Monday 30 December 2013

የኢየሱስ ደም - ክፍል አራት


Please read in PDF
                                                                             
የኢየሱስ ደም አገልግሎት

                     “ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻ”(1ዮሐ.1፥9)

                     “በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን የሚታይ”(ዕብ.9፥24)

                    “በቅዱስ ደሙ ኃጢአታችንን የሻረ”(ትምህርተ ኅቡዐት)

                   “መዓዛው የጣፈጠ ንጹህ መስዋዕት”(ቅዱስ ቄርሎስ)

      ፊተኛው የደም አገልግሎት ኃጢአትን ከመቀነስ ይልቅ እየጨመረ፣ ከማንጻት ይልቅ እያዳፈነ የኃጢአት ፍህም በየማለዳው አዲስ እየሆነ ምድርን በእድፈትና በርኩሰት ስላካለለ ኢየሱስ ከዕድፈትና ከርኩሰት፣ ከፊት መጨማደድም ንጹህ የሆነች (ኤፌ.5፥27) ቤተ  ክርስቲያንን ያዘጋጅና ይሞሽር ዘንድ ወደደ፡፡ ስለዚህም በገዛ ደሙ የዋጃትንና ያነጻትን ቤተ ክርስቲያን እርሱ በገዛ ፈቃዱ መሠረተልን፤ (ሐዋ.20፥28)፡፡

Thursday 26 December 2013

የክብር ፍጻሜው

እስኪ አትቸኩል ኤልያብ አልሆነም
የእግዚአብሔር ሞገስ ዘለግታ አይደለም
ዳዊት ነው በሞገስ ሊቆም የሚቻለው
ጌታ ሊያድርበት ወዶ የፈቀደው
የእንጨት ስራ አይደለም መቅደሱ ልብ ነው።

Monday 23 December 2013

የኢየሱስ ደም - ክፍል ሦስት

                           Please read in PDF :- yeEyesus dem 3

     ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሰርቶ በጨረሰ ጊዜ “ሀያ ሁለት ሺህ በሬዎችና መቶ ሐያ ሺህ በጎች ሠዋ” ይለናል ታላቁ መጽሐፍ፡፡ (2ዜና.7÷5)፡፡በአንድ ቀን እንዲህ ያለ መስዋዕት ከቶውንም በብሉይ ኪዳን ውስጥ ቀርቦ አያውቅም፡፡ሀያ ሁለት ሺህ በሬና መቶ ሐያ ሺህ በጎች በአንድ ቀን!!! አስተውሉ! ከአንድ እስከሀያ ሁለት ሺህ  ቁጠሩና እንደገና ከአንድ እስከመቶ ሐያ ሺህ ጊዜ ቁጠሩ!!! ቁጥር ብቻ ግን አይደለም የሚፈሰውንም የደም ብዛት እዩ! ከዚያ እናንተ በሰሎሞን ቦታ ቁሙ! ምን ያህል ደም በፊታችሁ እንዳለ አስተውሉ!!! የክርስቶስ ደም እንዲህ ነው ከኃጢአት ሁሉ የጋረደንና ለክብሩ የሰወረን!!!
    ሰሎሞንን የመስዋዕቱ ደም ከድኖታል ፤ሰሎሞን የተኛው ሙሉ ለሙሉ በደም እንደተጋረደና በደም እንደተሸፈነ ነው፡፡እንዲህ ሆኖ ተኝቶ ሳለ ጌታ እግዚአብሔር በሌሊት ለሰሎሞን ተገለጠለት፡፡ልዩ ኪዳንም ገባለት፡፡(2ዜና.7÷11-22)፡፡የሚገርመው ግን ይህ ሁሉ መስዋዕት በቀን እየቀረበ እንኳ ፍጽምትና ቅድስት ፣አዲስና ህያው የሆነችውን መንገድ ከኢየሱስ በቀር መርቆ መክፈት የተቻለው አልነበረም፡፡ ምክንያቱም  እነዚህ ሁሉ መስዋዕቶች ፦
የሰውን ዋጋ ስለማይተካከሉ(ማር.8÷37፤ዕብ.÷10÷1)
ጊዜያዊ መፍትሔ እንጂ ኃጢአትን የማያስወግዱና ፍጹም ድህነትን(ድነትን) የማያሰጡ ስለሆኑ(ዕብ.9÷9፤10÷1)
መስዋዕቶቹ በራሳቸው ፍጹማን ስላልሆኑ
እስከመታደስ ዘመን ብቻ በምሳሌነት አገለገሉ፡፡(ዕብ.9÷9)፡፡ስለዚህም ሰው ልዩና ታላቅ ቤዛ ከኃጢአቱም ነጻ የሚያወጣው ሊቀ ካህን የሆነ ቤዛ አስፈለገው፡፡


