“መልካሚቱም የአምላኩ እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና” እንዲል፣ ጌታ እግዚአብሔር በመልካምነቱ ባለፉት አሥራ ኹለት ዓመታት በረድኤቱ
በጽሑፍ እንዳገለግል ረድቶኛል። በነዚህ ጊዜያቶች ከእግዚአብሔር ልጅ ከክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ለመስበክ አልተመኘኹም፤ ሰብኬውም
ገና አልጠገብኩትም፤ ኢየሱስ ጽዋዬና ርስቴ ነውና ከርሱ በቀር ሌላ ምንም አያጓጓኝም፤ እግዚአብሔር አለኝ፤ በቂዬ ነው!
ቀሪዬ ዘመኔ በርሱ ይወረስ፤ ርሱ ብቻ ይድመቅበት፤ ስንዝር የምታህለው የሕይወቴ
ክፍል እስከማትቀር ድረስ ኢየሱስ ብቻ ይክበርበት፤ ይግነንበት፤ እኔ እጅግ አንሼ፣ ርሱ ልቆና ተልቆ ይታይበት! አሜን።
በነዚህ ዘመናት ሳትለወጡ፣ በአገልግሎት አብራችሁኝ ያላችሁ ወንድሞችና እህቶች
ጌታ ጸጋውን ስላበዛላችሁ ጌታን እጅግ አመሰግናለሁ! ስሰንፍ በማንቃት፣ ስደክም በመምከር፣ ሳፈገፍግ በማበረታታት፣ ስቸገር በመርዳት
… ቀኛችሁን የሰጣችሁኝን ስሞቻችሁን ጠርቼ ዋጋችሁን አላሳንስም፤ ኢየሱስ በሰማያት በጌጥና በክብር አክሊል ይመልስላችሁ! አሜን።
“ጌታችንን
ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ለሚወድዱ ሁሉ ጸጋ ይሁን።” (ኤፌ. 6:24) አሜን።
No comments:
Post a Comment