የምዩጣኑ ጥርስ ያገጠጠ
ውሸት!
መንደርደሪያ
ጃንደረባው የተባለ ሚድያ የሠራውን ቪድዮ፣ ተመልክቼአለኹ፤ አሰላስዬዋለኹም። ብዙ ሰዎች ደውለውልኝ የምጽፍበትን
መንገድ ሲያመላክቱኝ፣ ከነገሩኝ ሰዎች ተጽዕኖዎች ነጻ ልወጣ እንዲገባኝ ከራሴ መክሬአለሁ። በተለይም ደግሞ አንዳንድ ነገሮች፣
በቀጥታ ከእኔ ጋር የሚያያዙ በመኾናቸው ይህን ጽፌአለሁ። እጅግ በጣም አስነዋሪ ውሸቶችን ደግሞ ለማጋለጥ ስል፣ በግል የተደረጉ
የውይይት ቅጂዎችን ለመጠቀም ተገድጄአለኹ።
የሚዲያው አዘጋጆች፣ ተሐድሶ “ገንዘብ አለው” ከሚለው የአሉባልታ ተረት ነጻ መውጣታቸው፣ ጸረ ማርያም፣ ኦርቶ ጴንጤ
ከሚል ታርጋ ልጠፋ፣ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ፣ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን (በርግጥ ሄኖክ ተጠቅሞታል - የያ ትውልድ ትዝታ
ባይወጣለት መሰለኝ)፣ ጡት ነካሽ መና-ፍ-ቃን ከሚሉ ፍረጃዎችና ልጠፋዎች ... ነጻ በመውጣታቸው ደስ ብሎኛል። ይህን ሳስብ
አኹን ሥራ መሥራት ጀምረዋል ማለት ነው ብዬ አሰብኹ። ይህን ያደረጉት ከኹለት ምክንያት አንጻር ይመስለኛል፤ አንደኛው “የጥላቻ
ንግግር አዋጁን” ከመፍራትና ኦርቶዶክሳዊ ተሐድሶ ያመጣውን ተሐድሶ አዎንታዊ በኾነ መንገድ ላለመቀበል።
ሌላው፣ ዕቅበተ እምነትን በዚህ ልክ “በተሳሳተ መንገድ ቢኾንም”፣ተዘጋጅተው መሥራታቸው እጅግ ይበል የሚያሰኝ ነው።
ለእኔ ከዚህ ቀደም ማኅበረ ቅዱሳንና ያረጋል አበጋዝ በመጽሐፍ ከሠራቸው ሥራዎች አንጻር በይዘቱም በሞጋችነቱም በተወሰነ ረገድ
“ጠንካራ” ነው።
“ተሐድሶ” የልከኛ ኦርቶዶክሳዊነት
መገለጫ ነው!
ጃንደረባ ሚድያ ያልተረዳውና ሊያውቀው የማይፈልገው እውነታ፣ ኦርቶዶክሳዊ ተሐድሶ አይቀሬና ግዴታ መኾኑን ነው።
ደጋግመን እንደ ተናገርነው፣ ኦርቶዶክሳዊነት፣ “የክርስቶስ ሕይወትና ትምህርት፣ ሥራውም የተገለጠበት እውነት እንጂ ተቋም
አይደለም” ብለናል።
ኦርቶዶክሳዊው የክርስትና እምነትና ምግባር የተመሠረተውና
የተንጣለለው፣ በኦርቶዶክሳዊ በኾነው በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምኅሮ ወይም ዶግማ ላይ ነው። ጤናማ ትምህርትም ጤናማ ሕይወትና የኑሮ
ጠባይን ማስከተሉ አይቀሬ ነው፤ አክብሮተ እግዚአብሔር ያልተለየው ርቱዕ ሕይወት (orthopraxy) እና ርቱዕ ጥልቅ ፍቅር