                        ክህነቱ የማይለወጥ ዐቢይ ሊቀ ካህናት(ዕብ.7÷25)

    የብሉዩ ሊቀ ካህን ዋና አገልግሎቱ ስለህዝቡ ህዝቡን ተገብቶ ስለኃጢአት ይቅርታ ደምን በእግዚአብሔር ፊት ይዞ መቅረብና መማለድ ነው፡፡ነገር ግን ይህ የሊቀ ካህኑ አገልግሎት ምንም እንኳ ህጉ ንጹህ ቢሆንም (ሮሜ.7÷12) እርሱ ራሱ በኃጢአት የተያዘ (ዕብ.5÷3)፣ሞት የሚከለክለውም ስለሆነ (ዕብ.7÷23) የሚያቀርበው የእንሰሳቱም ደም ፍጹም የሆነ የኃጢአትን ሥርየት ሊያስገኝ አልተቻለውም፡፡ ስለዚህም እርሱ ራሱ በኃጢአት ያልተያዘ ፣ቅዱስና ነቀፋ የሌለበት ንጹህና ከኃጢአተኞች የተለየ (ዕብ.6÷26) ሞት የማይይዘውና ለዘለዓለም በህይወት የሚኖር ዐቢይ ሊቀ ካህናት ይገባናል (ያስፈልገናል)፡፡

Thursday 19 December 2013

ቀን ሳለ ተመለስ

መቅረዝ ዕድሜህ ፈክቶ
እንደበር ተከፍቶ
ህመምህ ርቆ
መቆምህም ፀድቆ
ዳፍንት ሳይመጣ
ቀኑ ሳይሆን ማታ፤


Sunday 15 December 2013

የኢየሱስ ደሙ (ክፍል ሁለት)

Please read in PDf
                                                           የእንሰሳቱ ደም
     
               “የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን እንዲያስወግድ የማይቻል ነውና፤”(ዕብ.104)
   
       አለም ገና በኃጢአት ተይዛ ሳለ፥ ጌታ እግዚአብሔር ዋናው አካል እስኪገለጥ ምሳሌውን በማገልገል ጊዜያዊ ድኅነት(የማሥተሰርያ ሥርዐት) እንዲሰጡ ሌዋውያን አገልጋዮችን አስነሳ፡፡ ብሉይ ኪዳን በጊዜው ይሠራ ለነበረ ኃጢአት የማሥተሰርያ ሥርዐት አድርጎ ያቆመው፥ የእንሰሳትንና የአዕዋፋትን ደም ነው፡፡ በመሠዊያው ላይ የሚፈሰው የመሥዋዕቱ ደምየተቀደሰደም ነው፤ (ዘሌዋ.1710-14 ፤ ዘዳ.1223)፡፡ ምንም እንኳ በመሠዊያው ላይ የሚፈሰው የመሥዋዕቱ ደምየተቀደሰቢሆንም፥ በእግዚአብሔር አምሳልና መልክ ለተፈጠረው የሰው ልጅ  ፍጽምናና ብቃት ያለው መድኃኒት አልነበረም፡፡

      ዳሩ ግን አገልግሎት በምሳሌነት ሲገለገል ብርቱ ጥንቃቄ ነበረው፡፡ ሕይወት የተቀደሰና ክቡር በመሆኑ፥ የሕይወት ቤዛ ምሳሌ የሆነውን ደም በክብር መያዝ እንጂ፥ መግደልና መብላት ፈጽሞ የተከለከለ ሆነ፤ (ዘፍ.95 ፤ ዘኊ.3533 1ሳሙ.1432)፡፡  እግዚአብሔር በአሮጌው የመታረቂያ መንገድ፥ አንድን ኃጢአተኛ ይቅር ለማለት በእርሱ ፈንታ የሞተውንና የሚፈሰውን የእንሰሳውን ደም ያያል፡፡ ኃጢአተኛው ስለፈጸመው ኃጢአት የመስዋዕት ደም ሲፈስ በእርሱ ፈንታ ሌላ እንደሞተ፤ ኃጢአቱም በደሙ እንደተሠረየ ያመለክታል፤ (ዘሌ.517-19) ኃጢአተኛው የሚያቀርበው እንሰሳ ንጹህና እንከን የሌለበትን ነው፤ (ዘሌ.111)በተለይ ጠቦትና ገና የሚያሳሳ ዕድሜ ላይ ያለው እንሰሳ ለመሥዋዕትነት ይቀርባል፡፡

