Jechoota gurguddoo dubbii Waaqummaa keessaa inni tokko Furii dha. Kakuu duraa keessatti qabeenyi lubbuudhaaf furii ta'e caqasameera (Fkn. 13:8); warri Israa'el lafa ykn mana isaani erga gurguratan booda furii gochuudhaan deebisifachuu danda'u ture (Leewo. 25:24-34). Raajiin Muuseen ummata Israa'el gabrummaa Gibxi jalaa sababa bilisa baaseef furii ykn bilisa baasaa ta'eera ykn jedhamee yaamameera. (Ho. Erg. 7:35).
Saturday, 26 April 2025
የትክክለኛ ቤዛ መስፈርቱ ይኸው!
በአጭር ቃል ስብከት፣ "... እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤" (1ቆሮ. 1፥23) እና "ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤" 1ጢሞ. 1፥15) የሚለው ብቻ ነው። ቅዱሳን ሐዋርያትም፣ የስብከታቸው ማዕከል፣ "መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።" (ሐ.ሥ. 4፥12) የሚል ነበር።
Thursday, 24 April 2025
ሄኖክ ኃይሌ፣ “ሰባኪ” ከኾነ ከመጽሐፍ ለምን አይጠቅስም?
ሄኖክ ሃይሌ፣ ለጳጳሱ አባ ገብርኤል በመለሰው መልስ ውስጥ እንዲህ የሚል ንግግር አለው፣
“ያስተማሩት የታሰበበት ክህደት ነውና … ሙሴ ቤዛ
በተባለበት መጽሐፍ ቅዱስ እያመኑ ድንግል ማርያም ቤዛ አትባልም ላሉት ጳጳስ ቅዱስ ሲኖዶስ ቤዛ ሲሆናቸው ማየት አንፈልግም።
ጠንከር ያለ ቀኖናዊ እርምጃ እንጠብቃለን።”
ነገሩን
ግልጽ ለማድረግ፣ ሙሴ “ቤዛ” የተባለበትን ዐሳብ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማየቱ እጅግ መልካም ነው። በታላቁ መጽሐፍ ውስጥ
በእስጢፋኖስ አንደበት፣
“
… ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።” (ሐ.ሥ. 7፥35)
ተብሎ ተጠቅሶአል። ስለ
ሙሴ ጥቂት እንናገር፣ ሙሴ በግብፃዊቷ ልዕልት ቤት ያደገ ዕብራዊ ሰው ነበር (ዘጸአት 2፥1-10)። ለእኛ ባልተገለጠና
የመጀመሪያው ዘገባ በማይገልጠው መንገድ፣ ሙሴ ሕዝቡን ከባርነት ነፃ ለማውጣት እግዚአብሔር እንደ ላከው ያውቅ ነበር (ሐ.ሥ.
7፥25)። በመጀመሪያ ሙከራው ሙሴ ዕብራዊውን እየደበደበ ያለውን ግብፃዊ ሰው ገደለ። በማግስቱ፣ እስራኤላውያን ረድኤቱንና
ሥልጣኑን አለመቀበል ብቻ ሳይሆን ግድያውን እንደሚያውቁ ተገነዘበ። ፈርዖን ሳይገድለው ሙሴ ወደ ምድያም ምድር ሸሸ (ዘጸ. 2፥11–15)።
Wednesday, 23 April 2025
"ሊቃውንቱና መምህራኑ" እንዴት ከመጽሐፉ ተራራቁ?!
ደግሜ
ቤዛ ለሚለው ቃል የተሰጠ ፍቺ ልጥቀስ፣ " ... ቤዛ ማለት፦ “... ካሣ፣ የደም ቤዛ፣ አንዱ ሰው የሰውን ደም
ስለሚያፈስሰው ለውጥ ወይም ዋጋን፣ ገንዘብን፣ ካሣን መስጠት ወይም መዋጀት ማለት ነው።” ይላል የከሣቴ ብርሐን መዝገበ ቃላት።
(ከሣቴ ብርሃን መዝገበ ቃላት፤ 1951 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ገፅ 532)። ጌታችን ኢየሱስ ስለ ቤዝወት በተናገረ
ጊዜ እንዲህ አለ፣ "የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።"
(ማቴ. 20፥28፤ ማር. 10፥45) ብሎአል።
Tuesday, 22 April 2025
“ነይ ነይ እምዬ ማርያም… ቤዛዊት ዓለም … ስህ-ተ-ት ነው” (አባ ገብርኤል)
ከሰሞኑ
በጣም ያከራከረ አንድ ርዕሰ ጉዳይ አለ፤ ነገረ ቤዝወት። “ቤዝወት” ታላቅ ነገረ መለኮታዊ ዕሳቤን በውስጡ የያዘ አስደናቂ ቃል
ነው። በብዙዎች አንደበት የሚጠቀስ ቃል ቢኾንም፣ ቃሉ በትክክል ስፍራውንና ትርጕሙን አጊኝቷል ብዬ ግን አላምንም። ጥቂት ስለ ቃሉ
እናውጋ እስኪ!
