Monday, January 22, 2018

የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፱

Plesae read in PDF
የቃሉ እውነት ቁጥር 2 -   እግዚአብሔር ልጅነታችን እስከመለኮት መኾን የሚደርስ ነውን? አይደለም፡፡
    ሰዎች ክርስቶስን ይመስላሉ ስንል፦ የአዲስ ኪዳን ምንባባት ይህን አባባል በግልጥ ወስነው አስቀምጠውታል፤ ይኸውም፦ (1ዮሐ.3፥2፤ ሮሜ.8፥29፤ ፊል.3፥21፤ 1ቆሮ.15፥49) በእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ፣ ሰው ከእግዚአብሔር ስለተካፈላቸው የቅድስናና የግብረ ገብነትን ባሕርይ እንጂ ሰው ፍጹም አምላክ ስለመኾኑ የሚያመለክቱ አይደሉም፡፡ ከፍጥረታችንም ሰው መኾን እንጂ፣ መለኮት የመኾንም ኾነ ወደዚያ የማደግ አንዳች ምክንያት የለንም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም በዚህ ረገድ የሚያስተምረን አንዳች ትምህርት የለውም፡፡
    በዚህ ምድርም ኾነ ከሙታን ትንሣኤ በኋላ በሚኖረን ሕይወት ከእግዚአብሔር ጥገኝነት ፈጽመን መላቀቅ አንችልም፡፡ ደግሞም፣ “We are independent”[1] “እኛ ነጻ፤ ከምንም ነገር ኢ ጥገኛ ነን” ማለት አይቻለንም፡፡ መጠጊያ ጥጋችን እግዚአብሔር ብቻ ነውና፡፡ እኛ በራሳችን በዚህ ዓለም ብቻችንን ለመኖር የሚያበቃን ሐለዎታዊ ሕይወትን አላገኘንም፤ አልተሰጠንምም፡፡ የሕይወት እስትንፋስን የሰጠን የሰማይ አምላክ ነው እንጂ፡፡

Monday, January 15, 2018

የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፰


·        1ቆሮ.316፦ “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?” በሚለው ቅዱስ ቃል ውስጥ፣ የእምነት እንቅስቃሴ መምህራን “ቤተ መቅደስ” የሚለውን በመውሰድ፣ የሥጋን አገልግሎት የማደርያነት ብቻ እንጂ ዘላለማዊ ወይም ከሰውነት ኹለንተና አንዱ አለመኾኑን ለመሞገት ያቀርቡታል፡፡
    ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ክፍል እየተናገረ ያለው፣ ስለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ማለትም በጥቅሉ ስለጉባኤው የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ ስለመኾናቸው ነው፡፡ ከክፍሉ ዓውድ እንደምንረዳው እየተናገረ ያለው አንድን ሰው ሳይኾን በጠቅላላ ተደራስያን የኾኑትን የቆሮንቶስን ቤተ ክርስቲያን አማኞች ነውና፡፡ ክፍሉን እንደምናስተውለው፣ ከሰው የሥጋ ሰውነት ጋር በመያያዝ የተነገረ አይደለም፡፡

Saturday, January 6, 2018

ታቹን አልርመጥመጥ!

መንቁር አፉን ነቅሎ
ጥፍሩን ኹሉ ጥሎ
ክንፉን እንኳ ሳይቀር ፍጹም አስወግዶ
በመለወጥ ሂደት መግል ቁስሉን ሽሮ
ዳግመኛ እስኪታይ በከፍታ በሮ

Wednesday, January 3, 2018

የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፯

Please read in PDF
ሬም በቀጣይነት የሰውን ሰው-ነት በመካድ ለሚያስተምሩት የስህተት አስተምሮአቸው የሚያነሷቸውን ጥቅሶች በማንሣት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሾችን እንሰጣለን፡፡
·        2ቆሮ.5፥1 ፦ ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ሥፍራ ሰው-ነታችንን “ምድራዊ ድንኳን” በማለት ይጠራዋል፡፡ ድንኳን ጊዜያዊ መኖርያ እንደኾነ እንዲሁ፣ ይህ የለበስነው ሥጋችንም በምንኖርበት ጊዜያዊ ዓለም ኗሪ፣ ለድካም ተጋላጭ፣ ሙስና መቃብር የሚያገኘው ነው፤ ስለዚህም ሥጋ መንፈሳዊ አካልን ሊለብስ ዳግም እስኪነሣ ድረስ በሞት ዓረፍተ ዘመኑ ይገታል፡፡ “የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰው-ነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል” (2ቆሮ.4፥16) እንዲል፣ ይህ እንደድንኳን ያለው ጊዜያዊ ማደርያችን የኾነው ሰው-ነታችን፣ ይለወጣል፣ ይጠፋል፣ ይታደሳል፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ከማይጠፋውና ሊሻር ከማይችለው ከሚኾነው ዳግም ትንሣኤ የተነሣ መንፈሳዊ አካልን ይለብሳል፡፡