Thursday 12 December 2013

የኢየሱስ ደም (ክፍል አንድ)

ቅዱስ እግዚአብሔር በበጎ ፈቃዱና ከታላቅ ባዕለጠግነቱ የተነሳ ሰውን ፍጹምና ቅዱስ አድርጎ ከመፍጠሩ በፊት የተፈጠረው ክቡር ፍጡር በገዛ ፈቃዱ ወድቆ እንደሚረክስ በባህርይ እውቀቱ አወቀ፡፡ስለዚህም የሚፈጥረውን ውድ ፍጥረት አብ በልብ እንዳሰበ በወልድ ህያው ቃልነት ሲፈጥረው፤ መጥቶ እንደሚያድነውና እንደሚዋጀው ኪዳንን ገባ፡፡ይስሐቅ በአብርሐም ህሊና ቀድሞ እንደታረደ ወልድም በአብ ህሊና ቀድሞ የታረደ ሆኖ በበጉ ያመኑትና የዳኑት ቀድሞ ስሞቻቸው በህይወት መዝገብ ተጻፈ፤መንፈስ ቅዱስ ይህን እውነት ቀድሞ ለተወሰኑ ምርጦች በብሉይ ኪዳን ኋላም ለሐዲስ ኪዳን አማኞች ናኘው፡፡
  አቡቀለምሲሱ(ባለራዕዩ) ዮሐንስ “ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ህይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል፡፡”(ራዕ.13÷8) ባለው ቃሉ የአብ አንድ ልጁ ለዓለሙ ኀጢአት የታረደ ሆኖ የታየውና ኪዳኑ የተወሰነው ገና አሮጌው ኪዳን ሳይመጣ እንደሆነ “ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ህይወት…” በማለት ይነግረናል፡፡እግዚአብሔር ከዘመን በፊት ፍጥረት እንዲድን እንጂ እንዲጠፋ አልወደደም፤ስለዚህም እንደእግዚአብሔርነቱ ራሱን ፣እንደእኛም ከእኛ በተለየ አካሉ ኢየሱስ ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሳው ሥጋ እኛን ወክሎ ከፍጥረት በፊት ልዩ ኪዳኑን ሰጠን(ገባልን)፡፡ቅዱስ ሐዋርያ ጴጥሮስም ከፍጥረት በፊት ሰውን ለማዳን ክርስቶስ ቤዛ እንዲሆን በእግዚአብሔር(አብ) የተመረጠ መሆኑ የታወቀና የተረዳ መሆኑን በመልዕክቱ ገልጧል፡፡ (1ጴጥ.1÷20)
     የዚህ ቁርጥ ውሳኔ ዋና አላማ የሰው ልጅ በኀጢአት መውደቅና መርከስ፣ያለአድራሻው በሞት ኩነኔና፣ በዘላለም ፍርድ መያዙ ስለሆነ ከዚህ የሚቤዠውና የሚያድነው አንዳች ሌላ አዳኝ ስላልተገኘና ስለሌለም  ነው፡፡
                   

                                ኃጢአትና ኃጢአተኝነት


        የመስዋዕት ደም ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት ስለኃጢአት ነው፡፡“ኃጢአት” የሚለውን ቃል የአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ሲፈታው “በቁሙ በደል፣ዐመጥ፣ግፍ፣ህገ ወጥ ሥራ በኃልዮና በነቢብ በገቢር የሚሰራ፣ ፅድቅን መቃወም … ” ነው ሲል በሌላ ትርጉምም “ማጣት፣መቃጣት፣ዕጦት፣ችግር፣ሽሽት ፣ኩብለላ፡፡” በማለት ተርጉመውታል፡፡(ኪዳነ ወልድ ክፍሌ/አለቃ/፤መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፤1948 ዓ.ም፤አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፤ገጽ 474፡፡)

Tuesday 10 December 2013

ይህስ ከመናፍቅነት ያንሳልን?


