Monday 1 April 2024

እባክህን ማረን !

 Please read in PDF

አገር ትድኻለች በረሃብ እንፉቅቅ

ትውልድ ይራኮታል በዋይታና በጭንቅ

ድኻ ፍትሕ ጎድሎት እንባ እየረጨ

መኖር ምሬት ኾኖ ተስፋ እየተቀጨ

አረርን ከሰልን ተኮማትረን ቀረን

መጻጉ'ን የፈወስክ እባክህን ማረን፡፡

 

እባክህን ማረን ከመጉበጥ እንቅና

ተብረክርከን አንቅር በኃይሉ እንጽናና

ቁስላችንም ይሻር በብርቱ እንጽናና

ዓመጽ ዕድሜው ይጠር ሰንኮፉ ይነቀል

የዘረኝነት ግንድ ይቆረጥ ይመንገል

መጨካከን ይውደም ጥላቻ ይከንበል

ማረን በምሕረትህ ሞት ይደንግጥ ዛሬ

መጻጉ'ነት ይብቃ አትጋን በዝማሬ! 

1 comment:

  1. ሁሉ በእርሱ ከእርሱ ነውና ክብር ሁሉ ለእርሱ ይሁን!!

    ReplyDelete