Tuesday 12 March 2024

እኔ ነኝ አድራሻው!

Please read in PDF

 ጌቶችና አለቆች  ገናና ክቡራን

በሰው ፊት ታላላቅ የኾኑ ኃያላን

ለምድር ለከበዱ ታዋቂ ምሑራን

ለግብዝ አስመሳይ ለሚወዱ ዓለምን …

አይደለም ለነርሱ ከሰማይ መውረዱ

ለእኔ ነው የመጣው እኔን በመውደዱ፡፡

ኀጢአት ላረገፈኝ ለምጽ ላነደደኝ

ሰይጣን መጫወቻ ዕቃቃው ላረገኝ

ለኔ ነው ጌታዬ እኔኑ ፍለጋ

የተንከራተተው እስከ ምድር ዖሜጋ

እኔ ነኝ አድራሻው እኔ ነኝ ናፍቆቱ

እኔን ለማግኘት ነው ተሰቅሎ መሞቱ!  

No comments:

Post a Comment