Please read in PDF

 በአጭር ቃል በእኛ መካከል ዝሙት እንዳለ ይታወቃል፡፡ኃጢአት ከእግዚአብሔር መንግስት እንደሚያወጣ ለድርድር በማይቀርብበት በሐዲሱ ኪዳን ዘመን እንደነውር እንኳ ሳይቆጠር ዝሙት በመካከላችን አብቦ ፈክቷል፡፤መናፍቅነትን ሊያወግዝ ደቦ የሚጠራ ህብረታችን ዝሙትን ለማውገዝና እንደመናፍቅነት ያለ ኃጢአት ነው ለማለት ድፍረቱ የተሰለበብን ይመስላል፡፡
    ቤተ ክርስቲያንን በጥፋታቸውና በአሰቃቂነታቸው ወደር ያልተገኘላቸው አላውያን ነገስታት ፈጽሞ ከክርስቶስ ሊለይዋት አልቻሉም፤ነገር ግን የገዛ ኃጢአቷ ፈጽሞ ከጌታዋና ከሙሽራዋ ኢየሱስ ይለያታል፡፡ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በከባድ ተግሳጽ ከተወቀሰችበት ኃጢአት አንዱና ትልቁ ባላመኑ አህዛብ ዘንድ እንኳ ያልተሰማ አዲስ ነውር በክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መሰማቱና መታየቱ ነው፡፡ፍጥረታዊውና እንሰሳዊ ማንነታችን ውስጣችንን ሲገዛ በአደባባይ ለመፈጸም ከማናፍርባቸው ኃጢአቶች አንዱ ዝሙት ነው፡፡
       ፍጥረታዊ ሰው ለነውሩ ዳርና ድንበር የለውም፡፡በእግዚአብሔር አደባባይ ከመናገር እስከማድረግ እንኳ ፊቱን አይመልስም፡፡የተገለጠ ኃጢአቱን ሲናገረው እንደጀብዱነትና ዕውቀትም ያወራዋል፡፡ዝሙቱ በግልጥ ታውቆ በቤተ ክርስቲያን መካከል ይመላለስ ለነበረው ቆሮንቶሳዊ ታላቁ ልከኛ ሐዋርያ ፦ ከቅድስቲቱ ህብረትና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያስተላለፈው ውሳኔ የዛሬዎቹን አብያተ ክርስቲያናት በግልጥ የሚዘልፍ ነው፡፡በማናኛውም ሰው ላይ አብያተ ክርስቲያናት የሚያስተላልፉት የውግዘት (ከማህበረ ምዕመናን መለየት)ውሳኔ እንደቅዱስ ጳውሎስ ካልሆነ ውግዘታቸው ከቡድንና ከግለሰብ ሐሳብ የመነጨ ጥላቻ እንጂ የመንፈስ ቅዱስ ሐሳብ አይሆንም፡፡እንኳን በበደለ በአንድ ምዕመን በአገልጋዮች ላይ እየተወሰደ ያለው የዛሬው “ውግዘት” ግን እጅጉን የሚያሳዝን ነው፡፡
       ወደቀደመ ነገር ስንመለስ በሐገራችን በደቡብ ባለ አንድ “ታላቅ” ገዳም ውስጥ በኮሚቴነት  በሚያገለግል አንድ ሰው “ሆቴል” ቤት ውስጥ ዕድሜያቸው አስራ ስምንት አመት የማይመሉ እህቶች ለዝሙት ከመማገዳቸው ባለፈ እርቃን ጭፈራና የህብረት ዝሙት እንደሚፈጸም ጠራራ ፀሐይ ያስተዋለው እውነት ነው፡፡ግና ዛሬም ይኸው ሰው ለቤተ ክርስቲያን “ቆሜያለው” ከሚል ማህበር ጋር “በቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያንን እየመሩ” አሉ፡፡
      ሌላ የነውር ምሳሌ፦በምስራቅ ሐገራችን “በታወቀ” አንድ ገዳም “ድንግልናን ማስወሰድ” እንደታላቅ ስዕለት ይቆጠራል፡፡በአይኔ በቦታው ተገኝቼ እንዳየሁት ስዕለቱን ለማስፈጸም የሚቆሙ አመንዝራ ወንዶች በአከባቢው የክብረ በዓሉ ዕለት ጥግ ጥግ ይዘው “ባዕለስዕለትን” ሲጠይቁ የማፈር እንግዳ ጠባይ ፈጽሞ አይታይባቸውም፡፡ ይህ እየሆነ ያለው በአውሮፓ ወይም በአሜሪካ በሚገኝ አንድ ቤተ እምነት ውስጥ አይደለም፤እዚሁ “ቅድስት የክርስቲያን ደሴት” ብለን በምንሸልልባት ኢትዮጲያ ውስጥ ነው፡፡ምናልባት ይህን በአዋጅ ቤተ ክርስቲያን አልፈቀደችም ብለው የሚሟገቱ እንዳሉ አምናለሁ፤እውነት ነው ቤተ ክርስቲያን አልፈቀደችም፣አትፈቅድም፡፡


