Saturday 31 December 2022

“የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው መጻሕፍት ሁሉ - ኒዎኔወስቶስ” (2ጢሞ. 3፥16)

Please read in PDF

ቅዱስ ጳውሎስ ኹለተኛ ጢሞቴዎስን ሲጽፍ፣ የኑዛዜ ያህል በሞቱ ዋዜማ ነው (4፥6)፤ የሚጽፍለት ደግሞ “በመንፈስ ለወለደው ልጁ” (1፥2) ቅዱስ ጢሞቴዎስ ነው፤ ለዚህ ተወዳጅ ባላደራ አገልጋይ፣ የቅዱሳት መጻሕፍትን እስትንፋሰ እግዚአብሔርነት በግልጥ ይጽፍለታል። ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ክፍል፣ መጽሐፍ ቅዱስን፣ “ቅዱሳት መጻሕፍት” እና የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው መጻሕፍት” በማለት ይጠራቸዋል። “ኒዎኔወስቶስ” የሚለውም የግሪክ ቃል፣ የቅዱሳት መጻሕፍትን የእግዚአብሔር እስትንፋስነት የሚገልጥ ቃል ነው።

Sunday 25 December 2022

ሄኖክ ኃይሌ(ዲያቆን) ስለ አዋልድ መጻሕፍት ያሳየው ደካማና ጠንካራ ሙግቱ!

 Please read in PDF

ሄኖክ ኃይሌ፣ ስለ ተአምረ ማርያም በጻፈው ኹለተኛ ክፍል ላይ እስካኹን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ አዋልድ መጻሕፍትን (ማለትም ትርጓሜያትን፣ ገድላትን፣ ድርሳናትን፣ መልክዐ መልክዕን፣ ተአምራትን፣ ነገራትን፣ ፍካሬያትን) ለማስተካከልና ለማደስ የተቸገረችበትን ምክንያት ሲጠቅስ እንዲህ ይላል፤

“ … ላለፉት ሠላሳ ዓመታት ያሳተሟቸውና በነጻ ያደሏቸው መጻሕፍት … ክርስቶስን ‘ጨርሶ አታውቂም’ የሚሏትን ከሳሾችዋን በማስታገሥ ሥራ ላይ ተጠምዳ እንድትቆይ ግድ ኾኖባት ቆይቶአል።”

Friday 16 December 2022

ዮናታዊ ቀበሮነት!

 Please read in PDF

በግልጽ ቃል የዮናታን ዓላማ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ አይደለም፤ ዓላማው ቅዱስ ወንጌልን መስበክ ቢኾን ኖሮ፣ “የቃል እምነት እንቅስቃሴ” ከሚባል ነሁላላ ትምህርት አስቀድሞ ራሱን ባረቀና በጠበቀ ነበር። ነገር ግን ይህ የኑፋቄ ትምህርቱ እንዳይታወቅበት፣ የኦርቶዶክስን ድርሳንና ገድላት በመንቀፍና በመተቸት “ራሱን ወንጌላዊ አድርጎ ለማቅረብ” ብዙዎችን ያሞኛል፤ ያጃጅላል።



Monday 12 December 2022

ተሐድሶ እንዴት ይታያል? የመጨረሻ ክፍል

 Please read in PDF

ካለፈው የቀጠለ …

የቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዓታት የዶግማ ማስፈጸሚያ ሥልቶች ናቸው። ለምሳሌ መጠመቅ የግድ ነው፦ ዶግማ ነው፤ የአጠማመቅ ኹኔታ ግን ሥርዓት ነው። ቁርባን ዶግማ ነው፤ ‹እንዴት መቁረብ ይኖርብናል?› በሥርዓት መልስ ያገኛል። በዚህ ዓይነት ከሐዋሪያት ጀምሮ ያሉ አባቶች ከኅብረተ ሰቡ የአኗኗር ሁኔታ ጋር የሚስማሙና ለጽድቅ ሥራ የሚያበቁ የእምነት መተግበሪያ ስልቶችን ነድፈዋል፤ እንደ ኹኔታውና እንደ ኅብረተ ሰቡ እያዩም ሊያስተካክሉት ይችላሉ።

