Saturday, 25 January 2025

ጥበብ ልቆ ታየ

Please read in PDF 

የጠቢባን ምክር የአስተዋዮች ጥበብ

የኀያላንና ባላባቶች መዝገብ

የብርቱዎች ትምክህት የብዙዎች ክብር

ዝናና ጀግንነት ልዕልና ወንበር

ውበት ብልጥግና የዚህ ዓለም ነገር ...

መሲሑ ሲመጣ

ረብና ጥቅም አጣ

ሥጋ የለበሰ ኹሉ እንዳይመካ

የኾነውን ነገር መሲሑ አጠፋ።

 

ከዚህ የተነሳ!

የተናቀው ከብሮ ምናምንቴው ቆመ

ደካማው ተመርጦ ምርጡ ግን ደከመ

የዓለምን ጥበብ ሊያሳፍር ብሎ

ጥበብ ልቆ ታየ በሕፃናት አእምሮ!

 


No comments:

Post a Comment