Monday 28 May 2018

ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንና የ“ዲያቆን” ዳንኤል ክብረት የክፋት ሸፍጥ (ክፍል ፩)


ቂቀ እስጢፋኖሳውያንና የ“ዲያቆን” ዳንኤል ክብረት የክፋት ሸፍጥ (ክፍል ፩)
መግቢያ
   ዚህ ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የኾነኝ “ቀሲስ” ዳንኤል ክብረት የተባለ ሰው፣ በebs tv በአርአያ ሰብ(Who is Who) ፕሮግራም ላይ፣ በቀን 19/9/2010 ማታ 2፡00 ሰዓት ገደማ ላይ ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንን በተመለከተ በሰጠው ቃለ ምልልስ፣ ፍጹም ሸፍጥና ክፋት የተሞላበትንና ከታሪክ እውነታ ያፈነገጠ ሃሳብን በማቅረቡ፣ እውነታውን ከቤተ ክርስቲያኒቱ መጻሕፍትና ከአባቶቿ አንደበት ማሳወቅ አስፈላጊ ኾኖ በመገኘቱና ነው።
   ለዚህም ጽሑፉ ከደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ታሪካዊ ዳራ ይልቅ እጅግ በአመዛኙ በእነርሱ ላይ የተፈጸመውና ቤተ ክርስቲያን በመጻሕፍቶቿ የያዘቻቸው እውነት ከቅዱሳት መጻሕፍት[1][ከመጽሐፍ ቅዱስ] አንጻር እንዴት ይዳኛል? ዳንኤል ክብረትስ ምን የተለየ ሃሳብን በደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ዙርያ ይዞ ብቅ አለ? ይዞ ብቅ የማለቱ እሳቤስ ምን መዘዝ አለው? ቅዱሳት መጻሐፍትስ እንዴት ይዳኙታል? ዳንኤልና ቅዱሳት መጻሕፍት ምን ያህል ጥብቅ ዝምድና አላቸው? ዳንኤል በማናቸው ምክንያትስ ቢኾን የሰው በአሰቃቂ ኹኔታ መገደል የሚገደው ነውን? … የሚሉና ሌሎች ተያያዥ ኹኔታዎችን በአጭሩ ለመዳሰስ እንሞክራለን።

Saturday 26 May 2018

ከአጋንንት ምስክርነት?


ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣበት ዋና ዓላማ የዲያብሎስን ሥራ ያፈርስ ዘንድና (1ዮሐ.3÷8) በኃጢአት የታሰሩት ነጻ ወጥተው ህይወት እንዲሆንላቸው፤ እንዲበዛላቸውም ነው፡፡ (ዮሐ.10÷10)፡፡ ይህንን ለማድረግም ቀድሞ “ኃይለኛውን ሰይጣን ማሰር” እንደሚገባና ከዚያ በኋላ “ወደኃይለኛው ቤት በመግባት ቤቱን መዝረፍ” ማለትም ሰይጣንን በማሸነፍ አጋንንትን ማውጣት ፣በክፉ መንፈስ የሚሰቃዩትን፣ በኃጢአት ባርነት የተያዙትን በጽድቅ ነጻ በማውጣት ምርኮን መከፋፈል እንደሚገባ አስተምሮናል፡፡ ትልቁ የጌታ ምስራችና የአገልጋዮቹ ደስታ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት፣ ምስክርነትና የሥልጣን ቃል የአጋንንትና ግዛት በማስደድ መንግስቱን ወደሰዎች ልብ ግዛት ማቅረብ ነው፡፡

