና በአስጨናቂዎች ተያዘች፡፡ህይወት የደገሰላትን ትልቁን ጌታ ትታ ሞት የሠረገላትን ተራ ባርያ ዲያብሎስን ሰምታ እንዲያስጨንቃት በላይዋ ሾመችው፡፡ስለዚህም ሲቻለው በግልጥ አልያ ደግሞ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ለክፉ ሐሳቡና ምኞቱ ያጠምደናል፡፡
       እኛ ክርስቲያኖች የጌታ ፈቃድ ብቻ የነገሰባትን ያቺን የጽዮን ተራራ ለመውረስ የምንጓዝ የዘወትር መንገደኞች ነን፡፡በተሰፈረ እድሜ የማይሰፈርና መጠኑና ይዘቱ ሊለካ የማይቻለውን በረከትና ህይወት ለመውረስ በቀንና ማታ የምንቃትት ነን፡፡ክፉ ገዢ ካለባት ከዚህች ምድር ወደሚያሰማራን ጌታ ለመጓዝ  የምንፋጠን ፣በተስፋ የምንናፍቅ ደጅም የምንጠና ነን፡፡
     ከሁሉ ይልቅ ደግሞ አንድ ትልቅ እውነት ተረድተናል፡፡ጠላታችን መናፍስት መሆናቸውንና ተግዳሮታቸውም ውስብስብ መሆኑን፡፡ደግሞ አለሙ ሁሉ በክፋት እንደተያዘም በሚገባ እናውቃለን፡፡ (1ዮሐ.5÷19) ስለዚህም ሰልፋችንና ውጊያችን ከአጋንንትና ከጨለማው አለም ገዢዎችና አለቆች ጋር ነው፡፡ ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከነዚህ በዓይን ከማይታዩ አዕላፍና ልምድ ካላቸው መናፍስት ጋር ነው፡፡(ኤፌ.6÷12)

Thursday 17 October 2013

እጅጉን ቀላል ናት

ከባድማ አይደለም የማይቻል ነገር
በፍቅር የታዘዝነው የጌታችን ወንጌል
በጣት 'ማይነካ አስቸጋሪና ጭንቅ
አይደለችም ወንጌል የአምላካችን መንገድ፡፡

         ከባዱ ሌላ ነው እጅግ አስጨናቂው

Monday 14 October 2013

የቱ ይበልጥብናል?


                  Please read in PDF
    
     ስለመብለጥ ሚዛናችንን ከቅዱስ ቃሉ አንጻር ካላየንና ብልጫነትን ከሌላ ነገር ተነስተን የምንመዝን ከሆነ በቅጽበት እድሜ ቃሉ ያልፈቀደውንና ፈጽሞ የማይወደውን ሚዛን እናበጃለን፡፡በዓለም ላይ ከሚገመተው ቁጥር በላይ የሆነው ሰው የሚዋደቅለትና አብዝቶ የሚመኘው ነገር ቢኖር ብልጫነትን ወይም መብለጥን ነው፡፡መቼም ለመልካምና እግዚአብሔር በሚወደው ነገር በቅዱስ ቅንአት ማደግና መጎልመስን ከዚህ እንደማናያይዘው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ምክንያቱም በክርስትና ትምህርት ባደግን፣በቤቱ በኖርን ቁጥር መብለጣችንን ሳይሆን በተወደደ ትህትና አለልክ ዝቅ ብለን ሁሉን ማገልገል እንዲገባን እንቆጥራለን እንጂ በአንዳች እንኳ የምንበልጥበት እንዳለን በልባችን ሐሳብ አይገባንም፡፡
      በእርግጥ ዛሬ ለምጽፋት "ትንስዬ" ጭብጤ ይህን ብዬ ተንደረደርኩ እንጂ ዋና ሐሳቤ ሌላ ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የመስዋዕትን ህግ ለሙሴ ሲሰጠው የተናገረውን ብዙ ጊዜ እንዲህ ሲገለጥ እወደዋለሁ "ለእንሰሳ ቀንዱ ካልከረከረ፣ጠጉሩ ካላረረ፣ጥፍሩ ካልዘረዘረ ከንጹህና ከተወደደው መካከል መርጦ" ፣ለእህል ቁርባኑ ደግሞ "ነቀዝ ካልበላው ፣ወፍ ካልጠረጠረው፣ እንክርዳድ ከሌለው ከሰባውና "ከመልካም ዱቄቱ" መባሉን አብዝቼ እወደዋለሁ፡፡በእርግጥ ቃሉም ይህን በሚገባ ይገልጠዋል፡፡
      እግዚአብሔር የብሉይ ኪዳኑን የሞትና የኩነኔ አገልግሎቱን እንኳ እንዴት ባለ ክብር እንደወደደ እዩ!! እንኪያስ በደሙ የከበረውና የመንፈስና የጽድቅ አገልግሎት የሆነው የምህረቱ ዘመን አገልግሎት እንዴት ባለክብር ይበልጥ ይሆን?እንደከበረው ምርጡና ውድ መስዋዕት ሆኖ የቀረበውን ትልቁና ዋናውን ነገር ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ብሎ ይገልጥልናል