Sunday 11 December 2022

ተሐድሶ እንዴት ይታያል? ክፍል ፩

 Please read in PDF

ከረጅም ጊዜያት ጀምሮ የተሐድሶ ጉዳይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አነታራኪ ኾኖአል። ንትርኩም “ባፍ በመጣፍ” እንደሚባለው ኾኖአል ማለት ይቻላል። ንትርኩና ፍትጊያው አኹንም ድረስ ያለና እንዲያውም፣ በአኹን ወቅት ደግሞ በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ “ጸረ ተሐድሶ የተባሉ ኮሚቴዎች” የተቋቋሙበትና ከፊት ይልቅ በጽኑ ለመቃወም ቅስቀሳ እንዳለ ጸሐፊው ያስተውላል። ንትርኩና ጭቅጭቁ ደግሞ፣ ቀለል ከሚለውና ለመመለስ ግን ከሚቸግረው፣ “ተሐድሶ የሚባለው እንቅስቃሴ አለ ወይስ የለም?” ከማለት ይጀምራል። እኔም ከዚሁ፣ “እውን የተባለው የተሐድሶ እንቅስቃሴ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ እየተካሔደ ነው ወይስ የለም?” ብዬ በመጠየቅ ልነሳ ፈለግኹ።



Saturday 3 December 2022

የዕብራውያን መልእክት ዓላማና የእኛ ዘመን መመሳሰል!

 Please read in PDF

ኢየሱስ ከይሁዲነት ይልቃል!

ኢየሱስ ከኦሮሞነትና ከአማራነት ከሌሎችም ይልቃል!

ኹሉም የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የተጻፉበት የየራሳቸው ዓላማ አላቸው፤ የመጻሕፍቱ ዋነኛ ዓላማ ማጠንጠኛው ደግሞ፣ የእግዚአብሔር መንግሥትን ማዕከል ያደረጉ ናቸው፤ ከዚህም የተነሣ ዓላማቸው የሚበልጠውንና የሚልቀውን የእግዚአብሔርን ዐሳብና ፈቃድ ማሳየት ነው። ከዚህ አንጻር የዕብራውያን መልእክትን ስንመለከት፣ ኹለት ዋና ዋና ዓላማዎችን ማውጣትና መናገር እንችላለን።

የመንፈስ ቅዱስ ጸጋዎች ቀርተዋል ለማለት አንሻፍፈው የሚተረጕሟቸው ጥቅሶች

Please read in PDF

   “በአሁኑ ዘመንም የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ በሚታይበት ቦታ ኹሉ አንዳንዶች ያፌዛሉ፤ ሌሎች ደግሞ እውነተኛ ምልክት እያዩ “ዐይኔን ግንባር ያድርገው” በማለት ለአኹኑ ዘመን አይደለም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በሐዋርያት ዘመን አክትሟል ሲሉ ሌሎች ደግሞ “ተጠንቀቁ” በማለት በድፍኑ መሸሽን ይመርጣሉ።”[1]

ኹሉም የስሕተት አስተማሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ክፍሎች ለትምህርታቸው ዋቢነት ከዐውዱ ውጭ ቦጭቀው በማውጣትና በመጥቀስ ዘወትር ይታወቃሉ። የቅዱሳት መጻሕፍትን ሐሳብ ለገዛ ትምህርታቸው በማጣመም ይታወቃሉ፤ ግልጡን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በማጣመም ወይም አወሳስቦ በመተርጐም የሚያኽላቸው የለም፤ ቅዱስ ጴጥሮስ “በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፥ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ” እንዲል (2ጴጥ. 3፥16)።