በቤቱ የተዘነጋ አባ ወራ

   ጽሐፍ ቅዱስ ወንድ አባ ወራ እንደ ኾነ ይነግረናል፤ “ባል የሚስት ራስ ነውና።” (ኤፌ.5፥23፤ 1ቆሮ.11፥3)፣ እንዲል። እናም ወራውን(ቤተሰቡን) በአግባቡ ማስተዳደር አለበት፤ “ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤ ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል?” (1ጢሞ.3፥4-5)። አባ ወራነት አስቀድሞ የወራ[በኦሮሚኛ ቤተሰብ ማለት ይኾንን?] ምስክርነት ያሻዋል፤ ቤተሰቡን የማይወድና ለቤተሰቡ ምንም ከበሬታ የሌለው አማኝም ኾነ አገልጋይ በውጭ ያለውን ዓለም በመላው እንደ ሚወድ ቢናገር ወይም ቢያሳይ ግብዝ ወይም አርቲስት እንጂ ሌላ ምንም ሊኾን አይችልም።
   የባል አባወራነቱ አስተዳደራዊ ነውና፣ ትልቅ ፍቅር የሚጠይቅ ነው። በትልቁም በትንሹም ውድ የኾነውን የባሎቻቸውን ፍቅር ያዩ ሚስቶች፣ ለባሎቻቸው እስከ ሞት በሚያደርስ ፍቅር እንደ ሚታመኑ ጥርጥር የለውም። ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን ፍቅር ዓይታ ለነፍሷ እንደ ማትሳሳ እንዲሁ፣ ሚስቶችም የአባ ወራቸውን “ደማቅ” ፍቅር ዓይተው ለባሎቻቸው የማይታመኑበት፣ ልጆችም አባታቸውን እንደ “ንጉሥ” የማያዩበትና የማያከብሩበት አንዳች ምክንያት አይኖርም።

Tuesday 22 May 2018

ጌታችን ኢየሱስ ወደ ሰማያት ለምን ዐረገ? (የመጨረሻ ክፍል)

Please read in PDF

3.ሌላው አጽናኝ ወደ እኛ ይመጣ ዘንድ፤
  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ መስቀል ነፍሱን ስለ ሰው ልጆች አሳልፎ ሊሰጥ እጅግ በቀረበበት ሰዓት፣ ደቀ መዛሙርቱ እጅግ ማዘን ጀምረው ነበር፤ ተላልፎ እስከ ተሰጠባትና መስቀል ላይ እስከ ወጣበት ጊዜ ድረስ መከራው በሙሉ ያነጣጠረው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ነው። ነቀፌታውም፣ ስድቡም፣ ትችቱም፣ ጥላቻውም፣ መገለሉም፣ መሰደዱም፣ በመጨረሻም በመስቀል ከባድ መከራንም የተቀበለው ጌታችን ኢየሱስ ነው። ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን መከራው እነርሱንም እንደ ሚያገኛቸው አስቀድሞ አልነገራቸውም፤ ምክንያቱም በእርሱ ሕይወት ሲያልፍና ሲኾን የነበረውን ኹሉ ሲመለከቱ ነበርና። ከንግግር ይልቅ ሕይወት የማስተማር አቅሙ እጅግ ታላቅ ነውና!
 ነገር ግን ወደ ሰማያት ወደ አባቱ ሊሄድ ሰዓቲቱ እንደ ደረሰች ሲያውቅ፣ “እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደ ሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።” (ዮሐ.16፥1-2) በማለት፣ መከራው ለእነርሱም እንደ ማይቀር ነገራቸው። በጌታችን ኢየሱስ ላይ የወረደው የዓለሙ ኹሉ ጥላቻ በእነርሱም ይፈስሳል፤ የተገለጠ ንቀትም ፊት ለፊት ያገኛቸዋል፤ በዓለሙ ኹሉ ፊት እንደ ጉድፍ ይቆጠራሉ፤ ጌታቸው ባለፈባት የምጥ መንገድ እነርሱም ያልፉ ዘንድ አይቀርላቸውም። የመከራው ጫፍ ሰዎች እነርሱን ሲጠሉ፣ ሲያሳድዱ፣ ሲገድሉ … ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን የማቅረብ ያህል በጭካኔ ያደርጉባቸዋል። በዛሬ ዘመን ምን እየኾነ ይኾን? ሰዎች የእግዚአብሔር ሰዎች ነን እያሉ፣ በሃይማኖት ሽፋን ሰዎችን ለምን ይገድላሉ? ይጠላሉ? ያሳድዳሉ? የሰዎችን ስምስ በመረረ ጥላቻ ለምን ያጠፋሉ? …።