Saturday 7 December 2013

ጸሎት- ከራስ መልካምነት ታደገኝ!

 Please read in PDF

     አቤቱ የጽድቄ አምላክ ሆይ በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ ፣ወዴት ነህ? ባልኩህ ጊዜም ተገኝልኝ፡፡ የተጠጋሁብህ አምባዬ የተጠለልኩብህ ታዛዬ ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ ለባርያህ መንገድህን እከተልህ፣ አብሬህም አድር ዘንድ አሳየኝ፡፡
          ጌታዬ ሆይ ዛሬም በመቅበዝበዝ ተይዣለሁ፡፡ እንደሰካራም አንተን እንኳ ቀምሼ መሄድ ያምረኛልና እባክህን ወደልቤ መልሰኝ፡፡ አንተን መከተል ማለት ህይወትን መከተል ማለት እንደሆነ ይህን አንድ እውነት ለልቤ ግለጥልኝ፡፡ አውቀዋለሁ፣ ባትነግሩኝም ባላነበውም ይገባኛል ከሚል አይቶ ማንበብን ሰምቶ ማስተዋልን ከሚጠላ ጋኔን ባርያህን ጠብቀኝ፡፡ አንተን አምኜ በተረዳሁበት እምነት አጽናኝ፡፡

Wednesday 4 December 2013

ብቻውን እናምልክ

በጸናች ክንዱ
በተዘረጋች እጁ
በድንቅ እየሠራ
ምሪት እየመራ
ያዳናቸውን ቃል የዕሪታቸውን መልስ
ኪዳኑን ሲረሱ ልባቸውም ሲረክስ
የአርባ ቀን ቆይታ ትዕግስት ነስቷቸው
ያወጣን ያዳነን ሙሴ ቀረ ብለው

Friday 29 November 2013

ሩጫውን ወይስ ሩጫዬን ጨርሻለሁ?

በመጽሐፍ ቅዱስ ካልተጻፉ ነገር ግን እንደተጻፉ ተደርገው በየመድረኩ ከሚጠቀሱልን ጥቅሶች መካከል አንዱና ዋናው ጥቅስ ቅዱስ ጳውሎስ ለቅዱስ ጢሞቴዎስ የጻፈው “መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋ ጅቶልኛል፥ …” (2ጢሞ.4÷7) የሚለው ቃል ነው፡፡
      ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በህይወት ዘመናቸው በዙርያቸው ካሉትና ከሩቁ ብዙ ስድብ ፣ነቀፌታንና ትችትን የጠገቡ አባት ናቸው፡፡እንዳለመታደል እነዚያ ይጠሏቸውና በድብቅ በስድብ ይዘምቱባቸው የነበሩት ሰዎች ቅዱስ ፓትርያርኩ በቁም ሳሉ ያልተናገሩትን ሲሞቱ ቁጣቸውን፣ ተግሳጻቸውን፣ ምክራቸውን ወጣ ወጣ ሲያደርጉ አይተናል፡፡ (በእርግጥ እሳቸውም ሰው ናቸውና ይደክማሉ፤ደክመውም ይዝላሉ፡፡ ስህተት አይቶ ከመርገም፦ እንዲመለሱ ፣እንዲታነጹ ያኔውኑ ነበር በግልጥ መግለጡ … ሳይመክሩና መንገድ ሳያሳዩ ቁጣ እንዴት ያለ ስንፍና ነው?) ወደሐሳቤ ልመለስ፡፡
      እሳቸው ባረፉ ሳምንት በ“ታላቁ” የአራት ኪሎው የሥላሴ ካቴድራል ላይ የተለጠፈው “ትልቅ ስቲከር” እንዲህ ይላል፦    
             “መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫዬን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን
              ጠብቄአለሁ፤ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥” (2ጢሞ.4÷7)፡፡

