Friday 27 November 2015

ወንድሜ ማን ነው? (ክፍል አንድ)

    
        Please read in PDF

  ይህን ጽሁፍ ከመጻፌ በፊት ለብዙ ሰዓታት ውስጤ ከገለባ ይልቅ እስኪቀልብኝ ድረስ “አስቀድሞ ነገር፥ እኔ ራሴ ለሌላው በተለይም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎቼ ወንድም መሆን እችላለሁኝ?” ብዬ ከራሴ ጋር ተሟግቻለሁኝ፡፡ ምናልባት ጥያቄው ያን ያህል ከባድ ላይመስል ይችላል ፤ ይህን ጥያቄ ይዘን ወደታላቁ መጽሐፍ ሚዛንነት የተጠጋንና ራሳችንንም በታላቁ መጽሐፍ ሚዛንነት ያየን እንደሆን ግን እጅግ የሚስቡና እይታችንን የሚያጠሩ እውነቶችን እናስተውላለን፡፡
      “ወንድም” የሚለውን ቃል ታላቁ መጽሐፍ ሲፈታው፥ ከአንድ እናትና አባት የሚወለዱትን ብቻ ሳይሆን የአንድ አገር ተወላጆችን (ዘጸ.2፥11 ፤ ሐዋ.7፥23-26) ፤ ከጥብቅ ወዳጅነት የተነሳ እጅግ የተቀራረቡትን (2ሳሙ.1፥26-27) ፤ ከቅርብ ዘመድ የተነሳ የተወዳጁትን (ዘፍ.36፥10 ፤ ዘኊል.20፥14 ፤ ሮሜ.9፥3) ፤ በቃል ኪዳንም (1ነገ.5፥1 ፤ 12) ወንድማማችነት እንዳለ ይነግረናል፡፡ ወንድማማችነት ምንም እንኳ መሠረቱ በደም መወለድ ቢሆንም፥ ከዚሁ ጋር ሊተካከል በሚችል መልኩ ደግሞ ታላቁ መጽሐፍ በአላማ የተሳሰሩትን እኩል አስተካክሎ ያስቀምጣል፡፡

Monday 23 November 2015

ግድ የለም ታገሰው



ጌታ …
ዝም ያለ ሲመስል
በጆሮ እንዳልሠማ
በአይኑም እንዳላየ
                        ቀና ቀና ይላል
                        የመከራው መከር
                        ጭንቅ እያበራየ

Monday 16 November 2015

ድንግል ማርያም በድንግል ማርያም አንደበት (ክፍል ስድስት)




5.  እግዚአብሔርፍርድያደላድላል

“ … ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል ፤ ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል ፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል” (ሉቃ.1፥51-52)

    ብዙዎቻችን የክፉዎችን ክፋት አይተን፥ ለእግዚአብሔር ከማሳሰብና በፊቱ ጥቂት ከመታገስ ካለመቻልም በላይ፥ በብዙ ማጉረምረም የተጠመድን ነን ፤ በውጪው አለም የሚኖሩ እልፍ አዕላፍ ዲያስፖራዎቻችንና አገር ቤትም ያሉ ጥቂት የማይባሉ ወገኖች መንግሥት በመክሰስ የተጠመዱ ናቸው፡፡ አንድ ነገር እንደአማኝ እጅግ አምናለሁ ፥ መንግሥት ያጥፋም ፤ አያጥፋም ከሁሉ በፊት ጸሎት እንደሚገባው (1ጢሞ.2፥1-2) ፤ የሚያጠፋ ከሆነም ደግሞ በአገባቡ ሊመከር ፣ ሊወቀስ  ፣ ሊገሰጽ እንዲገባው አምናለሁ፡፡ ይህን ሳያደርጉ ከመሬት ተነስቶ ቱግ ማለት ከድንግል ማርያም የምስጋና ቃል አለመማር ነው፡፡ 

Tuesday 10 November 2015

ከፍቶታል በሩን






የሴቲቱ ዘር፥ የእባቡን ራስ ʼሚቀጠቅጠቀው፤
የአብርሃም ዘር፥ የምድርን ነገድ የሚባርከው፤
ከዳዊት ወገብ፥ በትር የሚሆነው ለምለም ቁጥቋጦ፤

Wednesday 4 November 2015

ጣሊያናዊው የደብር አለቃና - የተከሰሰበት ግብረ ሰዶማዊነቱ




 Please read in PDF

       ስለተከሰሱ ሰዎች መብት የኢትዮጲያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ሕገ መንግሥት “በፍርድ ሂደት ባሉበት ጊዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደጥፋተኛ ያለመቆጠር ፥ መብት አላቸው፡፡” በማለት ይገልጣል፡፡ (ሕ/መን.አን.20(3)) ነገር ግን “ሕጻናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች በሚወሰዱበት ጊዜ በመንግሥታዊ ፥ ወይም በግል የበጎ አድራጎት ተቋሞች ባለ ሥልጣኖች ወይም በሕግ አውጪ አካላት፥ የሕጻናት ደህንነት በቀደምትነት መታሰብ አለበት፡፡”
    በቀደምትነት መታሰብ ያለበት ብቻ ሳይሆን ፦
“ማንኛውም ሕጻን ጉልበቱን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ ፥ በትምህርቱ፥ በጤናውና በደህንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሥራዎች እንዲሠራ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ መብትም እንዳለው” በግልጥ አስቀምጧል፡፡
(ሕገ መን.አን.36(1)መ)