Saturday 19 May 2018

ጌታችን ኢየሱስ ወደ ሰማያት ለምን ዐረገ? (ክፍል ፪)


2. ምስክርነታችንን እጅግ የታመነ ይኾን ዘንድ፤
   ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማያት ካላረገና ካልሄደ በቀር ምስክርነታችን ምሉዕ አይኾንም፤ ጌታችን ኢየሱስ ወደ ሰማያት ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን ምስክሮች እንደ ሚኾኑ ተናገራቸው፤ (ሐዋ.1፥8)፤ ምስክርነታቸው ከጌታ ኢየሱስ ለሠሙትና ላዩት ነገር ኹሉ ነው፤ (1ዮሐ.1፥1-3)፤ ካዩት ነገር ዋናውና አንዱ ደግሞ ዕርገቱ ነው። ቅዱሳን መላእክት ማረጉን ወዲያው ተናገሩት፣ “ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል” (ሐዋ.1፥11) በማለት። ጌታችን ኢየሱስ ወደ ሰማያት ወደ አባቱ ክብር ይገባ ዘንድ ዐርጓል፤ ስለዚህ “ትኩር ብላችሁ ወደ ሰማያት አትመልከቱ፤ በመመልከትም ጊዜን አታባክኑ፤ እስከ ምድር ዳርቻ ልታስተምሩ ገና ሰፊ በርና አገልግሎት አላችሁ” አሏቸው፤ አዎን! ሰማይ በዕርገቱ ሲከፈት፣ በምድር ደግሞ የአገልግሎት በር መርቆ ተከፈተ።
  የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ብዙ ተጠራጣሪዎችን ወደ እምነት መንገድ መልሷል፤ ቅዱስ ማቴዎስ እንዲህ ይለናል፣ “አሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ግን ኢየሱስ ወዳዘዛቸው ተራራ ወደ ገሊላ ሄዱ፥ ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ የተጠራጠሩ ግን ነበሩ።” (ማቴ.28፥16-17)፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማያት ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱ አምልከውታል፤ ስግደትም አቅርበውለታል። በሌላ ሥፍራም ወደ ሰማያት ሲያርግ እንደ ሰገዱለት ተጽፎ እናገኛለን፤ (ሉቃ.24፥52)። የባሕርይ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ስግደትና አምልኮን ይቀበል ዘንድ ይገባዋል።

Thursday 17 May 2018

ጌታችን ኢየሱስ ወደ ሰማያት ለምን ዐረገ? (ክፍል ፩)

Please read in PDf 

  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ማረጉ ለእኛ ክርስቲያኖች ዋስትናና ወደ ሰማያዊው ዓለም ለመፍለሳችን ታላቅ የማይናወጥ ምስክራችን ነው፤ ዕርገት ከክርስትና ዋና ትምህርቶችም እንደ አንዱ የሚቆጠርበት ምክንያቱና ዕርገቱን አለ መቀበልም ከዋናዎቹ መናፍቃን የማስቆጠሩም የማይካድ እውነታ ይኸው ነው። እናም ጌታችን አምላካችን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ሰማያት በክብር ማረጉ፣ ለእኛ ለክርስቲያን አማኞች ታላቅ ፋይዳ አለው። ከእኒህ ታላላቅ ፋይዳዎች ሦስቱን መጥቀስ እንችላለን፤ እኒህም፦

Tuesday 8 May 2018

ጮኸን የለፈፍነው

Please read in PDF

ልክ ነው መስቀሉ፥ እንጨት ነበር ያኔም፤
መዳብ ነው? ወርቅ ነው? ነሐስ ነው? …
                     እያልን መቼም አልሞገትንም

Wednesday 2 May 2018

አዎንታዊ ሐድሶ

Please read in PDF

የኋለኛው ቤትህን "አዲስ" ልትገነባ
በጥንቱ ጎጆህ ላይ ዕቅድ ስታወጣ
ለማፈራረሱ ራርተህ እዘንለት፤