ካለፈው
የቀጠለ …
2. ፍጹም ፍቅር፦ እግዚአብሔርም[ሥላሴ] ፍቅር ነው (1ዮሐ. 4፥16)፤ ይህ ፍቅር፣ ፍጥረት ከመፈጠሩ በፊት በሥላሴ ዘንድ ያለ ነው፤ ጌታችን ኢየሱስ፤ “ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ … ።” (ዮሐ. 17፥24) ብሎ ሲናገር፣ አብና ወልድ ከዘላለም ጀምሮ ይዋደዱ እንደ ነበርና አብም ለወልድ የሚሰጠው ክብር እንዳለ ያሳየናል። “አባት ልጁን ይወዳል” እንዲል (ዮሐ. 3፥35)።
ፍቅር የሥላሴን
የሥራውን ዓላማ ያመለክታል፤ እግዚአብሔር
ፍቅር ስለ ኾነ ራሱን ለሌሎች አሳልፎ የሚሰጥ ነው፤ “የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ
እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።” (1ዮሐ. 4፥9) እንዲል፣ የእግዚአብሔር ፍቅር አንድያ ልጁን ለዓለሙ በመስጠት ተገልጦአል (ዮሐ. 3፥16)፤ ይህንም
ያደረገው ርሱ አስቀድሞ እኛን በመውደድ ነው፤ (1ዮሐ. 4፥19)።
ፍቅር ምንጊዜም መልካም የኾነውን ብቻ
ያስባል፣ (1ቆሮ. 13፥1-11)። ደግሞም በባሕርይው ፍቅር የኾነው እግዚአብሔር ብቻ ነው። በፍጥረት ላይ ያለው የዘወትር ዓላማውም
ኾነ የዘላለም ፈቃዱ ፍቅር ብቻ ነው። እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጣቸውም ሕግጋት መሠረታቸው ፍቅር ነው፤ “እግዚአብሔርን በፍጹም
ልብህ፣ ነፍስህና ዐሳብህ ውደድ” የሚልና “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚል።
እግዚአብሔር በፍቅሩ ኹሉን ይወዳል። በባሕርይውና በተግባሩ ኹሉ አፍቃሪ ነው፤ በእንዲኹ ፍቅር
ራሱን ገለጠልን፤ (ዮሐ. 3፥16፤ ሮሜ 1፥16)፤ ፍቅሩም በልባችን ፈሰሰ፤ (ሮሜ 5፥5፤ 1ዮሐ. 4፥8)። ዓለም ሳይፈጠር
በሥላሴ ዘንድ ያለው አኹንም ወሰን የሌለው ፍቅር ይገኛል። በሥላሴ ዘንድ ምንም ዓይነት ጥላቻ ወይም ቅይማት የለም።
የርስ በርስ መዋደዳችን ምንጩ፣ ከሥላሴ ዘንድ በመነጨው ፍቅር ነው፤ “ወዳጆች ሆይ፥
እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል።” (1ዮሐ. 4፥11)፤
ክርስቶስንም ለመከተላችን መገለጫው ሌሎችን መውደዳችን ነው፤ “ርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ
ኾናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።” (ዮሐ. 13፥35)። ስለዚህ ማናቸውም ሰው ሥላሴን የማያውቅ ከኾነ፣ እውነተኛ
ፍቅርን ጨርሶ አያውቀውም!
“ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥” (ሮሜ 5፥10)
እንዲል፣ ጠላት ሳለን እግዚአብሔር[ሥላሴ] ታርቆናል፤ ስለዚህም እኛም ከእግዚአብሔር በተሰጠን ፍቅር፣ “በሰማያት ላለ
አባታችሁ ልጆች ትኾኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም
ጸልዩ፤”
(ማቴ. 5፥44-45) ተብለን ታዝዘናል። ሥላሴን በትምህርትም፤ በሕይወትም የሚከተል ለፍቅር እንግዳ አይደለም፤ ሌላውንም ለመውደድ
ጸጋ አይነጥፍበትም።
“በማያቋርጥ ፍቅር ጌታችንን
ኢየሱስ ክርስቶስን ለሚወዱ ሁሉ ጸጋ ይሁንላቸው።” (ኤፌ. 6፥24)
ይቀጥላል …
ፀጋው ይብዛልህ
ReplyDeleteVery interesting article. May God bless your work. Indeed, the Lord Jesus is the bridegroom of the Church. And his bride, the Church, longs for him, chanting MARANATHA (O Lord Come) so that he may come and take her to the Kingdom.
ReplyDelete