በእግዚአብሔር ጸጋ ፍጹም አምናለሁ፤ ዳሩ ግን በ”ብልጽግና”
ወንጌል አንዴ የተለከፉትን፤ እነርሱን በንስሐ ማደስ እጅግ ከባድ ነው፡፡ ምክንያቱም ትምህርቱ፣ የቀደሙትን ሰዎች አዳምና ሔዋንን
እንዳሳተው አሳች፣ አንተን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስተካክል አጋንንታዊ ትምህርት ነውና፡፡ ለዚህ ነው ዶክተር ተካልኝ “የጸሎት-ንግድ
ቤት” በሚለው መጽሐፉ እንዲህ በማለት የሚጠይቀውና የሚመልሰው፣
“… በእግዚአብሔር ማመንን ወደ “እንደ እግዚአብሔር ማመን” ቀይሮ ክርስትና የሚባል እምነት ይኖራልን? ፈጽሞ፤ … የትምህርቱ ኹሉ ነገር እምነት በሚባል አስገዳጅ ኃይል እግዚአብሔርን ጨምሮ ነገሮችን ኹሉ ለሰው ጥቅም ማስገዛት እና ማስገበር ነው፡፡” (ገጽ 60) ይላል፡፡