Wednesday 9 October 2013

ስውር አገልጋዮች


Please read in PDF

 ርዕሰ መምህራን ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝብ ወደተሰበሰበበት ቦታ በመሔድ ያስተምር እንደነበር አራቱ ወንጌላውያን በህብረት ዘግበውታል፡፡ በለቅሶ ቤት ፣በገበያ ቦታ ፣በምኩራብና በመቅደስ ፣በባህር ዳርቻ፣በሠርግ ቤትና በሌሎች ስፍራዎች  ከሳሾች እስኪገረሙና እስኪደነቁ ፣ኃጥአን እስኪጽናኑና  እስኪመለሱ፣ ጻድቃን በልባቸው የመንፈስ ቅዱስ ሐሴትና ደስታ እስኪመላና እስኪበዛ ፣ትዕቢተኞች እስኪገሰጹና በሥራቸው እስኪያፍሩ … ያለከልካይ በግልጥ ያስተምር ነበር፡፡ዛሬ በሚያሳዝን መልኩ ለአብዛኛዎቹ አገልጋዮች እንደክስ ምክንያት የሚሆነው ከቤተ መቅደስ ውጪ የሚሰጡት አገልግሎት ነው፡፡በየቤቱ ተሰባስቦ ለሚደረገው የሥጋ ግብዣና ተራ ወሬ ከልካይ ሳይኖርበት ቃለ ወንጌል ለመነጋገርና ለመወያየት ሲሆን ግን ከሌላ ነገር ጋር በግድ ማያያዝ ጠማማነት እንጂ ሌላ ምንም ትርጉም አይሰጠውም፡፡ በእርግጥ አንዳንዶች ይህን አገልግሎት ለኃጢአት አውለውታል፤ ነገር ግን ከኀጢአተኞች ተነስቶ ጻድቁንም መንቀፍ በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ነው፡፡
        የአደባባይ አገልግሎት በነፍስ መወራረድን  የሚጠይቅ ፣የተገለጠ የምስክርነት ህይወትን ያዘለና ጥንቃቄና ማስተዋልን የሚሻ የአገልግሎት አንዱ ክፍል ነው፡፡ የአደባባይ አገልጋዮች የተራቆተ ገላ ናቸው፡፡ ሁለንተናቸው መሰወር የማይችል፡፡ የሰገነት መብራቶች ናቸው በሁሉም ዘንድ የሚታዩ፡፡ ጌታ ለዚህ አገልግሎት  አስራ ሁለት ደቀ መዛሙርት ሲመርጥ ሌሎች ሰባ ሁለት ረዳት ወንድሞችና ሰላሳ ስድስት ምርጥ እህቶችም አብረው ነበሩ፡፡