Sunday 29 March 2015

ኒቆዲሞስ - በክፉዎች መካከል የበቀለ መልካም ተክል

                                            
                                       Please read in PDF     
                                               
  


      በቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት፥ ቅዱስ ያሬድ እንደሰየመው አሰያየም ፥ያለንበት ሳምንት “ኒቆዲሞስ” ይባላል፤ ቅዱስ ያሬድ፥ ጌታ ኢየሱስ ነገረ ጥምቀትን ለኒቆዲሞስ እንዳስተማረው በማውሳት “ሆረ ኃቤሁ ዘስሙ ኒቆዲሞስ” ማለትም “ኒቆዲሞስ የሚባለውም ወደእርሱ ሄደ” ብሎ ርዕስ ሰይሞ ዘምሮታልና ፤ ቤተ ክርስቲያንም ይህን በማሰብ የጌታን ፆም አንዱን ሳምንት ሰይማ ፥ ጌታዋን ታመልክበታለች፡፡

Sunday 22 March 2015

ቸር አገልጋይ ማነው?











“በጎ ሥራ እየሠራ ጌታው የሚያገኘው ቸርና የታመነ አገልጋይ ማነው ? ባለው ሁሉ ላይ የሚሾመው ደግሞም  እግዚአብሔር ቸር ታማኝ አገልጋይ በጥቂቱ የታመንክ ወደጌታህ ደስታ ግባ የሚለው፡፡
(ቅዱስ ያሬድ)

      የስድስተኛውን የዓቢይ ጾም ስያሜ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ “ገብር ኄር” ትርጓሜውም “መልካም ባርያ” ሲለው ፤ የዕለቱን የመዝሙር ርዕስ ደግሞ “መኑ ውእቱ ገብር ኄር” ትርጓሜውም “ቸር አገልጋይ ማነው?” ብሎ ሰይሞታል ፤ የሚነበበው የወንጌል ክፍል ደግሞ  ማቴ.25፥14-31 ነው፡፡ በዚህ ዕለት በዋናነት “ስለቅን አገልጋዮችና ስለአገልግሎታቸው ትጋት “ገብር ኄር” እያለ ዋጋን የሚከፍል ፤ ሰነፍና ታካች አገልጋዮችን የሚቀጣም አምላክ እንዳለ በስፋት ይወሳል፡፡”

Thursday 19 March 2015

እኔ ላንተ ፈራሁ!


                                  Please read in PDF 


ትመስለኝ ነበረ፣ ለጨለማው ብርሃን ፣ ለጣዕም አልባው ጨው
ትመስለኝ ነበረ፣ ለብ ያለውን ሁሉ ፣ ግለህ ʻምታግለው
ትመስለኝ ነበረ፣ ብርሃንህ የበራ ከእንቅብ በላይ ሆኖ
ትመስለኝ ነበረ፣ ከጨለማ በላይ ከጋኑም ከፍ ብሎ

Sunday 15 March 2015

ጌታ ሆይ ፤ ና! (1ቆሮ.16፥22)


                                                 Please read in PDF
 

     
 የጥንት ክርስቲያኖች ጌታ ወደሰማያት ከማረጉ ምንም ሳይቆይ በመናፈቅ ለሁልጊዜ ይጮኹ የነበሩት የዳግመኛ መምጣቱን ነገር እንደሆነ ታላቁ መጽሐፍ አስረግጦ ይነግረናል፡፡ የአዲስ ኪዳን የትንቢት መጽሐፍ የሆነው የራዕይ መጽሐፍ የመጽሐፉን መግቢያ ሲጀምር በተደጋጋሚ “ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር… ” እንደሆነና ጌታ ባረገ ገና አንድ ምዕት ሳይሞላው “ዘመኑ ቀርቦአልና …” (ራዕ.1፥1 ፤ 3) በማለት ዘመኑ በደጅ የቀረበ መሆኑን በግልጥ ተናግሮ ሳያበቃ መጽሐፉን የዘጋው “ዘመኑ ቀርቦአልና … እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ … መንፈሱና ሙሽራይቱም ፦ ና ይላሉ ፦ የሚሰማም ፦ ና ይበል። … አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።“ (ራዕ.22፥10 ፤ 12 ፤ 17 ፤ 20) በማለት በተደጋጋመ ናፍቆታዊ መቃተት ነው፡፡

Friday 13 March 2015

“የምርጫ 97 ቀይ ስህተት እንዳይደገም ”ቤተክርስቲያን ድርሻዋን ብትወጣስ?!


                        Please read in PDF

   
     ቤተ ክርስቲያን አግባብነት ላላቸው የመንግሥት ሕጎችና ሥርዓት ሁሉ ልትገዛ እንደሚገባት ታላቁ መጽሐፍ “ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና … ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና … ” (ሮሜ.13፥1 ፤ 1ጴጥ.2፥13) በማለት ያስቀምጣል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ሆነ ቅዱስ ጴጥሮስ ይህንን ቃል የተናገሩት በዚያ ዘመን ምድርን ይገዙ ለነበሩት ሮማውያን ቄሳሮች ፥ ደቀ መዛሙርት እንዲገዙና እንዲታዘዙ በማሳሰብ ነው፡፡ ምክንያቱም ባዕለ ሥልጣናት “ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ (ከእግዚአብሔር) ተልከዋልና … በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፡፡” (1ጴጥ.2፥14-15)

Tuesday 10 March 2015

ሰው የለንም ጌታ!


                Please read in PDF

አንቀልባው አረጀ ደከመ አልጋችን
ፈውስህ ራቀንና ቃሬዛ በዛብን
ጎብጦ ሳይል ቀና ኑሮ እንዳከሰለው
ቀኑ እንደጨለመ ይሄዳል ሰው ይኸው፡፡ 

Sunday 8 March 2015

አመሰግናለሁ!





       እግዚአብሔር ጉልበትና ማስተዋል ሆኖኝ ፥ ይኸው ይህን አገልግሎት ከጀመርኩ ሁለት አመት ሞላኝ፡፡  የዘላለም መዳን ፈቃድን ሲጠይቅ (ማር.2፥5 ፤ ዮሐ.5፥6 ፤ ሐዋ.8፥37 ፤ 13፥46) አገልግሎት ደግሞ ጥሪና መለየትን ይሻል፡፡ (ዘፍጥ.12፥1-9 ፤ ሐዋ.9፥15) በየትኛውም ዘመን የተገለገለ የወንጌል አገልግሎት ያለመከራና ነቀፋ ተገልግሎ አያውቅም፡፡ የሐዋርያትን ዘመን ትተን ክርስትና በነጻነት ተገለገለ የተባለበትን ዘመን ብናይ እንኳ እነቅዱስ አትናቴዎስ ከአርባ አመታት በላይ በከባድ ስደትና ህመም ፤ በስም ማጥፋት ፣ እነቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በእስርና በስም ማጥፋት ክስ የወደዱትን ጌታ አገልግለውታል፡፡

Wednesday 4 March 2015

ይገባሃል

ይገባሃል!


                               Please read in PDF



“ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ። ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።”
(ራዕ.4፥10-11)



ይገባሃል ውዳሴ
ይገባሃል ቅዳሴ
ይገባሃል ዕልልታ
ይገባሃል ማኅተሙንም ልትፈታ
ይገባሃል የማያቋርጥ ግርግርታ፡፡