(orthopathy) ከርቱዕ እምነት (orthodoxy) ጋር የተቈራኘና ከርሱም የሚመነጭ እንደ ኾነ ዘወትር ሊዘነጋ አይገባውም።
ታድያ ኦርቶዶክሳዊነት
መገለጫው ይህ ከኾነ፣ “ዛሬ ኦርቶዶክስ ነን የሚሉት ራሳቸውን የሚገልጡት በዚህ እውነት ልክ ነው ወይ?” ብለን መጠየቅ እወዳለን።
ይህን እውነታ ያስተዋሉትና ኦርቶዶስ ሳይኾኑ ሌላውን መና-ፍ-ቅ የሚሉትን በመታዘብ አለቃ መሠረት ስብሃት ለአብ እንዲህ በማለት
ተናግረዋል።
“ተዋሕዶ ሳይኾን ስሙ ሃይማኖቱ
ኦርቶዶክስም ሳይኾን ባህሉና ትምህርቱ
ሰርቆና ቀምቶ የሰው ስም በከንቱ
ሰው ኹሉ አለስሙ ምነው መጠራቱ”[1]
እውነታው ይህ ኾኖ ሳለ፣ ዛሬ ላይ ኦርቶዶክስ ሳይኾኑ ራሳቸውን ኦርቶዶክስ የሚሉ ወገኖች እጅግ ያሳዝኑኛል።
ጃንደረባው ሚዲያ፣ በሲኖዶስ ወይም በሐገረ ስብከት ደረጃ ካሉት ወይም ከሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ወይም
ከቤተ ክርስቲያኒቱ ኮሌጆች መካከል አንዱ ኾኖ ይህን ሲያቀርብ አይስተዋልም፤ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ውክልና
ፈጽሞ የለውም። ልክ ማኅበረ ቅዱሳን ከዚህ ቀደም፣ “ተሐድሶን አጥፊና አፍራሽ” አድርጐ በማቅረብ የግል ስምና ዝና፤ ሀብት
እንዳካበተበት እንዲኹ፣ ጃንደረባው ሚዲያም ይህን በማድረጉ “ከምድራዊ ረብ በቀር” አንዳች የሚያገኝበት ነገር የለውም።
አንድ እውነት ግን ማንም ሊያስተባብል አይችልም፤ ኦርቶዶክሳዊው ተሐድሶ በሲኖዶስ፣ በሊቃውንት ጉባኤ፣ በቤተ
ክርስቲያኒቱ ኮሌጆች፣ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ኹሉ ውስጥና በኦርቶዶክሳውያን አማኞች ልብ ውስጥ አለ፤ ይኖራልም። ተሐድሶ
ወንጌል በትክክል ባልተነገረበት፤ ባልተሰበከበት፤ ባልታወጀበት ኹሉ ቦታና ልብ መኖሩ ሊስተባበል አይችልም።
የምዩጣኑ ግብዝነት
በጃንደረባ ሚድያ ላይ የቀረቡት ሦስቱንም “ወንድሞች” አውቃቸዋለሁ። ኹለቱን በአካልና በትምህርት፤ አንዱን ደግሞ በሕይወትም
ጭምር። አየለና ሌላኛው ወንድም ሐረር በሥራ በነበርኩበት ጊዜ በሚገባ አውቃቸዋለሁ። የዚያኔ ለሰዎች “የእውነት ቃል አገልግሎት” አማኝና ሰባኪ የኾነውን የግርማ በቀለን የስብከት ካሴትን በድብቅ
የሚሸጡና የሚያከፋፍሉ ነበሩ። ከዚህ ባለፈ ደግሞ የሐረሮቹ ልጆች በሰዶማዊነት ከፍ ባለ ድምጽ ስማቸው ጐልቶ ከሚነሱ መካከል
ናቸው። የጃንደረባ ሚዲያ ሰዎች ይህን ሰምታችኹ ይኾን?!
