Tuesday 30 March 2021

በጌታ ቸርነት ኹለተኛ መጽሐፌ ታተመ!

 Please read in PDF

“ያለ እውነት፥ የእውነት ቃል አገልግሎት!?” በሚል ርዕስ፣ ስለ “እውነት ቃል አገልግሎት” ማኅበር ከታሪካዊ ዳራቸው ጀምሮ፣ ትምህርቶቻቸውን የሚያስቃኘው መጽሐፌ ታትሞ ከቀን 22/7/2013 ጀምሮ ለንባብ ይበቃል! እንድታነቡት በፍቅር እየጋበዝኩ፣ አስተያየት እንድትሰጡበት፣ አንብባችሁ የማይረባና የማይጠቅም መስሎ ከታያችሁ “ጊዜያችንን አቃጥለህብናል፤ የማይገባ ድካም ደክመሃል” ብላችሁ ልትወቅሱኝ፣ ፍሬና ቁም ነገር ካገኛችሁበት ደግሞ “ታንጸንበታል፤ በርታ!” ልትሉኝ ትችላላችሁ።

Wednesday 24 March 2021

Friday 19 March 2021

አቢግያ - ኹለት ቤት ያዳነች ሴት

Please read in PDF

(የታማኝ ትዳር ውብ ምሳሌ)

መጽሐፍ ቅዱስ፣ እጅግ አስደናቂ ስለ ኾኑ ሴቶች ካስቀመጠልን ሕያው ምስክር አንዷ አቢግያ ናት፤ እንዲህም የተመሰከረላት፣ “የሴቲቱም አእምሮ ታላቅ፥ መልክዋም የተዋበ ነበረ፤” (1ሳሙ. 25፥3)። በተቃራኒው አቢግያ የስሙ ትርጓሜ “ጅል” ተብሎ ለሚጠራው ለናባል ሚስቱ ነበረች፤ እርሱ በምግባሩ “ባለጌ፥ ግብሩም ክፉ ነበረ፤ ከካሌብም ወገን የኾነና … ምናምንቴና ባለጠጋም ነበረ” (ቊ. 3፡ 25)። ሰውየው ባለጌ፣ ግብረ ክፉ፣ ካሌብ የስሙ ትርጉም “ውሻ” እንደ ኾነ፣ የውሻ ጠባይ ያለው ሰው ነበረ፤ ከሚስቱ ፍጹም ተቃራኒ ሰው!


Thursday 11 March 2021

መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፮)

 Please read in PDF

ካለፈው የቀጠለ …

ባለፉት ጊዜያት የ“መድሎተ ጽድቅ” መጽሐፍን በቀጥታ በመጽሐፍ ቅዱስ ከመመዘናችን በፊት፣ በመጽሐፉ ውስጥ ከቅዱሳት መጻሕፍት ዐሳብ ውጭ በኾነ መንገድ እንደ ገና ተተርጕመው የቀረቡትን ቃላት መመልከት መጀመራችን ይታወሳል። ቃላቱን በተመለከተ ዛሬም ቀጣዩን ክፍል የምናቀርብ ይኾናል። መልካም ንባብ።

·        መዳን፦ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥና በአጭር ቃል ስለ መዳን ሲናገር እንዲህ ይላል፣ “በእርሱ[በክርስቶስ] የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” (ዮሐ. 3፥16)። በመጽሐፍ ቅዱስ መዳን የሚለው ዐሳብ፣ ልክ በዚህ ክፍል እንደ ተጠቀሰው የዘላለም ሕይወት፣ አዲስ ልደት (ቲቶ 3፥5)፣ አዲሱን ሰው መልበስ (ቈላ. 3፥10)፣ አለመጥፋት (ዮሐ. 3፥16፤ 2ጢሞ. 2፥11)፣ ልጅነት (ሮሜ 8፥13)፣ ዳግመኛ መወለድ (ዮሐ. 1፥12-13፤ 3፥3-8) በሚሉ ተካካይ ዐሳቦች ገልጦት እንመለከታለን። 


Monday 8 March 2021

ኢየሱስ እስኪመጣ - ዘጠኝ የአገልግሎት ዓመታቴ

 Please read in PDF

በእግዚአብሔር ቸርነትና የተትረፈረፈ ምሕረት፣ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በብሎግ ወይም በጡመራ መድረክ አገልግሎት አገልግያለሁ፤ በእነዚህ ዓመታት ከእግዚአብሔር የሰማኋቸውን፣ የተቀበልኳቸውን፣ ቅዱስ ቃሉን ሳነብብና ሳጠና መንፈስ ቅዱስ የገለጠልኝን፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች የደረሱትን እጅግ አሳዛኝ ሰቆቃዎችንና ከፍ ያሉ በደሎችን በአካል በስፍራው ተገኝቼ በመመልከት እግዚአብሔር ምን ይሰማው ይኾን? ብዬ ሙሾ አውርጄአለሁ።   

Saturday 6 March 2021

የጾመ ሕርቃልና የጾመ ዓቢይ ተቃርኖ

 Please read in PDF

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የዓቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ስያሜ “ዘወረደ” ወይም “ጾመ ሕርቃል” ይባላል። የመጀመሪያውን ሳምንት “ዘወረደ” የሚለውን ስያሜ ያገኘው በባለዜማው ያሬድ ሲኾን፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከሰማያት መውረድና የሰዎችን ልጆች ለማዳን ያደረገውን የውርደት መንገድ በማሰብ፣ ከቅዱሳት መጻሕፍት ንባባት እየተነበበ አምልኮ የሚቀርብበትም ሳምንት ነው። ይኸው ሳምንት ከዚህ ከጌታችን ባሕርይ ተቃራኒ በኾነ መንገድ “ጾመ ሕርቃል” ተብሎም ይጠራል።

የጾመ ሕርቃል አጭር ጥንተ ታሪክ[1]

Thursday 4 March 2021

አዲሱ የሮዳስ ተረት!

Please read in PDF

መቼም የሐሰት መምህራንን ጠባይ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር እንዲህ ይላል፣ “ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ” (2ጢሞ. 3፥13)።  አንድ የስህተት አስተማሪ ፈጥኖ በቅዱስ ፍርሃትና የቅዱሳት መጻሕፍትን ሥልጣን በማክበር በመታዘዝ ካልተመለሰ፣ እየባሰ፣ እየከፋ፣ ኀጢአቱን እየጨመረ፣ አሳሳችነቱን ይበልጥ እየገፋበት ይሄዳል።