Wednesday 29 November 2017

የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፬


ሰው መንፈስ ነውን?

   ሰው ሥጋና ነፍስ ወይም ሥጋና መንፈስ ነው፤ የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት የብልጥግና ወንጌል[1] መምህራን፣ “ሰው መንፈስ ነው፤ ነፍስ አለው፤ በሥጋ ውስጥ ያድራል፡፡”[2] በሚለው ፍጹም ክህደት ደምድመውታል፡፡ “ሰው መንፈስ ነው” የሚለው ትምህርታቸውን የሚያስተምሩበት ዓላማቸው ኋላ ላይ አግተልትለው ከሚያመጡት “ፈጣጣ ክህደት” አንጻር እንጂ ወዲያው አይገባንም፡፡ በአጭሩ “ሰው መንፈስ ነው” የሚሉበት ዋና ዓላማቸው ሥጋ ለባሹን ሰው፣ “እግዚአብሔር ለማድረግ” ከሚባዝን ከንቱ ምናባዊ ቅዠት የተነሣ ነው፡፡ ይህንን በድፍረት ኢትዮጲያዊው የቃል እምነት መምህሩ ኃይሉ ዮሐንስ እንዲህ ይላል፦
   “ … አዎ ልክ እንደእግዚአብሔር ነን[ኝ] በሚለው እስማማለሁ፤ ምን ማለት ነው ይህ? መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች አሉኝ፤ በመጀመርያም የምሄደው ዘፍ.1፥26-28 ያለውን በመጥቀስ ነው፤ … ያ መልክና አምሳል ሙሉ ለሙሉ እግዚአብሔርን እንድንመስል ያደርገናል የሚል አመለካከት አለኝ፡፡ ግን “detail” መሄድ ቢያስፈልግ ጌታችን ኢየሱስ ስለራሱ የተናገራቸው ነገሮች ትዝ ይሉኛል፤ በዮሐ.14፥8 ላይ … “እኔና አብ አንድ ነን” ያለበት ሃሳብ በእኔ አመለካከት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ የእግዚአብሔር ልጅ ማለት ደግሞ ሰው ነው፤ በእኔ አመለካከት የሌላውን ሰው አመለካከት ልጋፋው አልችልም፡፡ ጌታ ኢየሱስ “እኔና አብ አንድ ነን” ካለ፣ ታላቅ ወንድማችን እንደዛ ካለ፣ እኛ ደግሞ ከአባታችን ጋር አንድነታችንን መናገር እንችላለን፤ ምክንያቱም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው እኛም ደግሞ የእግዚአብሔር ልጆች ነን፡፡

Saturday 25 November 2017

ሁሉ አንሶ ይታየኝ!


እልፍ ጥሪት ኖሮኝ ሕይወት እንዳላጣ
በሚስቴ ተክቼህ ካንተ እንዳልፋታ
እናት አባት ወንድም እህትና ዘመድ ...

