Monday 21 November 2022

ተሐድሶን ለማጥፋት መወሰድ ያለባቸው ርምጃዎች! (የመጨረሻ ክፍል)

Please read in PDF

2.  የተሐድሶን ጥያቄዎች መቀበል

የተሐድሶን ጥያቄዎች በደፈናው ከመቃወምና አገልጋዮችን ከማውገዝ ይልቅ፣ በቅንነትና በእግዚአብሔር ቃል መሰረት መዝኖ ጥያቄዎችን መቀበል ተሐድሶን ለማጥፋት የመጀመሪያ ርምጃ ነው። ይህም ርምጃ ምናልባት በአገልጋዮች እውቀትና ልምድ ማነስ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን ከተሐድሶ ዓላማ ጋር የማይሄድ ችግር ለማስቀረትና ሙሉ ለሙሉ በተሻለ አቅም ተሐድሶን ለመምራት ያስችላል።

ተሐድሶን አልፈልገውም ተብሎ አይካድም፤ ምክንያቱም ተሐድሶ በራሱ መንገድ የእግዚአብሔር ቃል በተነገረበት፣ የእግዚአብሔር ስም በተጠራበት እንዲሁም የእግዚአብሔር መንፈስ በሚሠራበት ቦታ ኹሉ የሚከሠት እንቅስቃሴ እንጂ ልናስቀረው የምንችለው ጉዳይ አይደለምና።

Sunday 20 November 2022

ተሐድሶን ለማጥፋት መወሰድ ያለባቸው ርምጃዎች! (ክፍል 1)

በእግዚአብሔር ቃልና በእግዚአብሔር መንፈስ ተፈጥሮ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ያለውን ተሐድሶን ለማጥፋት እንዴት ይቻላል? የሚለው ጥያቄ፣ የብዙ ዓመታት ጥያቄ ነው፤ ከታሪክም ኾነ በዚህ ዘመን እየኾነ ካለው እውነታ እንደምንረዳው አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናትና ግለሰቦች ተሐድሶ እንዲጠፋ ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን እንዴት ሊያጠፉት እንደሚችሉ አያውቁም። ለምሳሌ፦ በአገራችን ታሪክ በአባ እስጢፋኖስና በተከታዮቹ ደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ በኢትዮጵያውያን ነገሥታትና ጳጳሳት በተለይም በዐጼ ዘርዓ ያዕቆብ የተፈጸመውን ግፍ፣ ከአውሮፓ ታሪክም በአሥራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን በተነሣው የተሐድሶ እንቅስቃሴ ላይ ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የተደረገውን ተቃውሞ ማንሳት ይቻላል።

Saturday 5 November 2022

መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፳፪)

 Please read in PDF

ምጽዋት የናቡከደነጾርን በደል ደመሰሰን?

1.1.3. “… ልዑሉም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለሚወድደውም እንዲሰጠው እስክታውቅ ድረስ ከሰዎች ተለይተህ ትሰደዳለህ፥ መኖሪያህም ከምድር አራዊት ጋር ይሆናል፥ እንደ በሬም ሣር ትበላ ዘንድ ትገደዳለህ፥ በሰማይም ጠል ትረሰርሳለህ፥ ሰባት ዘመናትም ያልፉብሃል። የዛፉንም ጉቶ ይተዉት ዘንድ ማዘዙ፥ ሥልጣን ከሰማያት እንደ ሆነ ካወቅህ በኋላ መንግሥትህ ይቆይልሃል። ንጉሥ ሆይ፥ ስለዚህ ምናልባት የደኅንነትህ ዘመን ይረዝም እንደ ሆነ ምክሬ ደስ ያሰኝህ፤ ኃጢአትህንም በጽድቅ፥ በደልህንም ለድሆች በመመጽወት አስቀር። ይህ ሁሉ በንጉሡ በናቡከደነፆር ላይ ደረሰ።” (ዳን. 4፥25-28)።