Tuesday 29 March 2022

ማራን አታ!

 Please read in PDF

“ማራናታ” የሚለውን ቃል፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማኹት፣ በ20/7/1995 ዓ.ም በከሰዓት መርሐ ግብር፣ በሻሸመኔ ከተማ በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በተደረገ ጉባኤ ላይ [ያኔ ይህን ጉባኤ ለመታደም ከአርሲ ነጌሌ፣ ሻሸመኔ ድረስ በእግራችን ነበር የምንሄደው] ከመምህር ይልማ ቸርነት አንደበት ነው። በዕለቱ መምህሩ፣ በዘፍጥ. 3፥10 ላይ ያለውን ኃይለ ቃል አንስቶ አስተምሮ፣ ትምህርቱን ሲያሳርግ፣ “ማራናታ” የሚለውን ቃል ሲናገር፣ ትርጉሙ ባይገባኝም፣ ቃሉ በልቤ መካከል ተሰንቅሮ ከብዙ ጥያቄዎች ጋር በውስጤ ቀረ። በጊዜው መምህሩን አጊኝቼ ትርጕሙን ለመጠየቅ ዕድል ባላገኝም፣ በተደጋጋሚ ብዙ ሰዎችን ጠይቄ የመለሰልኝ ሰው ግን አልነበረም።

Saturday 26 March 2022

የካውንስሉ የማይቀር መንገዳገድ!

 Please read in PDF

ቅዱስ ቃሉ፣ “በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።” (ኤፌ. 4፥3) እንዲል፣ ቤተ ክርስቲያን ከምንም ነገር ይልቅ መጠንቀቅ ያለባት ለመንፈስ አንድነትዋ ነው። መሲሑ በሊቀ ካህናትነት በጸለየውም ጸሎትም፣ “ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው።” (ዮሐ. 17፥11) የሚል ነው። ሰይጣን፣ ቤተ ክርስቲያንን ከሚፈትንበትና ድል ከሚያደርግበት አንዱና ዋናው መንገዱ፣ መለያየት፣ መከፋፈል፣ ክፉ የልዩነትን ዘር በመዝራት ነው። “አንድ ቤተሰብ እርስ በእርሱ ከተለያየ ጸንቶ መኖር አይችልም” እንዲል (ማር. 3፥25)።

Wednesday 23 March 2022

ይድረስ ለፓስተር ቸሬ!

 Please read in PDF

“ኢየሱስን መንፈስ ቅዱስ ብቻ እንጂ ሥጋና ደም አይገልጠውም!”

“ኦርቶዶክሶች ማርያም ካለቻቸው እንዴት ኢየሱስ የላቸውም ብለህ አሰብህ? … ።” (ከፓስተር ቸሬ ንግግር የተወሰደ)

ፓስተር ቸሬ፣ “ኤጳፍራ ቤተ ክርስቲያን” በሚባል ከወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት በአንዱ፣ የሚያገለግል አገልጋይ ነው። አገልጋዩ በትዳር እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮችና በስህተት መምህራን ላይ በሚናገራቸው ንግግሮቹ በአብዛኛው ይታወቃል። እኔም በበኩሌ የተወሰኑ ትምህርቶቹን ለመከታተል ጥረት አድርጌ፣ በተወሰነ መንገድ ተጠቅሜበታለሁ። አገልጋዩ በትዳር ጉዳዮች ላይ ባለው ትምህርቱ ቢቀጥል፣ እጅግ ትርፋማ ይኾናል ብዬም ገምታለሁ። ከሰሞኑ ግን “ለኦርቶዶክሳውያን ወንጌል መሰበክ የለበትም፤ ያውቁታል” የሚል መልእክት ያለው ንግግር ማሰማቱን ሰምቼ ይህን ለመጻፍ ተገደድሁ።

Sunday 20 March 2022

የጌታ ያልኾኑ የጌታ ነበርን ባዮች!

 Please read in PDF

የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ፣ “ተሐድሶ ወይም ሐድሶ” የአንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንቅስቃሴ፣ በመኾኑ እንጂ፣ የአንድ ወይም የተለዩ አካላት መጠሪያ በመኾኑ አያምንም። አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፦ “ሐድሶ ማለት ማደስ፤ መለወጥ፤ ሐዲስ ማድረግ፤ ማጥናት ማበርታት፤ መሥራት መጠገን፤ ያሮጌ የሰባራ።” በማለት ተርጉመው፣ “ሐዳሲ ወይም ሐዳስያን ማለት ደግሞ፣ የሚያድስ የሚጠግን፤ ወጌሻ፤ ገንቢ፤ ዐናጢ” ብለው፣ ውጤቱን ደግሞ፣ “ተሐደሰ፤ ታደሰ፣ ተለወጠ፤ ዐዲስ ኾነ” በማለት በግልጥ የተረጐሙትን ትርጒም ታሳቢ በማድረግ፣ “ሐዳሲ ወይም ሐዳስያን” የሚለውን ቃል ይጠቀማል።

ሐዳሲነት፣ ጤናማ ትምህርትና ሕይወት ይፈልጋል!

Friday 18 March 2022

ምኩራቡ!

