Monday 8 April 2024

ለምን ቶሎ አትምጣ!?

 Please read in PDF

አኹንማ አትምጣ

ኹሉንም ልትቀጣ

ትንሽ ዘግየት በል

ትንሽ ቆየት በል

ምናልባት ... እስክንስተካከል!

አንድ እግርህ ተነሥቶ በደጅ ብትኾንም

በቶሎ እንድትመጣ አናስቸኩልህም!

 

ትውልዱ ደንዝዟል

በኀጢአት ሰልጥኗል

ላንተ ጀርባ ሰጥቶ

ለክፋቱ ነቅቶ

ርቆ ሄዷልና

ሲመለስ ጠብቀህ እባክህ ቶሎ ና!

 

ግን አኹን አትምጣ

ሰው ላንተ እስኪመጣ

ብዙ ዕድል ሰጥተኸው እምቢ ካለህማ

አትዋል አትደር ኢየሱስ አኹን ና!

3 comments: