Tuesday 24 April 2018

Namni nama malee Hafuraa miti! (kutaa 3ffaa)

Please read in PDF

Waaqayyoon “akka bifa keenyaatti, akkaa fakkaattiis nama ni umna” dubbi jechuu isaa(Uma.1:26-31)
Kutaan kitaaba Qulqulluu kun namni bineensa lubbuu qabu irraa “haa ta’u, haa ta’u” jedhee Waaqayyon akka hin uumne agarsiisa. Inumayyuu kabajaafi jaalala guddaan harka isaatiin kan tolchee, kanas immoo bifa fi fakkaatti isaatiin uumu isaa ni agarra. Waaqayyoon akkeenya(dhaqna Hafuraa) isaa akka callaqisnu uumama keenya keessatti ibsuun fedha isaa ibseera. Kanaanis namni bineensa kamiyyuu irraa adda ta’u isaa hubachuu dandeenya. Sagalee Waaqayyoo sirritti hubbachuudhaaf sagalicha warri dura dhaga’e maal akka hubatee sakkata’uun bayyee barbaachisaa dha. Warri dura hubatee waan hubateen alatti; nutis addatti wanti haarayatti hubannu tokkoleen hinjiru.

Monday 16 April 2018

“ዓለም ያለድንግል ማርያም አማላጅነት አይድንም” ማለት፥ የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ ማክፋፋት ነው! (የመጨረሻ ክፍል)

Please read in PDF

ዓለም የሚድነው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ካመነ ብቻ ነው!
     ደቀ መዛሙርት ቅዱሱን ጰራቅሊጦስን እንደተቀበሉ ወዲያው ያስተማሩት እንዲህ የሚል ነው፦ “የሕይወትንም ራስ ገደላችሁት፤ እርሱን ግን እግዚአብሔር ከሙታን አስነሣው፥ ለዚህም ነገር እኛ ምስክሮች ነን” (ሐዋ.3፥15)፤ በመቀጠልም በሁለተኛው ቀን ስብከታቸው እንደገና፥ “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና” (ሐዋ.4፥12) ብለዋል፡፡ እውነት ነው እርሱ ራሱ ጌታችን ኢየሱስ፦ “ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥ በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል”፤ (ሉቃ.24፥46-47)፡፡

Friday 13 April 2018

“ዓለም ያለድንግል ማርያም አማላጅነት አይድንም” ማለት፥ የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ ማክፋፋት ነው! (ክፍል ፪)

Please read in PDF

ያድነን አንድያ ልጁን ላከ፤ አዳነንም!
    ቅዱሳት መጻሕፍት በአንድ ቃል ተስማምተው እግዚአብሔር አምላክ ዓለሙን እንዲያድን አንድያ ልጁን መላኩንና አንድያ ልጁም ዓለሙን ሁሉ በደሙ ከኃጢአት ሁሉ እንዳነጻ ይመሰክራሉ፡፡ “እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና” (ዮሐ.3፥16) የሚለው ቃል፣ ሰውን ለመውደድ መነሻውና ምንጩ አንድያ ልጁን በፈቃዱ የሠጠን ራሱ አብ አባታችን መሆኑን ነው፡፡ አስተውሉ! አዳም በወደቀ ጊዜ ቅድስት ሥላሴ “ወዴት ነህ?” ብሎ ፈለገው፡፡ አሁንም ከሥላሴ አንዱ አካል አብ “ውድ ልጁን እስኪሰጠን ያለምክንያት በእንዲሁ ፍቅር” ወደደን፡፡ ክብር ይግባው፡፡ አሜን፡፡
   ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በፈቃዱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሊያድነን “አማኑኤል” ሆነ፤ ተወለደም (ማቴ.1፥23)፡፡ “ሥጋ ያልነበረው እግዚአብሔር አምላክ ቃል ወደእኛ መጥቶ በፈቃዱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ነፍስ ዕውቀት ያለው ሥጋን ተዋሐደ” (ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ ምዕ.25 ክፍል 4 ቁ.37፡፡ ገጽ.60) እንግዲህ ጌታችን ከሰማያዊ ዙፋኑ ወደእኛ የመጣው በፈቃዱ ነው፡፡

Saturday 7 April 2018

በ'ኛ ገኖ እንዲኖር!