Please read in PDF 

ቅዱሳት መጻሕፍት የሚነበቡበት

የሚፈከሩበት የሚሰበኩበት

ምኩራቡ ነበረ ውብ ዓውደ ምሕረት

Wednesday 16 March 2022

“የሎጥን ሚስት አስታውሱ” (ሉቃ. 17፥32)

 Please read in PDF

ስለ ኢየሱስ ብዙ ተናግሬአለሁ፤ ከእንግዲህ ስለ ማርያም በመናገር ዘመኔን አሳልፋለሁ” (ወደ ኦርቶዶክስ ከተመለሱት አንዱ የተናገረው)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ወደ ኋላ ስለ መመለስ ጠቅሶ ከተናገራቸው ምሳሌዎች አንዱ፣ ወደ ኋላ በመመለስዋ ምክንያት፣ የጨው ሃውልት የኾነችውን የሎጥን ሚስት በመጥቀስ ነው። የሎጥን ሚስት በምሳሌነት ከማንሳቱ ጋር አያይዞ፣ እንዲህ የሚል ምሳሌም አብሮ ተናግሮአል፤ “በቤቱ ጣራ ላይ ያለ ማንም ሰው በቤቱ ውስጥ ያለውን ንብረት ለመውሰድ አይውረድ፤ እንዲሁም በእርሻ ቦታ ያለ ሰው ወደ ኋላው አይመለስ።” ይላል። ጌታችን ይህን ምሳሌ ጠቅሶ ባስተማረበት ቦታ የነበሩ ሰዎች፣ በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በመኾናቸው፣ የቤቶቻቸው ጣራ ክፍትና ለመዝናናት ምቹ እንዲኾን ተደርጎ የተሠራ ነበር።

Thursday 10 March 2022

ጾም ለአዲሱ ሰው

 Please read in PDF

በድጋሚ፣ በቅድስና እየጾማችሁ ላላችሁ፣ እንኳን ለዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ!!! ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ እየተመላለሰ በሚያስተምርበት ወቅት፣ የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ቀርበው፦ “እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀ መዛሙርት ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው? አሉት” (ማቴ. 9፥14)፡፡ እነዚህ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት፣ መጾማቸው መልካም ነበር። በጾማቸው ውስጥ ግን የሚያዩት እግዚአብሔርን ሳይኾን፣ የሌሎችን አለመጾም ነበር። ስለዚህ ጾማቸው፣ “በክስ የተሞላ ሥነ ሥርዓትን” ብቻ ያሟላ እንጂ የልብ መሠበር፣ የንስሐ መንፈስ፣ ፍቅር የነበረው አልነበረም። ጾማቸውን ለሃይማኖታዊ ውድድር ወይም ውርርድ አውለውታል። ስለዚህ መልስና እርካታ ያለው አልነበረም። ጾም ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት መንፈሳዊ መስመር፤ ቅዱስም ተግባር ነው።



Tuesday 8 March 2022

ኢየሱስ እስኪመጣ አሥር ዓመታት በጡመራ መድረክ አገልግሎት!

 Please read in PDF

እግዚአብሔር አምላኬ በብዙ ባበዛልኝ ጸጋ ተደግፌ፣ ላለፉት አሥር ዓመታት በጡመራ መድረክ (blog) አገልግያለሁ። ቅዱስ ጳውሎስ፣ “ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል።” (1ቆሮ. 3፥11-13) እንዲል፣ አገልግሎቴ አንድ ጊዜ በተመሠረተው መሠረት ላይ እንጂ፣ አዲስ ወይም ወይም ሌላ መሠረት በመመሥረት አልነበረም። ምክንያቱም አዲስ መሠረትን ብመሠረትና ከኢየሱስ የተለየ ወንጌልን ብመሰክር አገልግሎቴ በእሳት ሊበላ አለውና።

Monday 7 March 2022

ከአምልኮተ ኢትዮጵያ ተጠበቁ!

 Please read in PDF

ብሔራዊ ቲያትር ላይ አድዋን አስመልክቶ በተዘጋጀው “ዝክረ አድዋ” መርሐ ግብር ላይ፣ “‘ከኦርቶዶክስ’ በቀር ሃይማኖት የለም!” ባዩ ዘበነ ለማ፣ “ሃይማኖቶችን አክብሮና ኢትዮጵያዊነትን አስመልኮ” መቅረቡ ይደንቃል! በትያትር ቤቱ አዳራሽ ያሉ ደግሞ፣ ጩኸታቸውና ጭብጨባቸው በትክክል “ምናባዊቷን ኢትዮጵያ” ተስላ እንጂ በእውን ሳያዩ በደንብ ይስተዋላል። ዘበነ ለማ ከተናገራቸው ንግግሮች ውስጥ እኒህ ደማቅ ትምክህቶች ጎልተው ይሰማሉ።


Wednesday 2 March 2022

ጾሙ ተሐድሶ ያስፈልገዋል!

Please read in PDF

ጾም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አምልኮ ሲኾን፣ ክርስቲያን የኾነ ኹሉ በግልም ኾነ በማኅበር እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ ለማምለክና ወደ እርሱ ለመጸለይ፣ ይቅርታን ለመለመን፣ ስለ ተለያዩ ችግሮችና የልብ መሻቶች የእግዚአብሔርን ርዳታና ምላሽ ለማግኘት እግረ ልቡናውን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀናበት መንገድ ነው። እግዚአብሔር የሚፈልገው በትሕትና የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ በመኾኑ፣ ክርስቲያን በጾሙ ራሱን ከኀያሉ እግዚአብሔር እጅ በታች ስለሚያዋርድ፣ እንዲህ በእውነት ተዋርዶ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበውን አምልኮትና ጸሎትም እግዚአብሔር ስለሚቀበለው ችግሩ ይቃለላል፤ጥያቄውም ይመለሳል፤ (መዝ. 51፥17፤ 1ጴጥ. 5፥6)።