Monday 20 November 2017

የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፫

2. ታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰውነቱ የተናገረውንና የተነገረለትን ልክ ለመለኮቱ እንደተነገረ ተቆጥሮ ሲካድ እንመለከታለን፡፡ ለዚህም እንደዋቢ አድርገው የሚጠቅሱት፣ “የክርስቶስን ከዘላለም የእግዚአብሔር ልጅ አለመኾኑን” ሁለት ሃሳቦችን በአንድነት በመስፋት ነው፡፡ እንዲህ በማለት፦ “አብና ወልድ …እኩል አይደሉም፤ አብ ወልድን ይበልጣል፤ … ገብርኤል እንዳለው ስሙ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል፤ ከዛ በፊት አባታችን ነው፤ ሌላ ማስረጃ በዕብ.2 ላይ “ልጆቹ በሥጋና በደም እንደሚካፈሉ እርሱም እንዲሁ በሥጋና በደም ተካፈለ፤ ማን ተካፈለ? አባታቸው፡፡ ስሙ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል በሚል የእግዚአብሔር ልጅ ብሎታል፤ ከዛ በፊት ልጅ አልነበረም ወይ? ልጅ አልነበረም፤ አባታችን ነው፡፡ አባትና ልጅ መሆንም አይችልም፡፡ … ኢየሱስ ክርስቶስ ለዘለዓለም ልጅ ከነበረ ለዘለዓለም ከአብ ያንስ ነበር ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ሥጋ የለበሰው መች እንደኾነ እናውቃለንና፤ ሥጋ የለበሰው የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ከድንግል ማርያም በተወለደበት ጊዜ ነው ልጅ የኾነው፡፡ ያን ጊዜ “officially”[በግልጥ ወይም በይፋ ለማለት ይመስላል] እግዚአብሔር የነበረው ሥጋ ሲኾን፣ አብ ከእኔ ይበልጣል፤ ብታምኑስ አብ ከእኔ ይበልጣል ብሏል፤ አብ ስለሚበልጠው እንደውም በሁሉ ነገር ይጸልይ ነበር እንደማንኛውም ሰው፤ እርሱ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ነው ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ከኾነ “somehow”[እንደምንም] የኾነ ቦታ ተወልዷል ማለት ነው፤ …የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር አይደለም፡፡”[1] በማለት፡፡
    “ኢየሱስ ከአብ ጋር አይተካከልም” ለማለት መናፍቃኑ የሚጠቅሱት ጥቅስ፣ በእውኑ ክፍሉ እነርሱ እንደሚሉት ሃሳባቸውን ይጋራልን? እውን ቃሉ እነርሱ እንደሚሉት የኢየሱስን የመለኮታዊ “ታናሽነት” ይናገራልን? የጌታችን ኢየሱስ ልጅነት ወይም አባቴ ብሎ መጥራቱ የእርሱን አምላክ አለመኾንን ያመለክታልን? ዓውዱስ ያንን የሚል ነውን? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ክብር እንደሌለው የሚያመለክት ነውን? … እና ሌሎችንም ተያያዥ ጥያቄዎችን በማንሳት መመርመር ይኖርብናል፡፡
ብ ከእኔ ይበልጣል” የማለቱ ምክንያት
   ንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ እጅግ በተደጋጋሚ የክርስቶስ ኢየሱስ ጌታችንን ከአብ ጋር ተካካይነት ሲገልጥልን አይተነዋል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደአባቱ እንደሚሄድ በተናገራቸው ጊዜ ልባቸው ታውኳል፣ (ዮሐ.14፥1)፣ ደግሞም ፈርተዋል፤ (ቁ.27)፡፡ ስለዚህ መፍራትና መሸበር እንደሌለባቸው በሚያጽናና ቃል ተናገራቸው፡፡ እንደውም የእርሱ ወደአብ መሔድ የተሻለ መኾኑን ስለሁለት ምክንያት ተናገራቸው፤ (1) “ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤”(ቁ.15-16)፣ (2) ጌታችን ኢየሱስ ወደአባቱ በመሄዱ አብ እርሱን ያከብረዋል፤ (ዮሐ.17፥5)፡፡ ደቀ መዛሙርቱ እኒህን ታላላቅ ምክንያቶች ያስተዋሉ አይመስሉም፡፡ ስለዚህም ለራሳቸው እጅግ ከማሰብ የተነሣ በራሳቸው ሃሳብና ኀዘን ውስጥ ተዋጡ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ እነርሱ በዚህ ዓይነት ድብልቅልቅ ስሜት ውስጥ እያሉ፣ “የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር” በማለት ተናገራቸው፡፡ ይህንንም ስለሁለት ነገር ተናግሯቸዋል፡፡ እኒህም፦

Thursday 16 November 2017

የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፪

ክፍል አንድ
    ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መለኰታዊ ማንነት መካድ፣ በእምነት እንቅስቃሴ መምህራን ዘንድ እጅግ የታወቀና እንግዳ ያልኾነ ነገር ነው፡፡ ምንም እንኳ በትምህርቶቻቸው መካከል በኢየሱስ ክርስቶስ “እንደሚያምኑ” ቢናገሩም፣ ነገር ግን እናምናለን የሚሉትን ሲያብራሩትና ሊያስተምሩት ሲነሡ ግን በትክክል ሲክዱት ይስተዋላል፡፡ በእርግጥም፣ የኑፋቄ መምህራንን ከምንለይበት መንገድ አንዱ፣ በደፈናው እናምናለን የሚሉትን የትኛውም ትምህርታቸውን፣ “እስኪ አብራሩት” ሲባሉ፣ ኑፋቄያቸው ወለል ብሎ ይታያል ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ በተቃርኖ ይቆማል፡፡
    ስለጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸውም ትምህርት እንዲህ የሚል ነው፦
   “ኢየሱስ መለኮታዊ መኾኑን ያወቀውና ያገኘው በውስጡ መኖሩን ፈልጐ ካገኘ በኋላ ሲኾን፣ ይህንንም በማወቁና ፈልጎ በማግኘቱ እጅግ ታላቅ አስተዋይ ሰው ነው፤ … ራሱም በአንደበቱ፣ “የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር” (ዮሐ.14፥28) ብሏልና፣ ከአብ ያንሳል፡፡ ሰው ብቻ ኾኖ እንጂ አምላክ በመኾን ፈጽሞ አልመጣም፡፡ ደግሞም በማናቸውም ሥፍራ ራሱን “እኔ አምላክ ነኝ” ብሎ አልገለጠም፡፡”
በማለት ይናገራሉ፡፡ ይህ ትምህርታቸው የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በግልጥ የሚክድ ነው፡፡
     በዚህ ትምህርታቸው ውስጥ ክርስቶስን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስን በመቃረን ብዙ ኑፋቄያት ተሰግስገው እናያለን፡፡ በዋናነትም ብንጠቅስም፦

