Thursday 29 July 2021

የመንፈስ ቅዱስን ደስታ መሞላት (ሐዋ. 13፥44-52)

ሰው እንዴት እግዚአብሔርን እየፈራ፣ ፍጹም እግዚአብሔርን ይቃወማል?! እግዚአብሔርን እየፈሩ እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ሰዎች፣ ተቃውሞአቸው ከምድር ኹሉ አደገኛውና ከባዱ ሲኾን ፤ በዚህ ኹሉ ውስጥ ግን የመንፈስ ቅዱስ ደስታ አለ! አሜን፡፡ 

Friday 16 July 2021

መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፲፩)

 Please read in PDF

ካለፈው የቀጠለ …

አንድን እውነት ማመን ብቻውን እምነት አይኾንም። ለምሳሌ፦ ሰዎች የእግዚአብሔርን መኖር ብቻ ቢያምኑ እርሱ እውነተኛ እምነት አይደለም። እውነተኛ እምነት ግን ከእግዚአብሔር የሚሰጠውን የዘላለም መዳን ለማግኘት ወይም ለመቀበል በክርስቶስ ኢየሱስ ፍጹም ማመንን የሚጠይቅ ነው። በልጁ የማያምን እምነቱ ርቱዕና ምሉዕ አይደለም። ስለዚህም የአዲስ ኪዳን እምነት በግልጥ ከዚህ በታች የሚከተሉትን እውነቶችን በውስጡ የያዘ ነው፤ እኒህም፦


መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፲)

Please read in PDF

“እምነት ብቻ”ን መጥላት!

ካለፈው የቀጠለ …

ስለ እውነተኛ መዳን ስንናገር፣ ምርጫ አልባ አድርገን የምናቀርባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች አሉ። ከእነዚህ ምርጫ አልባ እውነቶች መካከል አንዱ፣ “መዳን በእምነት ብቻ ነው” የሚለው የማይለወጥ እውነት ነው። የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊና አብዛኛው ኦርቶዶክሳውያን ግን ይህን ዐሳብ የሚረዱት በተቃራኒው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፣ “መዳን በእምነት ብቻ ነው” ሲል፣ ሥራን የሚክድና የሚቃወም ወይም ደግሞ በሌላ ጽንፍ፣ “ድነናልና ሥራ ለምኔ!” ለሚሉ አያሌዎች ይኹንታ የሚሰጥ የሚመስላቸው ብዙ ናቸው።



Thursday 8 July 2021

ከፍያለው ቱፋ፤ እግዚአብሔር በምሕረት ያስብህ!

ሃይማኖተኛ ሲታወር፣ ከዓለማዊ ይልቅ ዓመጸኛ እንደሚኾን አውቃለሁ። ትኵረት ለመሳብና ሰውን ለማስከተል፣ እምነቴና መረዳቴ እንዲህ ነው ብሎ መውረድ እንዴት ያጸይፋል?! ጌታችን ኢየሱስ፣ “በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል።” (ማቴ. 11፥22) ብሎ ተአምራት አይተው የካዱትን ኮራዚዮንና ቤተ ሳይዳን በጽኑ እንደ ወቀሰው፣ ከደነደነ አማኝ ይልቅ ያላመነ አሕዛብ ተስፋ እንዳለው በግልጥ ነግሮናል።

Sunday 4 July 2021

ከመንፈስ ቅዱስ “የተሻሉ አማኞች”!

 Please read in PDF

“ተግሣጽን የሚወድ ዕውቀትን ይወዳል፤ መታረምን የሚጠላ ግን ደነዝ ነው” (ዐመት)(ምሳ. 12፥1)

አይመጣም እንጂ ቢመጣ፣ ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ዘመን ካሉ አያሌ አማኞች የሚገጥመው ተቃውሞ እንዲህ የሚል ነው፤ “ምን ነክቶህ ነው ግን፣ ያን ኹሌ የቆሮንቶስን ነውር ፊት ለፊት የተናገርከው? በፍቅር ቀስ ብለህ በግል አትነግራቸውም ነበር? አጉል መተቸት ለምን ትወዳለህ? የሐዋርያት “አለቃ” የነበረውን ቅዱስ ጴጥሮስን ፊት ለፊት ስትቃወምስ ትንሽ ለምን አላፈርክም? ደግሞ የገላትያ አማኞችን አዚም[ጥንቆላ] ማን አደረገባችሁ ትላለህ እንዴ? …