Monday 31 December 2018

ያልተንኮታኮትኩኝ!

Please read in PDF


ሞትን የማልፈራው ኩነኔን ምንቀው  
የጨለማን ግርማ ከምንም ማልጥፈው  ...  

Tuesday 25 December 2018

ለቀን አምላኪዎች!

መጽሐፉ ታጠፈ ተከድኖ ወየበ
የአሮጊቶች ተረት ደምቆ ተነበበ
ቀን ሳለ ለትጋት ለሥራ የተሰጠው

Wednesday 19 December 2018

“ግብረ ሰዶማዊ ሎጐ” በስፖርት መንደር!

 Please read in PDF
 የሰው ልጅ በኀጢአት ከወደቀ በኋላ፣ ነገሮችን ኹሉ ይቃኝ የነበረው በወደቀውና ከእግዚአብሔር በተለየው የኀጢአት ዝንባሌው ነው።አዳም በኀጢአት ሲወድቅ ከእግዚአብሔር ተለየ፤ በመለየቱ ልክ እንደ እርሱ ያለውን ከእግዚአብሔር የተለየ ልጅን ወለደ፤ (ዘፍ. 5፥3) ከእግዚአብሔር የተለየው ልጅ ቃየል ወንድሙን በመግደሉ (ዘፍጥ. 4፥8) “ኀጢአት በደጁ የምታደባበት፣ ፈቃድዋም ወደ እርሱ” ኾነች፤ (ዘፍጥ. 4፥7)። የኀጢአተኝነት ዝንባሌ በትውልዱ ልክ የጥፋት ውኃ እያየለው እንደ ሄደው እንዲኹ ተንሰራፊና ተስፋፊ እየኾነ ሄደ፤ (ዘፍ. 7፥19)።



Monday 17 December 2018

ቤተ ክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 5)

Please read in PDF
1.3.           መለያየት
(ቤተ ክርስቲያን ለመንግሥት የፖለቲካ ትርፍ እንጂ፣ እንደ ጌታ ቃል አልታረቀችም)
    መለያየት ከሥጋ ሥራዎች አንዱ ነው (ገላ. 5፥21)፤ ቅዱስ ጳውሎስ በልመና ቃል “ወንድሞች ሆይ፥ ኹላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ አሳብም የተባበራችሁ እንድትኾኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይኾን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።” በማለት ይናገራል (1ቆሮ. 1፥10)፤ መለያየት መነሻው የገዛ ምኞትን ከመከተል እንደኾነ ሲገልጥ ጠቢቡ “መለየት የሚወድድ ምኞቱን ይከተላል፥ መልካሙንም ጥበብ ሁሉ ይቃወማል።” በማለት ገልጦታል።
    የታረደው በግ “ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ከዋጀ” (ራ. 5፥9) ቤተ ክርስቲያን ከልዩነት ይልቅ የመንፈስ አንድነት ላይ ትልቅ ሥራ ልትሠራ ይገባታል። የመለያየት መንፈስን ማጥፋት የሚቻለው ማንነታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የተወረሰና የእኛ የኾነ ምንም እንደሌለን መረዳት ሲቻለን ነው። ይህም ዳግመኛ መወለድን ማዕከል ያደረገ ነው፤ “በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ” (ሮሜ 12፥10) የሚለን ሕያው ቃሉ እንደማይለያይ ወይም መለያየት እንደማይችል ቤተሠብ አንድ መኾናችንን ያገናዝባል።

Thursday 13 December 2018

ቤተክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 4)

Please read in PDF
1.3.           የአስተምህሮ ዝንፈት
“ከትምህርት የተነቀለ ከሕይወት የተሰናበተ ነው።”[1]

“ …ፍሬምናጦስ አኹን ተገኝቶ ያለውን የቤተ ክርስቲያንን ትውፊትና ድኅነት፣ ወንጌልና ትውፊት መደበላለቅና መተራመስ ቢመለከት ያዝን ነበር ብዬ አስባለሁ። …”[2]
“በክርስቶስ … ሆኖ” ሃይማኖትንና ምግባርን ሳይለያዩ ሁለቱንም በአንድነት ማወቅና አውቆም መፈጸም ለክርስቲያን ሁሉ አስፈላጊ ነው። ከሁሉ በፊት ሃይማኖት ይቀድማል። ስለሆነም … እርሱን በቅድሚያ መማርና ማወቅ ይገባናል። ዳሩ ግን ክርስትናችን ስለሃይማኖት በመማርና በመመራመር፥ በማጥናትና በማወቅ ብቻ አያከትምም። ምክንያቱም ከላይ እንደጠቀስነው “እምነት” ስንል “በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ” እንዲያው እምነት በተናጠል ብቻውን በእውቀትና በትምህርት ደረጃ ብቻ የቆመ ነገር አይደለም።”[3]

Saturday 8 December 2018

አባይነህ ካሴ ጠቡ ከኢየሱስ እንጂ ከአቡኑ አይደለም!

Please read in PDF

  “ … በግድ በብዙ ስም የሚጠራውን ልዑለ ባሕርይ ጌታ በአንዱ ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ ኢየሱስ ብቻ ብላችሁ ካልጠራችሁ ብሎ ሙግት ሌላ የተሰወረ ዓላማን ከሚያሳብቅ በቀር ሌላ ትርፍ የለውም። ወይ እኛ ኢየሱስ ማለት ትክክል አይደለም አላልን፤ ይህ ባልተካደበት ሁኔታ ከስሞች መርጦ ለአንዱ ያጋደለ ስሜት እንዲፈጠር ለማድረግ መሞከር አደገኛነትን ያሳያል። …”[1]

   በቀን 27/3/2011 በቦሌ መድኀኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ብጹዕ አቡነ በርናባስ የሰበኩትን ስብከት ከዩቲዩብ አውርጄ አደመጥኹት፤ ከዚያም በዚህ ስብከት ላይ ጥላቻውን ጮኾ በሚያሰማ መንገድ [ለኑፋቄ ግብር የገቡ ልማደኛ … ሐራጥቃዊመምህር ሰውዬው … እያለ “አዋርዶ” በመጥራት] አባይነህ ካሴ የተባለ የማኅበረ ቅዱሳን ቀኝ እጅ የኾነ ሰው፣ ስብከታቸውን በመተቸት የጻፈውንም አነበብኹ፤ እናም “ጉዳዩ ኢየሱስ ኾነና” አንድ ነገር እናገር ዘንድ ተገደድሁ።