ኢየሱስ የማናፍርበት ወንጌላችን ነው፤ ወንጌል ክርስቶስ ባይኖርበት “የምሥራች!” ተብሎ ሊሰበክ አይችልም፤ የቆምነው፤ ያለነው፤ የምንኖረው፤ የምንንቀሳቀሰው… እግዚአብሔር በክርስቶስ ካትረፈረፈው ጸጋ የተነሣ ነው፡፡ ያለ ክርስቶስ ምንም ነን፤ ርሱ በምንም ነገራችን ውስጥ የገባ ምሉዕ አምላክና ሰው ነው፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት ያለ ክርስቶስ የሚመሰክሩት
ሌላ እውነት የለም፤ ሰማይና ምድር በውስጡም ያሉት ፍጥረታት ኹሉ ቢፈጠሩ የተፈጠሩት ለክብሩ ምስጋና ያቀርቡ ዘንድ ነው፤ “በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች
በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ
ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ” እንዲል (ራእ. 5፥13)፡፡
እንኪያስ ክርስቶስ ለእኛ፦
የሕይወት ራስና ባለቤት፤ መገኛ ነው፤ (የሐ.ሥ.
3፥14፤ 5፥31)፣
የመዳናችን ምክንያት ነው፤ (ዕብ. 5፥9-10)፣
ብቸኛው የኀጢአታችን ማስተስረያ (1ዮሐ.
2፥2)
ከአብ ዘንድ የታረቅንበት ብቸኛ መታረቂያችን
(ሮሜ 5፥11፤ 2ቆሮ. 5፥18፤ ቈላ. 1፥11)፣
ከርሱ በቀር የምንድንበት ሌላ መዳኛም፤ መንገድም
የለንም (ዮሐ. 14፥6፤ የሐ.ሥ. 4፥12)
በሰማይና በምድር ከርሱ በቀር የበረታና የማይሞት
ሌላ ሊቀ ካህናት የለንም (ዕብ. 4፥14፤ 6፥20)…
የምታምኑትና የምትወድዱት፤ በነፍስ ሳትሳሱ
የምታመልኩት ኹሉ ክርስቶስ ለእናንተ ምንድር ነው? ምስክርነታችሁን በመስማት ደስ ይለን ዘንድ መስክሩለት! ለክርስቶስ የማትመሰክር
ነፍስ በምድር ካሉት ነፍሳት ኹሉ ምስኪንና ድኻ ናት!
መስክሩለት፤ ኑሩለት፤ ስሙን አስከብራችሁ
እለፉለት እንጂ በስሙ ተደራድራችሁ መክሰር አይኹንባችሁ!
በኢየሱስ አንደራደርም!
ለድርድር የሚቀርቡ 2 አካላት ናቸው “እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ።”
ReplyDelete— ኢሳይያስ 40፥25 ጌታ ኢየሱስ የነፍሴ መልህቅ በተሻለ ተስፋ የገባልኝ ዋሴ ከጨለማው ስልጣን የዳንኩበት ነፍሴ እርሱን ስታስብ ብቻ ነው በመፈጠሯ የምትደሰተው ። ያለ እርሱ የሆኑኩባቸው በጨለማው ስልጣን የነበርኩባቸው አመታትን ሳስብ ኦ ጌታ ኢየሱስ የዮናታን ነፍስ በዳዊት ነፍስ እንደታሰረች ነፍሴ አንተን ብቻ ብላለች ። ጌታ ኢየሱስ እናንተ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም እንዳለ ያለ ኢየሱስ ሕይወት የለም ሕይወት ኢየሱስ ነው ። ያለ ኢየሱስ ያለ ሰው የሞተ በሕይወት ያለ ሰው ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ በሰማይ እና በምድር ክብር ለአንተ ይሁን።
ይሄ ከፍራሽ አዳሽ ህይወት ጋር ምን አገናኘው ማህሌቱ ዜማው ምንም ቢሆን ለእርሱ ነው ቤተክርስቲያን 24 ሰዓት ምስጋና ላይ ናት በዚህ አልክ በዛ 1 2 አዳራሽ ሄዶ ከምትዘሉት ጋር ወንጌል ሰበካው በፍፁም በፍፁም አይወዳደርም ከሚሰበከው ሰዓት ይጨመር ይሆን እንጂ ያነሰ አገልግሎት ቤተክርስቲያን የላትም።
ReplyDelete