ቤዛነት ምንድር ነው?
“ቤዛ” የሚለው ቃል፣ ከግዕዝ ቋንቋ የተወሰደ ሲኾን፣ ሰውን ከባርነት ነጻ ለማውጣት የሚከፈል ዋጋ
ወይም አንድን የተያዘን ወይም የተወሰደን ነገር ለማስመለስ የሚከፈል ዋጋን፣ ካሳን አመልካች ነው። ቤዛን
የመክፈል ሥራ ደግሞ፣ ቤዛነት ተብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሶአል። ቤዛነት፣ በበደለኛው ሰው የተወሰነውን ትክክለኛ ፍርድ
ተመጣጣኙን ዋጋ ከፍሎ ነፃ ማውጣት ነው። ስለዚህም ቤዛ ማለት፣ “በቁሙ ዋጋ፣ ካሳ፣ ለውጥ፣ ምትክ፣ ዋቢ፣ ዋስ፣ መድን፣ ተያዥ
… የመሰለው ኹሉ። [በደቂቅ አገባብ] ደግሞ፣ ስለ፣ ፈንታ፣ ምክንያት”[1] በማለት አለቃ ኪዳነ ወልድ
ክፍሌ ያብራሩታል። ከዚህ በመነሣት፦
Monday, 31 March 2025
Sunday, 23 March 2025
በአጕል ትህትና ሥጋን አትጨቁኑ!
መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ቃል፣
“… ለዚህ ዓለም መርሕ ከክርስቶስ ጋራ ከሞታችሁ፣ ታዲያ በዚህ ዓለም እንደሚኖር ለምን ትገዙላቸዋላችሁ? “አትያዝ!
አትቅመስ! አትንካ!” እንደሚሉት ዐይነት፣ እነዚህ ሁሉ በሰው ትእዛዝና ትምህርት ላይ የተመሠረቱ ስለ ሆኑ በተግባር ላይ ሲውሉ
ጠፊ ናቸው። እነዚህ ነገሮች በገዛ ራስ ላይ ከሚፈጥሩት የአምልኮ ስሜት፣ ከዐጕል ትሕትናና ሰውነትን ከመጨቈን አንጻር በርግጥ ጥበብ
ያለባቸው ይመስላሉ፤ ነገር ግን የሥጋን ልቅነት ለመቈጣጠር አንዳች ፋይዳ የላቸውም።” (ቈላ. 2፥21-23)
ይላል።
Thursday, 13 March 2025
Saturday, 8 March 2025
12 ዓመታት በጡመራ መድረክ!
“መልካሚቱም የአምላኩ እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና” እንዲል፣ ጌታ እግዚአብሔር በመልካምነቱ ባለፉት አሥራ ኹለት ዓመታት በረድኤቱ
በጽሑፍ እንዳገለግል ረድቶኛል። በነዚህ ጊዜያቶች ከእግዚአብሔር ልጅ ከክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ለመስበክ አልተመኘኹም፤ ሰብኬውም
ገና አልጠገብኩትም፤ ኢየሱስ ጽዋዬና ርስቴ ነውና ከርሱ በቀር ሌላ ምንም አያጓጓኝም፤ እግዚአብሔር አለኝ፤ በቂዬ ነው!
Saturday, 1 March 2025
“ … ውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶበታል።” (ሉቃ. 11፥39)
ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን ሲጽፍልን፣ ትኵረት
ካደረገባቸው ታላላቅ መንፈሳዊ ነገሮች አንዱ፣ ድኾችን በተመለከተ ነው። በወንጌሉ ውስጥ ኢየሱስ ቤት አልባ ድኻ ነው
(9፥58)፣ አገልግሎቱ አምነው በተከተሉት ሴቶች ይደገፍ ነበር (8፥3)፣ አገልግሎቱ ለድኾች ወንጌልን በመስበክ እንደ ኾነ
ተናገረ (4፥18)፣ ቅድስት ድንግል ማርያም ድኻ እናት መኾንዋን በመሥዋዕት አቀራረቧ አሳየ (2፥24)፣ “የተራቡትን በበጎ
ነገር አጥግቦአል፤” (1፥53) እንዲል፣ ድኾችን በብዙ እንደሚጐበኝና እንደ አልዓዛር ያሉ ድኾችን በሰማያት በብዙ ደስታ
እንደሚያከበር ማስተማሩን ጽፎልናል (16፥19)፤ ይህ ብቻ ሳይኾን ሉቃስ፣ በኤልያስ ዘመን የነበረችውንም የሰራፕታዋንም ድኻይቱን
መበለት አንስቶአል (4፥26)።
Thursday, 27 February 2025
Monday, 17 February 2025
ሕይወት ቴቪን "የእውነት ቃል አገልግሎት" ሊታደግ?
መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ቃል፣ “አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት
መልካሙን አመል ያጠፋል።” (1ቆሮ. 15፥33) ይላል። “አትሳቱ” የሚባለው ለሚያውቁና ለተረዱ አማኞች ነው። የሚባልበትም ምክንያት፣
የሚያስቱና የሚያሳስቱ ስላሉ ነው። ከክፍሉ እንደምንረዳው በቆሮንቶሳውያን መካከል ትንሣኤ ሙታንን በመናቅና በማቃለል፣ ሕይወትን፤
ዕለታዊ ኑሮን ከመብልና ከመጠጥ ጋር ብቻ ያያያዙትን “አማኞች” ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ካሉት መራቅና ኅብረታቸውን መተው እንደሚገባ
ይናገራል። ምክንያቱም ክፉ ባልንጀርነት የመልካሙን ዐመል ስለሚያጠፋ ነው ይለናል። ከበላተኛ ከጠጪ ወይም የሆድን ነገር ብቻ ከሚያወሩ
ጋር መዋል፣ ትንሣኤ ሙታንን እንድንንቅ ያደርጋሉና። በሌላ ንግግር የማይገባ ግንኙነት እንደ ጭንቁር እንደሚባላ ማስተዋል እንችላለን።
Tuesday, 11 February 2025
Fayyisuun kan Waaqayyooti!
Monday, 10 February 2025
ከአንድ ዐይነትነት የመንፈስ አንድነት ይበልጣል።
ዶግማና ቀኖና የማያሳስባቸውና የማያስጨንቃቸው፣ አንድ ላይ ያሉ አንድ ዐይነት “ኅብረቶች” ብዙ ናቸው። የሕይወት
ልምምድና የኑሮ ዘይቤ ግድ የማይሰጣቸው፣ በጋራ ግን "መንፈሳዊ የሚመስል ኅብረት" ያላቸው ጀማዎች፣ በዘመናችን
እንደ አሸን የፈሉ ናቸው። በአንድ ወቅት ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ተስማምተው አንድ ኾነው ነበር፣ ቅዱስ ጳውሎስን ለመክሰስ፤ ነገር
ግን አንድነታቸው የትንሣኤ ሙታን የዶግማ ጥያቄ ሲነሣ፣ ብትንትናቸው ወጣ፤ “... ይህንም ባለ ጊዜ በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን
መካከል ጥል ሆነ ሸንጎውም ተለያየ።” (ሐ.ሥ. 23፥7) እንዲል።
Friday, 31 January 2025
ወደ አዲስ ኪዳናዊ የመመለስ ተሐድሶ ያስፈልገናል!
ከዚህ ቀደም የጻፍኹትን ልጥቀስ፣
“ተሐድሶ፣ “ሐደሰ” ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ
ሲኾን፣ ትርጕሙ “አዲስ አደረገ” የሚለውን ትርጕም ታሳቢ ያደርጋል። በተገብሮ (Passive) “ተሐድሰ” ከሚለው ቃል ደግሞ፣
“ተሐድሶ” የወጣ ሲኾን፣ ትርጕሙ “አዲስ ኾነ” ማለት ነው። ስለዚህም ስያሜው ድርጊትን እንጂ ተቋማዊነትን ወይም አደረጃጀትን ፈጽሞ
አያመለክትም።” [1]
Monday, 27 January 2025
ተሐድሶም አብሮ እንዳይገፋ!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ጥር ፲፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ የቤተክርስቲያ
መብትና ጥቅም ለማስከበርና
የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በጥብቅ እየሠራች መኾኑን በራሷ የትስስር ገጾች አመልክታለች።
ቤተክርስቲያኒቱ በተለይም፣
“ ... ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አካላት መብትና ጥቅሟን የሚነኩ
* በአስተምህሮቿ
* በዕምነቷ
* በንዋያተ ቅድሳቶቿ ላይ መሰረታቸውን ያደረጉና ትዕግስቷን የሚፈታተኑ ክብርና ሉአላዊነቷን የሚዳፈሩ
እኩይ የትንኮሳ ተግባራት እየተፈጸመባት ይገኛል ...”
በማለት ገልጻለች።
Saturday, 25 January 2025
Monday, 6 January 2025
እረኞችና ሰብዓ ሰገል
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ
ከቅድስት ድንግል መወለድ፣ ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ ያልተሰማ እጅግ አስደናቂ ምስጢር ነው። ንጉሠ ሰማይ ወምድር ክርስቶስ ኢየሱስ
ሲወለድ፣ ሊቀራረቡ የማይችሉ አካላት በአንድነት ተገናኝተዋል። ኀጢአት በሰዎች መካከል ልዩነትን አድርጎአል፤ ባለጠጋና ድኃ፤
ታላቅና ታናሽ፤ አዋቂና መሃይም፤ አለቃና ምንዝር፤ ጌታና ሎሌ፤ ጥቁርና ነጭ፤ ገዢና ተገዥ … በሚል።