ምናልባት እሳቸው ናቸው የጻፉት ወይም የፊደል ግድፈት ነው እንዳንል በየትኛውም ቤተ ክርስቲያን ጀርባ ዘወር ብላችሁ የተጻፉ የመቃብር ላይ የዚህን ክፍል ጽህፈቶች ብትመለከቱ ተመሳሳዩን ለማየት አትቸገሩም፡፡ እንደውም አንዳንዶቹ “ሃይማኖትን ጠብቄያለሁ” የሚለውን ቃል ጭምር “ሃይማኖቴን ጠብቄያለሁ” ሲሉም ይደመጣሉ፡፡ (የእኔ ብቻ ለማለት ይሆን ክርስትናውን?)
      ይህን ተመልክተን በመጨረሻ የምንደርስበት ድምዳሜ ከታላቁ እስከታናሹ ፣ከሰባኪው እስከተሰባኪው … ቃሉን በህይወት ከመተርጎም ባሻገር በንባቡ እንኳ ያለማስተዋል ከባድ ችግር እንዳለብን ነው፡፡
       ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የመንፈስ ልጁ ቅዱስ ጢሞቴዎስን በብዙ ምስክር ፊት የሰማውን ቃል እንዲመሰክርና መከራን በመቀበል ከሙታን የተነሳውን፣ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን በማሰብ በትጋት እንዲያገለግል ሊመክረው ከተጠቀመበት ምሳሌዎች አንዱ ሩጫ ነው፡፡(1ጢሞ.2÷2-8)፡፡

Tuesday 26 November 2013

ሳይሰሙ መጋል

     ከሸክላ ምጣድ ጠባያት አንዱ ሳይሰማ አለመጋሉ ነው፤ መስማት (መሞቅ) የክርስቲያን ልዩ ጠባዩ ነው፡፡ በክርስትና መቀዝቀዝ አይቻልም፤ ዳግመኛ ወደኃጢአት ቆፈን ወደባርነት እንድንገባ አልተፈቀደልንም፤ (ገላ.5፥1)፡፡ ለማንም የማይመች ለብታም አይሆንልንም፤ ወይ በአግባቡ መስማት (መሞቅ) ወይም ደግሞ ቀዝቅዞ በገዛ እጅ ራስን ከእግዚአብሔር መለየት፡፡ ከብርሐንና ከጨለማ አንዱን መምረጥ እንጂ ሌላ ሦስተኛ ምርጫ አልነበረም፤ አይኖርምም፡፡
      በአንድ ወቅት እንዲህ ሆነ ይባላል፥ ሦስት እንደሰሙ የሚግሉ ሰዎች ነበሩ፡፡ ስለምናኔ ሲነገር መናኝ፣ ስለቅዱስ ጋብቻ ሲነገር ማግባት፣ ስለሰባኪ ሲነገራቸው ሰባኪመሆን የሚያምራቸው በተጣዱበት ሁሉ የሚሰሙ ነበሩ፤ በመጨረሻም መናኝ መሆን አማራቸውና፥ እንደተነገራቸው ሽንብራ ይዘው ወደገዳም ገቡ፡፡ ከብዙ ጾምና ጸሎት ጋር በቀን በሥላሴ ምሳሌነት ሦስት ፍሬ ሽንብራ ሊበሉ ወሰኑ፤ ነገር ግን አልቻሉም፡፡ በሚቀጥለው ቀን በስድስቱ ቃላተ ወንጌል ምሳሌ አሉና፥ ስድስት ስድስት ፍሬ ቢበሉም አልቻሉም፤ በሚቀጥለው ቀን በአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት፣ ቀጥሎም በሐያ አራቱ ካህናተ ሰማይ እንዲህ እያሉ ቢሄዱም ስላልተቻላቸው፥ በመጨረሻ በእልፍ አዕላፋት መላዕክት ብለው የያዙትን ጨርሰው ወደቤታቸው ተመለሱ ይባላል፡፡