ሐዋዝ ደግሞ ምንም እንኳ “ዘማሪ” ቢኾንም፣ ነገር ግን በቃለ አዋዲ ያገለግል በነበረበት ጊዜ በዚሁ አመለካከቱ
እንደ ነበረ ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት ስናወጋ የነበረውን የድምጽ ውይይታችንን ሰምቶ ማረጋገጥ ይቻላል።
እናም ሐዋዝም ኾነ ሌሎቹ
ተሐድሶን ኖረንበታል ቢሉትም፣ በርግጥ አያውቁትም፤ በተሐድሶ ኅብረት ውስጥ ኖረን ነበር ቢሉም፣ ነገር ግን በምልአት ለማለት የሚያስችል
የትምህርትም ኾነ የልምምድ ቁመና የላቸውም። ቢያንስ ስለ ተሐድሶ ለመናገር የሚቀድመው
እውነት፣ በትክክል ተሐድሶ መኾናቸውን ማመናቸው ነበረ፤ ግን ቀድሞም ተሐድሶ አልነበሩም አኹንም ተሐድሶ አይደሉም።
ማኅበረ ቅዱሳንና
ጃንደረባው የአንድ ሳንቲም ኹለት ገጽታ!
ማኅበረ ቅዱሳን የአክራሪነትና የወግ አጥባቂነትን መንገድ በመከተል የሄደ ነበር፤ የጃንደረባው ሚድያ ግን ውሸት፣
ግብዝነት፣ አጭበርባሪነትን በመከተል የትክክለኛ የእባብነት መገለጫን ገንዘብ በማድረግ የተሰማራ አስፈሪ ትውልድ ነው። በንጽጽር
ሲታዩ ምናልባት ማኅበረ ቅዱሳን የሚሻል ይመስላል።
ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያኒቱ ነግሦና ከብሮ የኖረው፣ “ተሐድሶን ጭራቅና አውሬ አድርጎ” በኦርቶዶክሳውያን ልብ
በመሳልና፣ በዚህም በብዙዎች ልብ ውስጥ ሰርጎ በመግባት ነው። እኔ የማኅበረ ቅዱሳን አባል በነበርኩባቸው ዓመታት፣ ስለ ተሐድሶ
እናገር የነበረውና ተሐድሶን ቀርቤ፣ መርምሬ፣ ፈትኜ ያየኹት እውነት ምሥራቅ ከምዕራብ የሚርቀውን ያህል አይገናኝም።
ጃንደረባው ሚዲያም “ከግብር አባቱ” ተምሮ በዚያው መንገድ መምጣቱ ብዙም አያስደንቅም። ተሐድሶ በሲኖዶስ ውስጥ
መኖሩን እንኳ ያስተባብላሉ፤ አንዳንድ በሕይወት ያሉና ያረፉ ጳጳሳት፣ ሊቃነ ጳጳሳትና ቆሞሳት አባቶች የሚያሰሙት አብዛኛው
ድምጽ የተሐድሶ ቢኾንም፣ እንደ ማኅበረ ቅዱሳንና ጃንደረባው ሚድያ ያሉ ተቋማት ግን እውነተኛው የተሐድሶ ድምጽ እንዳይሰማና
እንዲታፈን፤ ብሎም የሐ-ሰ-ት ፈጠራ በመፍጠር ሲናገሩ ማየት በቂ ምስክር ነው።
ዕቅበተ እምነት፣ ከጥንት የእውነተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ኦርቶዶክሳውያን አበው ሥራ ነው፤ አርዮስ፣ መቅዶንዮስ፣
ንስጥሮስና ሌሎችም የተወገዙት በርትዑ ክርስትና የሐሰት ትምህርታቸው ተመዝኖና ታሽቶ ነው። ነቀፋና ኑ-ፋ-ቄ ተገኝቶባቸው
በትክክል ተዳኝተው ነው። ማኅበረ ቅዱሳንና ጃንደረባው ሚድያ ግን የሚያደርጉት “የበሬ ወለደ” ትርክትን በማደራጀትና አሮጊታዊ
ተረቶችን ሰዎች ሰልቅጠው እንዲናገሩት በማድረግ ነው። በዚህ ግብራቸውም ኹለቱም የአንድ ሳንቲም ኹለት ገጽታ ናቸው።
ከዚህም በተጨማሪ ምዩጣኑም ኾኑ የጃንደረባው ሚዲያ
ባለቤቶች፣ ዋናው ትኵረታቸው፣ ኦርቶክሳዊውን ተቋም ማስመለክና ማግነን እንጂ የእግዚአብሔር መንግሥት እንዲሰፋና ወንጌል
ለብዙዎች እንዲደርስ ከማድረግ አንጻር ሲተጉ አንመለከትም። ለታሪካዊው ኦርቶዶክስ ከመወገንና ከመቆም ይልቅ፣ ለተቋማዊው
