የ“ሥፍረ ዘመን አማንያን” ትምህርቶቻቸው ከተመሠረቱባቸው መሠረታዊ ትምህርቶች አንዱ፣ የሕግና የጸጋ አስተምኅሮአቸው ነው። ጸጋን እጅግ ከመለጠጣቸውም የተነሳ፣ ስለ ሕግ አንዳችም ነገር እንዲነገር አይፈልጉም፤ ከዚህ ስሑት አስተምኅሮአቸው ነጻ የወጣው ሚስተር ማውሮ ሲናገር እንዲህ ይላል፣ “ … በእግዚአብሔር ቅዱስ ሕግ ላይ የሚጥሉት ምኞቶች በጠቅላላው ሙሉ እና ከባድ ደግሞም የተሳሳተ መግለጫ ነው።”
እንደ እውነት ቃል አገልግሎት አስተምህሮ፣ ሕግ
አንድ ራሱን የቻለ ሥፍረ ዘመን (dispensation) ነው። ዘመኑም ከሙሴ ዘመን ጀምሮ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ደሙን እስካፈሰሰበት
ጊዜ ያለውን የሚያጠቃልል ነው። በርግጥ፣ ሕግን በሥፍረ ዘመንነቱ ማስቀመጣቸው በራሱ ችግር ነው ብዬ አላምንም። ኹሌም የስህተት
ትምህርት ችግሩ የሚፈልቀው፣ መብራራት ሲጀምር ነው። እናም እቃአዎች(እውነት ቃል አገልግሎት ለማለት ነው) የሕግን ሥፍረ ዘመን
ሲያብራሩ፣ ኢየሱስን ጭምር የሕግ ሥፍረ ዘመን አካል አድርገው ከማቅረብ ይጀምራሉ።
ከዚህም የተነሣ፣ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይልቅ፣
ጸጋን አብዝቶ ያብራራውና የገለጠው ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ኾነ በትምህርቶቻቸው በብዛት ሲገለጥ እንመለከታለን። ይህ ዐሳብ ኹለት አደገኛ
ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶችን በውስጡ አዝሎአል፤ ይኸውም፦
1.
ኢየሱስን የሕግ አካል ያደርገዋል፦ ጌታችን ኢየሱስ ወደ እኛ
በመምጣቱ የእግዚአብሔር ጸጋ በምልአት ተገልጦአል፤ ቅዱስ ወንጌል፣ “ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ
ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።” (ዮሐ. 1፥14) እንዲል፣ ጌታችን ኢየሱስ ከቅድስት ድንግል በነሣው ሥጋ ሲገለጥ
ጸጋ፣ እውነት፣ ኀይል፣ ብርሃንን በክብር ተመልቶ ነው።
ቅዱሳን ሐዋርያት “ተገለጠ” ብለው የሰበኩት የእግዚአብሔር
ጸጋ፣ ክርስቶስ ኢየሱስ ከሰማያት ከእግዚአብሔር ዘንድ ግልጥ በኾነ መንገድ፣ “የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ
እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።” (ማር. 10፥45) ብሎ እንደ ተናገረው በፈቃዱ ነፍሱን ስለ እኛ ሊሰጥ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ
ነው። ስለዚህም ከመስቀሉ በፊት የነበረው አገልግሎቱ ኹሉ፣ የመዳናችንና የጽድቃችን አካል ነው።
የክርስቶስ በጸጋ ወደዚህ ምድር መምጣት፣ የማይለወጠው
የእግዚአብሔር ፍቅርና ታማኝነት በአብሮነት መገለጣቸውን የሚያመለክት ነው።
2.
የቅዱስ ጳውሎስ መልእክቶች ምንጫቸው ወንጌላት ወይም የጌታችን ኢየሱስ ትምህርት፣
ሕይወትና ሥራ እንጂ ሌላ የተለየ መገለጥ አይደለም። ቅዱሳት መጻሕፍት የሕግን አላስፈላጊነት ሲናገሩ አንሰማም። ቀላል ምሳሌ ብናነሳ፦
የእግዚአብሔር መግቦታዊ ጸጋ የተፈጥሮ ሕግን ሳይቃወም ይሠራል፤ በሌላ በኩል ደግሞ መግቦታዊ ጸጋው የተፈጥሮ ሕግጋትን ወደ ፍጽምና
ለማምጣት የበላይ ኾኖ የሚሠራም ነው። ይህ ጌታ በትውልዶች ውስጥ ፈጽሞ አልተለወጠም።
በወንጌልና ሕግጋት ተብለው በሚጠቀሱት የብሉይ ኪዳን
“ውሱን መጻሕፍት” መካከል ያለውን ጤናማ ድንበር ደግሞ መረዳት ነገረ ድኅነትን በተገቢ መንገድ ማስተዋልን ያመጣል። ነገረ ድኅነትን
በትክክል ማስተዋል ደግሞ ስለ እግዚአብሔርና ስለ ፍጥረቱ ተገቢ ወደ ኾነ እውቀት ላይ ያደርሳል።
ምንም እንኳ በክርስቶስ ኢየሱስ የዳንን ሕሕቦች፤
ከሕግ እርግማን የተዋጀን ወገኖች ብንኾንም፣ የፍቅር ሕ ዕዳ የሌለብን መረን ሕሕቦች አይደለንም፤ ሸክም ቢራገፍልንም፣ ርሱ ያሸከመን
ቀሊል ሸክም፤ ልዝብ ቀንበር ያልተሸከምን አይደለንም፡፡ ለክርስቶስ ወደንና ፈቅደን የተገዛን የጸጋም የሕግም ባሮች ነን!
“ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ለሚወድዱ ሁሉ ጸጋ ይሁን።”
(ኤፌ. 6:24) አሜን።
No comments:
Post a Comment