Friday 22 November 2013

የእግዚአብሔር ትራፊ

ከግምት ከበዛው ከማይቆጠረው
ከተትረፈረፈው ጨብጠን ከያዝነው
ከአምስቱ አሳና ከሁለቱ እንጀራ
አለን ከምንለው ከኛ ብዙ ዝና
ይደንቀኛል ይገርመኛል የአምላኬ ሥራ!!

Tuesday 19 November 2013

ነፍሴ አንተን ብቻ



ወንድሜን አሳዳጅ ቃየላዊ እብደቴ፣
ጥርጥር የሚነዳው ዲዲሞስነቴ፣
ኬፋዊ ግርግር ችኩል የሚያሮጠው
ሄሮድሳዊ መርገም የህፃን ደም 'ሚጥመው፣

Sunday 17 November 2013

" 'ከወይን እሾህ' ይለቀማልን?"(ማቴ.7÷16)


ከወራት በፊት  አንድ አሁንም በህይወት ያሉ ሊቀ ጳጳስ ኤርትራ ካለው "የተቃዋሚ ጦር ቀጠና" በመገኘት ኢትዮጲያን እንዲወጉ መድፍና ታንኩን መትረየስና ቦንቡን "ባርከው"መመለሳቸውን ሰምተን ነበር፡፡(ይታያችሁ አሁንም ሊቀጳጳስ ሆነው አሉ!? "የሚረግሟችሁን መርቁ" የሚለውን ቃሉን ያስተምሩ ይሆን?!!)፡፡ሰሞኑን ደግሞ ሳውዲ አረቢያ ከዜጎቿ ውጪ ባሉ የውጪ ነዋሪዎቿ ላይ በወሰደችው እርምጃ ከሐገር ቤት ከአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት አንገት የሚያስደፋ ከአንድ ክርስቲያን ማህበረሰብ የማይጠበቅ ጸሎት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካባ አልብሰው  ሲሉና "ምላሹም እንደተገኘ" ሲናገሩ ሰምቼ ተክኜ በመንፈሴ ተበሳጭቻለሁ፡፡(ይታያችሁ ሶማሊያ፣ሳውዲ አረቢያ፣ፊሊፒንስ፣…. ከሰሞኑ በከባድ የጎርፍ አደጋ ተመተዋል፡፡ሳውዲ አረቢያ በእኛ ጸሎት እንዲህ ከሆነች ሌሎቹን "መአተኛው" እግዚአብሔር በማን ጸሎት ይሆን በጎርፍ የመታው?!)
    በሐገራችን አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ "በማዕረጉ ታች ያለ ዲያቆን" የአንዳንድ ቀሳውስትና ጳጳሳትን የጨለማን ሥራ ገልጦ ከወቀሰና ከሥራው ጋር ላለመተባበር ወስኖ አቋሙን በግልጥ ካሳወቀ(የሚበዙ “Business ተኮር" አገልጋዮችን አያካትትም) እስከመወገዝ ያደርሰዋል፡፡ውግዘት ፍራቻም ብዙዎች "ጆሮ ጭው የሚያደርግ ነውርና ኃጢአት" በመካከላችን እየተሰራ እያዩ ገለል ብለው አልፈዋል፡፡እኔም ውግዘትን ሳልፈራ ቀርቼ አይደለም ግና ስለክርስቶስ ኢየሱስ ምናልባት የተናቅሁ ሆኜ ከተገኘሁ "የይበቃናል እንመለስ" ጥሪዬን በደሙና በመንፈስ ቅዱስ ጉልበት ለመጮህና ጥቂቷን መክሊቴን መቅበር ስለሌለብኝ ነው፡፡በተረፈ የማንም ቅጥረኛና ተላላኪም አይደለሁም፡፡ከምንም በላይ ቤተ ክርስቲያን በቅድስና ያለእድፈትና ፊት መጨማደድ ክርስቶስን አጊጣ ማየት የዘወትር ናፍቆቴ ነው፡፡