Saturday 29 October 2022

መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፳፩)

 Please read in PDF

የመድሎተ “ጽድቅ” ጸሐፊ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን በግልጥ በመቃወም፣ ሌሎችን መጻሕፍት ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር ለማስተካከል የሄደበትን ሩቅ መንገድና እንዲሁም ቅዱሳት መጻሕፍትን አጥምሞ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላትን እንደ ገና በመተርጐም በመጽሐፉ ውስጥ እንዴት እንዳስገባ በጥቂቱ በማሳየት፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን ያለንን ዐሳብ እንቋጫለን፤ የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣንን ከተቃወመባቸው ወይም ከሻረባቸው መንገዶች ጥቂቶቹን እናንሳ፦

1.   ያላለውን እንዳለ አድርጎ በማቅረብ፦ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን የሚቃወሙ አካላት ከሚፈጽሟቸው ግልጽ ስህተቶች አንዱ፣ የመጽሐፉን ዐውድ በመጣስ ያልተናገረውን እንደ ተናገረ አድርጐ ማቅረብ ነው። የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ በዚህ ረገድ ለምሳሌ፦

Thursday 20 October 2022

ተሐድሶ፣ በማኅበረ ቅዱሳን አደባባይ!

 

ስለ “አጥማቂ” ግርማ ወንድሙ፣ በተደጋጋሚ ጠንቋ ይነቱን፣ በመቍጠሪያ ላይ ባስደገመው ድግምት እንደሚሠራና ሰዎችን ማሳበድ እስከሚያደርስ በሽታ ላይ እንደሚጥል በተደጋጋሚ ጽፈናል፤ አስጠንቅቀናል። ነገር ግን የዚያኔ አሰምተን ጮኸን ስንናገር እኛን እንደ መና ፍቅና ሐሰተኛ እንጂ ማንም “አሜን” ብሎ ሊቀበለን የወደደ አልነበረም።

Tuesday 11 October 2022

“ባዕዱ ወንጌል 2”ና ግለ ምልከታዬ!

Please read in PDF

ባዕድ 2 - ሌላ ኢየሱስ (የሐሰተኛ አስተማሪዎች ኢየሱስ - በቅዱስ ቃሉ ሲፈተሽ) ወይም “Baed Documentary Film” የሚለውን ዘጋቢ ፊልም ተመልክቼዋለሁ። የብልጽግና ወንጌል ለእውነተኛዪይቱ ቤተ ክርስቲያን ፈተናና ከባድ ተግዳሮት ሊኾን እንደሚችል ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ አይደለም። በዚህ ረገድ እኔም የድርሻዬን ለመወጣት በ2010 ዓ.ም “የእምነት እንቅስቃሴ - የዛሬዪቱ ቤተ ክርስቲያን ፈተና” በሚል ርዕስ፣ የእንቅስቃሴውን አደገኛነትና በተለይም በተሐድሶአውያን መካከል በነበጋሻው ደሳለኝ አማካይነት ማቆጥቆጡን ተመልክቼ ተቃውሜ ጽፌአለሁ።

Friday 7 October 2022

መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፳)

Please read in PDF

ከያዝነው ርዕስ ጋር በሚስማማ መልኩ፣ የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ ሮሜ 8፥34ን ለመተርጐም በተጠቀመበት መግቢያ ላይ እንዲህ ይላል፤

“በአዲስ ኪዳን የተጻፉ መጸሕፍት ኹለት ነገሮችን ታሳቢ ማድረግ አለባቸው። መጽሐፍ ቅዱስን የምትተረጕመው ቤተ ክርስቲያን ናት። መጽሐፉ ይህ ነው ብላም ለይታ፤ ሰፍራ፤ ቈጥራ የሰጠችውም ቤተ ክርስቲያን ናት። ቤተ ክርስቲያን ናት መጽሐፍ ቅዱስን የሠራችው እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን አልሠራም።”[1]

እንግዲህ አስቀድመን እንደ ተናገርን፣ ይህ የ“መድሎተ ጽድቅ” አቋም ወይም አስተምኅሮ የካቶሊክ እንጂ የኦርቶዶክሳውያን አቋም አይደለም። ጸሐፊው ግን የካቶሊክን አስተምኅሮና እምነት በግልጥ እንደ ኦርቶዶክስ አስተምኅሮ ሲያቀርብ እንመለከተዋለን። ይህን ግልጥ መስመር መለየት ባልቻለበት ኹኔታ፣ ማለትም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥልጣንን ከቤተ ክርስቲያን አሳንሶ ማቅረብ፣ መድሎተ ስሑትነቱን  በግልጥ ያሳያል።

Sunday 2 October 2022

አእመረ አሸብርና ብልጠታዊ ቋንቋው!

 Please read in PDF

አእመረ አሸብር፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቲቪ ላይ ያደረገውን የክፍል አንዱን ቃለ መጠይቁን አድምጬዋለሁ። እጅግ ሊደንቀኝ በሚችል መልኩ፣ ቃለ መጠይቁን ያደረገው ሰው ደጋግሞ ላነሳቸው ግልጽ ጥያቄ አእመረ አለመመለሱ ሳይኾን፣ ጠያቂው ጨርሶ ለማመን አለመቻሉ፣ ከአእመረ ይልቅ ጠያቂውን እንዳምነው ግድ ብሎኛል።