Thursday 30 August 2018

ቤተ ክርስቲያንም ከደቦ ገዳዮች እንደ አንዱ ስትኾን!

   Please read in PDF

ቤተ ክርስቲያን እንኳን የተፈጸመን ያልተፈጸመን ኀጢአት ማየት የምትችልበትን ነቢያዊ ችሎታ በመንፈስ ቅዱስ ተችሯታል። ኀጢአትን ለመቃወምና ለመጠየፍ፤ አለማዊነትንም ለመካድ ጭምር በክርስቶስ ኢየሱስ የተገለጠ የእግዚአብሔር ጸጋ ለቤተ ክርስቲያን ተገልጧል፤ (ቲቶ 2፥11-13)። ቤተ ክርስቲያን ይህን የተገለጠ ጸጋ በእውነት በመቀበልና በማመንም ጭምር፣ የሰማይ መንግሥት እንደ ራሴነቷን ማስቀጠል ይኖርባታል። ቤተ ክርስቲያን ይህን ዘላለማዊ አደራ ይዛ ለመሄድ ግን የሞተላትንና አንድ ቤዛዋን ክርስቶስ ኢየሱስን ትኵር ብላ መመልከት የዘወትር ተግባርዋ ሊኾን ይገባል።
  ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታችንን እንደ ተሰቀለ ኾኖ ትኵር ብሎ አለማየት ለድንዛዜና ለክፋት፤ ለእውነት ለማያሳዝዝ አዚም ሳያጋልጥ አይቀርም፤ (ገላ. 3፥1)፤ አዚም የአእምሮ ችግር አይደለም፤ ራስንም የመሳት ጉዳይ አይደለም፤ ፍጹም አለማወቅና አለመረዳትም አይደለም፤ ነገር ግን መረዳት እየቻሉ አለመረዳት፣ ማስተዋል እየቻሉ ተላላ በመኾን አለማስተዋል፣ ማየት እየቻሉ መታወር፣ መጠንቀቅ እየቻሉ ፍጹም ቸለተኛ የመኾን ጉዳይ ነው። የገላትያ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊቷ ያለውን እውነት በዝንጉነትና በቸለተኝነት ባለማስተዋል በአዚም ተያዘች። እናም የተሰቀለውን ክርስቶስን ባለማየት ስንፍና ተያዘች።

Thursday 23 August 2018

የሊቀ ጳጳሳት ፍራንሲስ ማሳሰቢያ ኹላችንን አይመለከትምን?

    የካቶሊኩ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፍራንሲስ፣ “ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በቀሳውስቷ በልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወሲባዊ ጥቃት የመከላከል እንዲህ ያለ አድራጐት ተፈጽሞ ቢገኝ እንኳ አንዳትሸፋፍን የሚያደርግ ባህል ለማረጋገጥ አስፈላጊው ጥረት ሁሉ መደረግ እንዳለበት” ዛሬ ከጽሕፈት ቤታቸው አስታውቀዋል። ይህ እጅግ አስደናቂም አሰቃቂም ውሳኔ ነው፤ ይህን ስሰማ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ባለ ነውር ተጠልፋ መውደቋን ደጋግሜ አሰብሁ፤ ውስጤም በጽዩፍ መንፈስ ኾኖ ተቈጣ።


Wednesday 22 August 2018

ከሆነኝ ኢየሱስ!

