Wednesday 30 October 2019

“ሂዱና … ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው።” (ማቴ. 28÷19)

Please read in PDF
   የቤተ ክርስቲያን የመጀመርያና የመጨረሻው ዋነኛ ራዕይና ተልዕኮ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ ማድረስና ደቀ መዛሙርት አድርጎ ወደመንግስቱ መሰብሰብ ነው። ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር የመንግሥት ወንጌል ከማገልገል በቀር ሌላ ምንም ተልዕኮ፤ የምትዋደቅለትም ዓላማ የላትም። በስደት ዘመን ሰማዕታት፤በሰላም ዘመን መምህራንና መጋቢዎችን፣ ድንቅ አማኞችን ቤተ ክርስቲያን ያፈራችው በእውነተኛው ዘር በክርስቶስ ህያውና ቅዱስ ዘር በሆነው ቃሉ ነው።

Thursday 24 October 2019

ገና አልተመለከታችሁምን? (ማር. 8፥17)

Please read in PDF
ይህ ጽሑፍ በ2008 ዓ.ም አጋማሽ ላይ በአንድ ሌላ የጡመራ መድረክ ላይ በብዙዎች የተነበበ ነው! መልእክቱ ዛሬም ደማቅ ስለ ኾነ በድጋሚ እንዲቀርብ ኾኖአል!
       ቃሉን የተናገረው በወርቀ ደሙ የዋጀንና ያዳነን መድኅን አለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ደቀ መዛሙርቱ በፈሪሳውያንና በሄሮድስ እርሾ ክፉ ኃጢአት በመዋጥ እንዳይጠፉ ባስጠነቀቃቸው ጊዜ፣ እነርሱ ግን ከማስተዋል ዘግይተው እንጀራ ባለመያዛቸው እንደ ተናገረ አስበው ተነጋገሩ። ጌታ ያየላቸው ዘላለማዊውን ዐሳብ ነው። እነርሱ ግን ገና በሥጋ አዕምሮ ነበሩና ስለ ቍሳዊውና ተበልቶ እዳሪ ስለሆነው እንጀራ አሰቡ። እርሱ ስለመንፈሳዊው ነገር ይነግራቸዋል እነርሱ ግን የሚናገራቸውን እንኳ በወግ አያስተውሉም።

Saturday 19 October 2019

በልብ መጠበቅ

Please read in PDF

ነገርን በልብ ስለ መጠበቅ በመጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ምዕራፍ ኹለት ጊዜ የተነገረላት እናት የኢየሱስ እናት ቅድስት ማርያም ናት። ቅድስት ድንግል ማርያምን በተመለከተ ከኹለት ልዩ ልዩ አካላት የሚሰነዘሩትን ነገሮች በጥሙና ለሰማ ሰው ዲያብሎስ ሐሳቡ የተሳካለት ይመስላል። (አንዱ ቤት ከአምላክ እንድትስተካከል አድርጎ፣ ሌላው ቤት ደግሞ ፈጽሞ እንድትጠላ በማድረግ)። ኹለቱም ወገኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ አድራሻ ለመራቃቸው እማኙና የመጀመርያው ማስረጃ ያው ታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። (ስለነዚህ ወገኖች ሌላ የብዕር ቀጠሮ ልያዝና በቀጥታ ወደ ዛሬው ዐሳቤ ላቅና)።

Sunday 6 October 2019

ሾላኮቹ (የመጨረሻ ክፍል)

Please read in PDF
ምን እንድርግ?
   በባለፉት ጊዜያት እጅግ መልካም ነገሮችን በማንሣት በዚህ ርእስ ሥር ስናጠና ቆይተናል፤ ሾላኮችን ጠባያቸውንና ኹለንተናዊ ባሕርያቸውን አንስተንም ተመልክተናል፤ ከዚህ በመቀጠል ደግሞ እኛ ምን ማድረግ እንደሚገባን በማንሣት የእግዚአብሔርን ቃል እንጫወታለን።
1.      ወደ ቃሉ እንመለስ፦ የሾላኮቹ ያላሳለሰ ተግባራቸው እኛን ከቃሉ መነጣጠል ነው፤ ወደ ቃሉ ልንመለስና ዘወር የምንልባቸውን ማናቸውንም ምክንያቶችና መንገዶችን ጨርሰው ነው የሚዘጉት። ብንመለስ እንኳ ለገዛ ራሳቸው እንዲመች አድርገው ቃሉን ያጣምማሉ እንጂ በትክክል እንድንመለስ አያደርጉም፤ አይፈልጉምም።

Friday 4 October 2019

እሬቻን የማላከብርበት ክርስቲያናዊ ምክንያቴ

Please read in PDF
መግቢያ

   ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ “የፖለቲካው ጡዘት አገራዊ መልኩን በመልቀቁ፣ ብሔርና ሃይማኖት ተደጋፊ” ከመኾን ጋር ተያይዞ፣ የበአላትን ፉክክር ሃይማኖታዊ መልክ ሲያለብሱ እየተመለከትን ነው። ይህ ደግሞ ውል አልባ የኾነ መጠዛጠዝንና መገፋፋትን፣ “እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ!” የሚል ሥጋዊ መቀናናትን ሲያስከትልና ትውልድ የሚመርዙ ተግባራት “ሃይ ባይ” ማጣታቸውንም እንድንመለከት አድርጎናል። ልክ እንደ ዘመነ መሣፍንት፣ “በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፤ ሰውም ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።” (መሣ. 16፥7) ተብሎ እንደ ተነገረው፣ የትኛውም ሰውና ብሔር መልካም መስሎ የታየውን ከማድረግ ከልካይ የሌለበትና እግዚአብሔር የተገፋበት የተናቀበት ዘመን ላይ ነን።