Thursday, December 28, 2017

የማይለወጠው ዥንጉርጉሩ ነብርና የኢትዮጲያዊ መልክ

 ነቢየ እግዚአብሔር ኤርምያስ፦ “በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? በዚያን ጊዜ ክፋትን የለመዳችሁ እናንተ ደግሞ በጎ ለማድረግ ትችላላችሁ፡፡” (ኤር.13፥23) በማለት፣ ስለይሁዳ ኃጢአት በከባድ ወቀሳ ይናገራል፡፡ ነቢዩ ኤርምያስ ይሁዳ ተጠራርጋ በእግዚአብሔር ፍርድ ልትጠፋ እንዳለች በእግዚአብሔር ስለተረዳ፣ ሚስትን ከማግባትና ልጆችንም ከመውለድ ተከልክሏል፤ (ኤር.16፥1-4)፡፡ ትዳር ብቻም ሳይኾን ወዳጆቹም እጅግ ጥቂቶች ነበሩ፤ አኪቃም (26፥24)፣ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስና (39፥14) ኢትዮጲያዊው አቤሜልክ ናቸው (38፥7)፤ የክፋቱ ጠጣርነት ከሰው በብዙ ስላገለለው ረጅም ዘመኑን ያሳለፈው በሐዘን ነው፡፡
     የይሁዳ ኃጢአቶች የተገለጡና ለኹሉ የታዩ ነበሩ፤ “ይሰርቃሉ፥ ይገድላሉ፥ ያመነዝራሉ፥ በሐሰትም ይምላሉ፥ መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም ይገፋሉ፥ በቅዱሱም ስፍራ ንጹሕ ደምን ያፈስሳሉ፥ ስሙም በተጠራበት በቤተ መቅደሱ በፊቱ ቆመው፦ ይህን አስጸያፊ የሆነ ነገርን ሁሉ አላደረግንም ብለው ይክዳሉ፣ ስሙ የተጠራበት ቤት በዓይናቸው ፊት የሌቦች ዋሻ አደረጉት፣ የቀደሙት አባቶቻቸው እግዚአብሔርን ተዉ፣ አመነዘሩ፣ አማልክት ያልሆኑትን ለራሳቸው አማልክትን አድርገው፣ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ አመለኩአቸውም ሰገዱላቸውም፥ ያስቈጡትም ዘንድ በሰገነታቸው ላይ ለበኣል አጠኑ፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቍርባን አፈሰሱ፣ ሕጉንም አልጠበቁም፤ እንዲኹም እነርሱም ከአባቶቻቸው ይልቅ ክፉ አድርገዋል፤ እነሆም፥ ሁላቸውም እንደ ክፉ ልባቸው እልከኝነት ሄደዋል እርሱንም አልሰሙትም” (7፥1-11፤ 16፥11፤ 20፤ 22፥9፤ 23፥10፤ 32፥29፤ 44፥2፤ 23)፡፡ በዚህ ኃጢአታቸው እግዚአብሔርን ፈጽመው አስቆጥተውታል፡፡

Tuesday, December 26, 2017

በጋሻው “አፍንጫው ሲነካ[ስሙ ሲነሣ]፣ ዓይናችኹ ላላቀሰ” ኹሉ!Please read in PDF
    በግልጽ አንድ ያልተግባባነው ነገር አለ፤ የሐሰት ትምህርትን መቃወምና የሐሰት መምህራንን አለመቀበል የወንጌል ልብ አለመያዝ ወይም በወንድም ላይ መፍረድ ማለት አይደለም፡፡ ለበጋሻው ሳልራራለት ቀርቼ አልነበረም የሐሰት ትምህርቱን የተቃወምኩት፡፡ “አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥ አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ፤” (ይሁ.22-23) የሚለውን የቅዱስ ይሁዳ ቃልም ፈጽሞ ጠፍቶኝ ወይም ተዘንግቶኝ አይደለም፡፡
  ብናስተውል፣ የሐሰት ትምህርትን እንደቃሉ መቃወም እውነተኛ አማንያን እንዲጠበቁና እንዲጠነቀቁ ማድረግ ብቻ ሳይኾን፣ ሐሰተኛውን መምህር እንዲመለስ ተግሳጻዊ በኾነ መንገድ “የመማጸንም ሥራ” ነው፡፡ ትምህርቱን ስንቃወም ሰውየውን[የሐሰት አስተማሪውን] ከመጥላት ጋር አይደለምና፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንቶስ የነበረውን የታወቀውን አመንዝራ ሰው፣ “ … እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው” ሲል፣ ከጥላቻና መዳኑን ካለመፈለግ አንጻር ሳይኾን፣ “  መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ” ነው፤ (1ቆሮ.5፥5)፡፡

Monday, December 11, 2017