Friday 17 November 2023

ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፮)

Please read in PDF

ካለፈው ቀጠለ …

4.2. አካል

“አካል ማለት የሚታየውና የሚጨበጠው ቁስ አካል አይደለም። አካል ‘ፍጹም ምሉዕና ቀዋሚ እኔ ባይ ማለት ነው’”[1]

ብዙ ሰዎች አካል የሚለውን ፅንሰ ዐሳብ የሚረዱት፣ ከሚዳሰስ ቍሳዊ ነገር ጋር በማያያዝ ብቻ ነው። በርግጥ የሰው ኹለንተና አካል ተብሎ መጠራቱ እውን ቢኾን፣ የሰው አካላዊነት ከዚህ የዘለለ ነው፤ ማለትም አካላዊነት ማንነትንና እኔነትን የሚያካትት ነውና። ስለዚህ አካል ስንል፣ የሰውን ወይም የአንድን ነገር የሚታየውን ቍሳዊ ነገር ብቻ እንዳልኾነ ልናስተውል ይገባል።

Friday 10 November 2023

ትምህርቱን ያር'ቅ ዘንድ!

Please read in PDF

ትምህርተ ሥላሴ የክርስትና ዋነኛ ትምህርት ነው። ጠንቅቀን ካልተረዳን ደግሞ ስተን የምናስትበት ትምህርት ነው። ቅድስት ሥላሴ የእምነት መሠረት እንደ መኾኑ፣ ይህን ትምህርት አለማመን ወይም ከትምህርቱ አንዱን አለመቀበል፣ ከኑፋቄ ያስመድባል። ለዚህ ምሳሌ፦ አርዮስንና መቅዶንዮስን በትምህርተ ሥላሴ ላይ ባመጡት ኑፋቄ መወገዛቸውን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስታውሷል።

Saturday 4 November 2023

ኢየሱስ የኀጢአተኞች ወዳጅ

 ኢየሱስ የኀጢአተኞች ወዳጅ የኾነው፣ እነርሱን ጻድቃንና ቅዱሳን የሚያደርግ ቅድስናና ጽድቅ ስላለው ነው። ኢየሱስ ይወደናል!



Wednesday 1 November 2023

ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፭)

Please read in PDF

ካለፈው ቀጠለ …

 4. ስለ ምሥጢረ ሥላሴ ስናጠና ልናስተውላቸው የሚገቡ ቃላት

ቃላትን በትክክል መረዳት ወይም ትክክለኛ ትርጕማቸውን ማወቅ ወደ እውነተኛ ዕውቀት ያደርሳል። በተለይ ደግሞ ትምህርተ ሥላሴን ስናጠና፣ በጥንቃቄ ልናጠናቸው የሚገቡ ቃላት አሉ። እኒህም፦

4.1. ሥላሴ፦ በአጭር ቃል፣ “ሥላሴ” የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ምንባባት ውስጥ የለም። ነገር ግን ለቃሉ ሳይኾን ለትምህርቱ ፍጹም ዕውቅናን እንሰጣለን። ምክንያቱም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሥላሴ ትምህርትና መገለጥ በስፋት አለና።

“በግእዝ ቋንቋ ቃሉ “ሦስትነት” ማለት ነውና በትምህርተ መለኮት ጥቅም ላይ ሲውል በአንዱ በእግዚአብሔር ሦስት አካላት እንዳሉ ያሳስባል። በ2ኛው መቶ ዓመት የአንጾኪያ ጳጳስ የነበረው ቴዎፍሎስ[1] በግሪክ ቋንቋ “ትሪአስ” እና ተርቱሊያን[2] በላቲን ቋንቋ “ትርንታስ” (በእንግሊዘኛ TRINITY) ስለ እግዚአብሔር ሲያስተምሩ፥ አካላት ሦስትነትን ለማመልከት ተጠቀሙባቸው። ከዚያን ጊዜ ጀምረው የቤተ ክርስቲያን አባቶች በእነዚህ ቃላት እየተጠቀሙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ለማብራራትና ለመወሰን ሰፊ ጥረት አደረጉ።”[3]