ገሃነም ፈረሰ ሲዖል ተረገጠ
ኃጢአት ተሸነፈ ሞት ኃይሉ ተዋጠ
መፍረስ መበስበስም ተሻረ አበቃ
መቃብርን ሽሮ ከብሯልና ጌታ!
ከዚህ የተነሣ ...

Tuesday 3 April 2018

“ዓለም ያለድንግል ማርያም አማላጅነት አይድንም” ማለት፥ የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ ማክፋፋት ነው! (ክፍል ፩)

Please read in PDf

የስህተት ትምህርቶች በየዘመናቱ የየራሳቸው መልክና ጠባይ አላቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ ለሚነሱ ኑፋቄያትና የተዛነፉ አስተምኅሮዎች እንደቀደሙት ቅዱሳን አባቶች መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ መክራ ዘክራ፣ አስተምራ ሞግታ፣ የሳተውን አቅንታ፣ በስህተቱ የጸናውንና ሊመለስ ያልወደደውን ለይታ በቅዱስ ቃሉ ማዕከልነት ማስተካከል ይገባታል፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተሰጣት መለኮታዊ ሥልጣን አለ፤ ይህን ባታደርግ ደግሞ ከአምላካዊ ወቀሳ ፈጽሞ ላታመልጥ ትችላለች፤ (1ዮሐ.4፥1፤ ራእ.2፥2)፡፡
    ከላይ በርእስነት በተናገርነው ሃሳብ ዙርያ፣ ማኅበረ ቅዱሳን የተባለው ማኅበር እየፈራና እየተባ፣ በግልጥ ከመቃወምና ካለመቃወም መካከል ቆሞ እንዲህ መናገሩ “ይደንቃል”፦
    “አንዳንድ ባሕታውያን ነን የሚሉ ሰዎች መናፍቃን ጸረ ማርያም በሆነ ትምህርታቸው ስለሚታወቁ ከዚያ በተቃራኒው በመቆም የበለጠ ተወዳጅነትን ለማትረፍ ሲሉ እመቤታችንን ያከበሩ በሚመስሉ ስሕተትና ኑፋቄ አዘል ትምህርቶችን ያስተምራሉ፡፡ በዚህ ዓይነት መልኩ በአንድ ግለሰብ የተጀመረ መፈክር መሰል ትምህርት ባጭር ጊዜ ውስጥ ተሰራጭቶ ብዙዎች የሚደጋግሙት በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ሳይቀር የሚደመጥ፣ በታላላቅ ጉባኤዎች ላይ በጉልህ ተጽፎ ብዙ ሰዎች ሊመለከቱት በሚችሉት መልኩ ሲሰቀል ማየት ተለምዷል፡፡ አባባሉ የአምላክን ሁሉን ቻይነት የሚፃረር መሆኑን፣ አምላክ እርሱ በፈቀደው መንገድ ዓለምን ማዳን የሚችል መሆኑን ገልጠው የተናገሩ ሰዎች ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፡፡
    አምላካችን ዓለምን ሲያድን እመቤታችንን ለተሰግዎት ቃል መረጣት እንጂ እርሷ አልመረጠችውም፡፡” [1]

Sunday 1 April 2018

“ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው” (ማቴ.21፥11)



    አይሁድ መምህራንና የካህናት አለቆች፣ ሽማግሌዎችም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመግደል ካስቸኮላቸውና ቶሎ እንዲገድሉት ውስጣቸውን “እጅግ ካነሣሣው” ነገሮች አንዱ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሲሕነቱን መግለጥ ነው፤ ወደኢየሩሳሌም ሲገባ እርሱ የገባው እንደ አንድ ምድራዊ ንጉሥ ወይም የጦር መሪን በሚመስል መልክ በፈረስ አልነበረም፤ ነቢዩ ዘካርያስ እንደተናገረ፦ “አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ” ነበር፤ (ዘካ.9፥9)።