Friday 10 November 2017

የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፩


Please readin PDF
መግቢያ
     የሐሰት መምህራን ክርስትና ከመጀመሩ በፊትም የነበሩና ያሉ፣ በእኛም ዘመን እንግዳ ኾነው የተከሰቱ ያይደለ ሲኾን፤ ትምህርታቸውም ከታየበትም ጊዜ ጀምሮ እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የሐሰት ትምህርታቸውን ሳይታገሱ ፊት ለፊት የተቃወሙ መኾናቸውን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ይነግረናል፡፡ ሐዋርያት በዘመናቸው ይሠራጭ የነበረውን የሐሰት ትምህርትና አስተማሪ መምህራንን ትምህርታቸውንና ስማቸውን ጠቅሰው ተቃውመዋል፤ የሰማርያው ጠንቋዩ ሲሞን (ሐዋ.8፥9)፣ ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ[እስክንድሮስ የተባለው ምናልባት የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ ሊኾን ይችላል (2ጢሞ.4፥14)] (1ጢሞ.1፥20)፣ ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ (2ጢሞ.2፥17)፣ ዴማስ(2ጢሞ.4፥10)፣ ዋናቸው ሊሆን የሚወድ ዲዮጥራጢስ (3ዮሐ.9) እና ሌሎችንም “ሐዋርያት ነን የሚሉቱን መርምረው ሐሰተኞች ሆነው ባገኟቸው” ጊዜ እንደለዩዋቸው ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክርልናል፤ (ራእ.2፥2)፡፡

   በኋለኛውም በቤተ ክርስቲያን አባቶች ዘመን፣ ቤተ ክርስቲያን የተነሡባትን የኑፋቄ ትምህርቶች እንደጉባኤ ኒቂያ፣ ቁስጥንጥንያ፣ ኤፌሶንና ሌሎችንም ጉባኤያትን በመሥራት ከኢቦናውያን እስከ ግኖስቲካውያን፣ ከሲሞን መሠርይ እስከ አርዮስ፣ መቅዶንዮስ፣ አቡሊናርዮስ፣ አውጣኪ፣ ንስጥሮስ፣ ቫሲለደስ፣ መርቅያን … ድረስ ያሉትን መናፍቃንን በየዘመኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መዝና ትቃወም፤ አልመለስ ያሉትንም አውግዛ ከመካከሏ ትለይ[ለሰይጣን አሳልፋ ትሰጥ (1ቆሮ.5፥5)] እንደነበር ታሪክ ምስክራችን ነው፡፡

Monday 6 November 2017

አመናፋሹ!



እንዳልተበጃጀ፣ በእግዜር ምስያ
እንዳልተፈጠረ፣ በመልኩ በአርዓያ
ራሱን ጫፍ ላይ ሰቅሎ፣ ሥጋውን አግንኖ
አስገኚ ነኝ አለ፣ አስገኚን ኮንኖ፡፡

ሚስቱን በቀኝ ክንዱ፣ ታቅፎ እየሳመ
እየበላ እየጠጣ፣ የላመ የጣመ
ቃሉን አመንፍሶ፣ እኔው መንፈስ አለ ...

Wednesday 1 November 2017

ልዩውን ወንጌል በወንድማማችነት ስም አለመቃወም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም!

   ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ስለማመንና ወንጌልን ስለማገልገል በሚገጥመን ነገር፣ “ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም” (ማቴ.10፥37) በማለት በግልጥ አስተምሯል፡፡ በመንፈሳዊው ዓለም ጌታችን ክርስቶስና የክርስቶስ ትምህርት ዋናና ዘወትር የቀዳሚነት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ነገር ነው፡፡ በዓለም ላይ ከትዳር፣ ከቤተሰብ፣ ከልጅ፣ ከአባት፣ ከእናት፣ ከባልንጀራ፣ ከወዳጅ፣ ከሃይማኖት አባት፣ ከሰባኪ፣ ከዘማሪ፣ ከመጋቢና ከቄሱም … ከማናቸውንም ሰውና ነገር ይልቅ ጌታችን ክርስቶስ ዋናና ተከታይ የሌለው ነው፡፡
   የክርስቶስ ዋናነት በትምህርታችን፣ በሕይወታችን፣ በመንገዳችን፣ በመውጣት በመግባታችን፣ በኹለንተናችን ጭምር ነው፡፡ በዓውደ ምሕረትም፤ ከዓውደ ምሕረት ስንወርድም፣ ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነትም ኾነ ለብቻችን በመንገዳችን ኹሉ ክርስቶስ ዋናና አይነኬ የክርስትናችን መሠረትና ማንንም የማናስነካው ዓይነ ብሌናችን ነው፡፡ ቅዱሱ መድኃኒታችን ክርስቶስ በቅድስና የምንኖርለት ብቻ አይደለም፣ የምንሞትለትም ጌታችን ነው፡፡ በማናቸውም መንገዳችን ክርስቶስንና ትምህርቱን ለድርድርና ለአማራጭ አናቀርበውም፤ አናስነካውምም፡፡