Sunday 28 June 2015

ስለግብረ ሰዶማዊነት ከአየርላንድ ስህተት ምን እንማራለን?

     
                            Please raed in PDF                        

   ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል ልጆች ከግብጽ በወጡ ጊዜ እርሱን በማክበርና በመፍራት እንዲያመልኩት በዓላትን ሰጥቷቸዋል፡፡ ከተሰጡት በዓላት መካከል ደግሞ የፋሲካ ፣ የመከርና የዳስ በዓላት የትኛውም እስራኤላዊ ከሚኖርበት ከስደት ምድሩ በመምጣት በእስራኤል ምድር ተገኝተው እንዲያከብሩ አዟቸዋል፡፡ (ዘጸ.23፥14፥17) በእነዚህ የበዓል ወራት የእስራኤል ጎዳናዎች ሁሉ የሚሸቱት እጅግ የተወደደውን የመንፈሳዊነትን ለዛና ዝማሬ ነው፡፡
      ከጥቂት ዓመታት በፊት በካቶሊክና በፕሮቴስታንት ጎራ ክርስትናዋን ከፍላ ጎዳናዎቿን በደም ያጨየቀችው አየርላንድ ፤ አሁን በጎዳናዎቿ የተሰማው ነውር ጆሮን ጭው የሚያደርግ ነው፡፡ ግብረ ሰዶምን በወንጀል ህጓ ጠቅሳ በመከላከልና ለጋብቻ ባላት እሴቷ በአገራችን ካለው ሕግና እሴት ጋር እጅግ የተቀራረበ ነበር፡፡ አየርላንድ በወንጀል ህጓ በግልጥ ግብረ ሰዶምን መከልከል ብቻ ሳይሆን ፈጽመው የተገኙትንም ትቀጣ ነበር፡፡

Sunday 21 June 2015

ክርስቶስን “በሚያባብል ቃል” … ለምን?! (ክፍል አንድ)

    
                                               Please read in PDF

    ጌታ እግዚአብሔር የነጻነት አምላክ ነው ፤ የወደድነውን ፣ ሕሊናችን የመረጠውን ኃላፊነትን ከሚያስከትለው ውጤት ጋር የመቀበል ሙሉ ነጻነትን ሰጥቶናል፡፡ መንገዳችንን እንደእስራኤል ዘሥጋ ቀድመን ማጥራትና መምረጥ ከእኛ ነው የሚጠበቀው፡፡ መንገዶቹም በረከትና መርገም የሚባሉ እንጂ  ሌላ ሦስተኛ አማራጭ የለም፡፡ ይህንን እውነት ነቢዩ ቅዱስ ሙሴ ምድረ ርስትን ሊወርስ ላለው ፥ ለአዲሱ ትውልድ ሕጉን ለማስተማር ፤ የምክርንም ቃል በተናገረበት አንቀጹ እንዲህ ብሏል፦
“እነሆ፥ እኔ ዛሬ በፊታችሁ በረከትንና መርገምን አኖራለሁ፤ በረከትም፥ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትሰሙ ፣ መርገምም፥ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባትሰሙ፥ ዛሬም ካዘዝኋችሁ መንገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎችንም የማታውቋቸውን አማልክት ብትከተሉ ነው፡፡” (ዘዳግ.11፥26-29)

Tuesday 16 June 2015

በክስ አታዳክሙኝ!


                    Please read in PDF  

ለምን እክዳለሁ ፣ አመንዝራነቴን ፤
ሌባና አመጸኛ ፣ ስግብግብነቴን ፤
አላስተባብልም ፣ ስሁት ሰው መሆኔን … ፤

Wednesday 10 June 2015

ቅዱስ ሲኖዶስና የመሰብሰቡ ዓላማ (የመጨረሻ ክፍል)



3. በግፍና ያለሥራው የሚወገዝ እንዳይኖር ለመከላከል

      “ … ወደጌታችን ወደኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ንጽሕና በሚቀርቡ ገንዘብ፡፡ ከካህናት ወገን ወይም ከሕዝቡ ወገን ቢሆን ኤጲስ ቆጶስ አውግዞ የለየውን ሰው ፍርድ ይመረምሩ ቸልታ እንዳይሆን ወይም ይህን በሚመስል ነገር ሁሉ እንደተገለጠላቸው ይፈርዱ ዘንድ፡፡” የሚለው የፍትሐ ነገሥቱ አንቀጽ አድሎዐዊነት እንዳይከሰት በውስጡ ማሳሰቢያ አዘል መልዕክት አለው፡፡ የቱም ጤናማ አባወራ ወይም የቷም ጤናማ እማወራ ልጆቿም የምታሳድገው ባለማበላለጥ በእኩልነት ነው፡፡ ኤጲስ ቆጶስም አማኞችን ሲመራ ልክ ቤተሰቡን እንደሚመራው አይነት ምንም አድሎ በማይኖርበት መልኩ ሊሆን ይገባዋል፡፡ (1ጢሞ.3፥4)

Thursday 4 June 2015

ጰራቅሊጦስ- መንፈስ ቅዱስ


                             Please Read in PDF


  ከግሪኩ “ፓራክሊቶስ” ወይም ከዕብራይስጡ “ፕራቅሊጥ” ከሚለው ግስ የተገኘው “ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል ትርጉሙ “ አማላጅ ፣ አስታራቂ ፣ አፍ ፣ ጠበቃ ፣ ትርጁማን ፣ አምጃር ፣ እያጣፈጠ የሚናገር ፣ ስብቅል ካፉ ማር ጠብ የሚል፡፡ … ፤ ናዛዚ ፣ መጽንዒ ፣ መስተፈስሒ ፤ መንፈስ ቅዱስ፡፡” በማለት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ተርጉመውታል፡፡ (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ/አለቃ/፤ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፡፡(1948 ዓ.ም)፤አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፡፡ ገጽ.907)