Wednesday 28 January 2015

መምህር ፣ ኢንጂነር ፣ አርቲስት ፣ ዲያቆን ...


                                         Please read in PDF
   
    መጽሐፍ ቅዱስንም ሆነ የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ ስናጠና ጸጋ ልዩ ልዩ እንደሆነ ፤ ነገር ግን መጋረጃን እንደሚያያይዘው ኩላብ የተያያዙና አንድን አካል እንደመሥራት ያሉ እንደሆኑ እናስተውላለን፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ ጸጋዎችን ለቤተ ክርስቲያን አማኞች የሚሰጠው የጸጋ ድኃ እንደሌለና የቤተ ክርስቲያንን ምልአት ለማሳየት ነው፡፡ በጸጋ ትምህርት ትንሽ የሚባል ጸጋ ከሌለ ሁሉም እኩል ሊከበሩና አገባብ ያለው ሥፍራ ፤ ክብር ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን በጳጳስነት ጸጋ እንደ ኤፌሶን ሽማግሌዎች የሚመራ አማኝ ፥(ሐዋ.20፥28) የእርሱ ጸጋ ቃሉን እንደልድያ በመስማት ልቡ ከተከፈተለት ሰው ጋር (ሐዋ.16፥14)  ምንም የጸጋ ልዩነት የለውም፡፡

Thursday 22 January 2015

ዕድሜና ፍሬያችን


                                      Please read in PDF

ከትላንት በስቲያ …
አሜሪካ ʻምትባል ትልቅዬ አገር
በአንድ መልሳ ፣ የሥጋ መንፈስዋን ፣ ክፍልፍሉን መንደር
ʻስቴቶቿን ሁሉ ቀምራ አዋህዳ
ተተኮሰች “አሉ” አድጋ ተመንድጋ
እኛን እዚህ ትታ እርሷ ወደህዋ …

Sunday 18 January 2015

“የምወድህ ልጄ አንተ ነህ …” (ማር.1፥10)





እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት መታሠቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡



    ጌታ የማስተማር አገልግሎቱን ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ሲሆን (ሉቃ.3፥23) በግልጥ ለማገልገልና ለመጠመቅ ከመውጣቱ በፊት ይኖር የነበረው ደግሞ በገሊላ ናዝሬት ነው፡፡ (ማቴ.2፥23) ናዝሬት በብሉይ ኪዳን በአንድም ሥፍራ ስሟ ያልተጠቀሰችና የማትታወቅ ከተማ ናት፡፡ ናዝሬት የማትታወቅና ያልተጠቀሰች ከተማ ብትሆንም፥ ለጌታ ኢየሱስ “ቅጥያ ስያሜ” ሆና “የናዝሬቱ ኢየሱስ” ለመባል የበቃች ከተማ ናት፡፡ ጌታ “የናዝሬቱ  ኢየሱስ” የተባለው ስለተወለደባትና ስላደገባት ብቻ እንጂ እንደነሶምሶን “ልዩ ናዝራዊ” ለመባል አይደለም፡፡

Monday 12 January 2015

ፊደል ከንባብ ፤ መንፈስ ከትርጓሜ ይስማማልን?

                         
                                Please read in PDF

                             “የሥጋ ሕግ ያጠፋል፤ የነፍስ ሕግ ግን ያድነናልና”
                           (በግርማዊ ቀዳ. ኃይለ ሥላሴ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጲያ
                            መልካም ፈቃድ በአሜሪካ ከታተመው የ1938 ዓ.ም
                            መጽሐፍ ቅዱስ ከታተመ የተወሰደ፡፡ ገጽ. 386)
    በማስጨነቅ ወይም እጅ በመጠምዘዝ ከሚተረጎሙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አንዱ ከላይ በርዕሳችን ያነሳነው ቃል በብዛት ይዘወተራል፡፡ ይህንን ቃል ብዙ ምዕመናን ብቻ ሳይሆኑ በሕዝብ ዘንድ “ተቀባይነት ያላቸው” የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና ሰባኪዎች ጭምር በመጽሐፎቻቸውና በስብከቶቻቸው መሐል ከመጽሐፉ ሐሳብ ውጪ በመውጣትና ወደራስ ሃሳብ በመሳብ ሲተረጉሙት አይተናል፤ ሰምተናልም፡፡

Tuesday 6 January 2015

የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ልዩ ነው!

       
                                  Please read in PDF



             እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 
               መታሠቢያ በዓል በሰላም  አደረሳችሁ!!!!

        ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዷል፡፡ መወለዱም “ልደተ አዳም እምድር ፤ ልደተ ሔዋን እምገቦ ፤ ልደተ አቤል እምከርሥ ፤ ልደተ በግዕ እምዕፅ ፤ ልደተ ሙታን እመቃብር” እንደሆነው ያይደለ የእርሱ ከዚህ የተለየ ልዩ ልደት ነው፡፡ (ወንጌል አንድምታ፤ ከቀድሞ አባቶች ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ንባብና ትርጓሜው ፤ 1997፤ በትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ድርጅት የታተመ፤ ገጽ.44) እርሱ የተወለደው ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ፤ ከሰው ነው፡፡ ለዚህም ነው ወንጌላዊው “ቃል ሥጋ ሆነ” ብሎ ሳያበቃ ፤ “ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ” ሲል የእኛን ሥጋ መዋሐዱን በማስረገጥ የተናገረው፡፡(ዮሐ.1፥1 ፤ 14)

Friday 2 January 2015

ኢየሱስ የማታሳስት በር


                  Please read in PDF

መግቢያዬ፣
መውጪያዬ፣
ሆነህ ስላየሁህ በህይወት ዘመኔ፤