ኦርቶዶክስ ጥብቅና መቆም አይሎ ይታይበታል።
ሐዋዝም ይህን በማጕላት እንዲህ ይላል፣ “ዓለም በዜማ በማያመሰግንበት ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
በዜማ ታመሰግን ነበር።” ይህ እጅግ ከፍ ያለ “ራስን የማምለክ” አባዜ ነው፤ ኢትዮጵያ በጣዖት አምልኮ ሥር ኾና አሕዛብ በነበረችባቸው
ዓመታት፣ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር የቀደመውን ኪዳን መግባቱንና ያ ሕዝብም እግዚአብሔርን በዜማ ያመልክ፤ ያመሰግን እንደ
ነበር ማውሳት ብቻውን የዚህን ንግግር ሐሰተኝነት አጕልቶ ያሳያል።
ጌታ ግን የታመነና እውነተኛ ነው።
ይቀጥላል …
በርታ
ReplyDeleteአመዛዝኖ እና በእውቀት አይመስለኝም። he is not even reasonable
ReplyDeleteኢየሱስ እኮ በሁኔታዎች አይቀየርም ሓዋዝ በምንም ዓይነት ሁኔታ ብታልፍ ኢየሱስ ግን ሁሌም ብቻውን ኣዳኝ፣ ብቻውን በቂ ነው! የማርያም ፍቅር አስለቀኝ ስንኝ ጻፍኩኝ ልቤ ተንቀጠቀጥብኝ እያልክ በፍጡር ፍቅር ፈጣሪህን መተው ካንተ 👉 "ሰርቼ ሳይሆን በስራው፣ ዳንኩኝ በፀጋው!" ብሎ ከዘመረ ሰው አይጠበቅም!!! ሰከን ብለህ አስብ ፣ጸልይ ፤ ጌታ ይርዳህ🙏
ReplyDeleteመካከለኝነት ጋርደዋል ብዬ አላምንም አለኮ why was he in the reformation-als then??
ReplyDeletepositive የሆነ ነገር ላይ ነው ማውራት የምችለው?..."ወንጌልን ለሰዎች ማድረስ ነው ፍላጎቴ"....ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቀማል የሚለው ጋር አልደረሰም?
"የኔን" የሚለዉ የቱን ነው?...he just say አሁን ያለችው ኦርቶዶክስ ተሳስታለች ብዬ አላምንም አለ።
የአእምሮውን ሀሳብ ነው የሚያመልከው እግዚአብሔር እንኳን አያውቅም ጌታን አሁን ነው የጃንደረባው ቃለመጠይቅ የተሰካካልኝ ግራ ገብቶኝ ነበር ለካ ከመጀመሪያው ነው የተንሸዋረረው😏
ሃዋዝ ውዝግብ ውስጥ ያለ ይመስለኛል። በሌላ በኩል ደግሞ እረኛ ሲመታ መንጋው ይበተናል። የእግዚአብሔር ቃል
ReplyDelete“በዚያን ጊዜ ኢየሱስ፦ በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤ እረኛውን እመታለሁ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ የሚል ተጽፎአልና፤”
— ማቴዎስ 26፥31 እንደሚል ፊተኛ የሆነውን በማጥቃት የቃለ አዋዲ ምዕመናኖችን ለመበተን ሰይጣን ጥሩ በር አግኝቷል።
የቃለ አዋዲ መሪዎች ንቁ !
Wendim Abenezer
ReplyDeleteNegeru ende mimeslegn alemetewawek kalewaedi hibret wust allee ye wendimachin bahil ayitayim.2nd Hawaz ye hone yetechegere neger yinoral bichaa yitasebibet kalawedihoch sile mengaw maseb alebachew