Please read in PDF

ጠዋት በማለዳ ሲመሽም በሠርኩ
በኃጢአት ወድቄ ድኼ እያለቀስኩ
መሐሪ ፍለጋ ለበደሌ ይቅርታ

Wednesday 15 August 2018

በሥጋ የተገለጠ አምላክ


    የክርስትና ትምህርት የመገለጥ ትምህርት ነው። የመገለጡ ምንጭ መለኮት ከኾነው ከራሱ ከእግዚአብሔር እንጂ፣ በሰው ወይም ከሰው አይደለም። ይህ መገለጥም “ከጥንት ጀምሮ በብሉይ ኪዳን ታሪክ እግዚብሔር በልዩ በልዩ መንገድ ለአበውና ለነቢያት በቃልም ሆነ በድርጊት፣ በራእይም ሆነ በሕልም በተአምራዊ ሁኔታ የገለጠላቸውን ሁሉ ያካትታል፤ በተለይም በኋለኛው ዘመን በሥጋ የተገለጠውን ክርስቶስንና የማዳን ሥራውን ሁሉ ይመለከታል።”[i]

ከዋናው መገለጥ በፊት የነበረው “መገለጥ”
     ብሉይ ኪዳን ታላቁን መገለጥ ፍለጋ ብዙ የመቃተት ድምጾች፣ ሕልሞች፣ ራእዮች፣ ትንቢቶች … የተሰማበት የምጥ መጽሐፍ ነው። እኒህ ብዙ መቃተቶችና ፍለጋዎች ለረጅም ዓመታት የተደረጉ ናቸው። በእኒህ ረጅም ዘመናት መላእክት ሊያዩት የሚመኙትንና ሰዎች ሊያገኙት ያላቸውን መዳን፣ ቅዱሳን ነቢያት “…ተግተው እየፈለጉ መረመሩት፤” (1ጴጥ. 1፥10-11)፣ ታላቁ ነቢይ ሙሴ፦ “የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ ነቢያት ቢሆኑ፥ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ መንፈሱን ቢያወርድ አንተ ስለእኔ ትቀናለህን?” (ዘኊል. 11፥29) በማለት፣ ታላቁ መገለጥ ለሕዝቡ ኹሉ እንዲገለጥና እንዲያገኛቸውም አብዝቶ ተመኘ። እጅግ የሚደንቀው ነገር የዘኊልቅ መጽሐፍን ሲጽፍ እንኳ፣ እጅግ የበዛውን ትውልዶች በመቁጠር ሲደክም ትልቁ ዓላማው ሊያርፍበት ያለውን ዋናውን መሲህ ፍለጋ ነበር። እርሱን ስላላገኘም በብዙ ፍለጋ ውስጥ ማለፉን እናስተውላለን።
    አንድ አባት ይህን እውነት በመጽሐፋቸው እንዲህ ብለው ገልጠዋል፦

Saturday 4 August 2018

ለ'ኔ ስትል "አርደህ"



"እኔ ቀናተኛ" ስትለኝ አምላኬ፤
እንዴት ትቀናለህ? ብያለሁ ሞግቼ፤
ግና ...

Wednesday 1 August 2018

“ … ይጸለይባችኋል” ፤ እንዲህም ደግሞ መች ነው የተጀመረው?

Please read in PDF
(ምነው ነውራችን አላልቅ አለ?)
   ከአንድ ወዳጄ ጋር በሥራ ምክንያት ተገናኝተን የቤተሰቡን የውርስ ጉዳይ ያማክረኛል። ሁሉም የተትረፈረፈ ሃብት አላቸው። የአባታቸው ውርስ ደግሞ የእነርሱን ይበልጣል። ሕጋዊውን መንገድ ከተጨዋወትን በኋላ መላ ቤተሰቡ ተማምነው ለታላቅ ወንድማቸው ውክልና ይሰጡትና ንብረቱ በየድርሻቸው በታላቅ ወንድማቸው እጅ እንዲተዳደር ይደረጋል። በሰላም ነገሩ ተቋጨ። ነገሩ ከተጠናቀቀ ከሦስት ወር በኋላ ግን የቤቱ አራተኛው ልጅ (ከሌሎቹ ይልቅ እጅግ ብዙ ሃብትና ተሰሚነት አለው) እኔው ያለሁበት ድረስ ይመጣል። ለካ፥ ከመካከላቸው አምስተኛው ልጅ ከአራተኛው ታላቅ ወንድሙ ጋር ተጋጭቶ በጠብ ይፈልገዋል።