Tuesday, 31 March 2020

ቀጥ ያለ ኦርቶዶክስ!

መብራቴ እንደ በራ ጨዌ እንደ ሰማ
ውስጤ እንደ ፈለገ የክብርህን ግርማ
አጊኝቼ ልራብህ አይቼ ልናፍቅህ

መጥተህ አጊኝተኸኝ ያጓጓኝ መምጣትህ
ትከለኝ በስምህ ቅጠረኝ በደምህ
ቀጥ ያለ ኦርቶዶክስ ልኹን አገልጋይህ።
ኦርቶዶክስ አድርገኝ የትምህርትህ ሎሌ
ሕይወቴም ይመስክር አንተን መከተሌ
ስትመጣ በዕፍረት እንዳላቀረቅር
ገብር ኄር አድርገኝ የስምህ ምስክር፤
አድርገኝ ኦርቶዶክስ የስምህ ተከታይ
አዚም ተገፎልኝ ቀጥ ብዬህ እንዳይ!


(ኦርቶዶክስ የስሙ ትርጉም ቀጥተኛ አስተምኀሮን የሚወክል ሲኾን፣ በዚህ ግጥም ውስጥም በጌታ ኢየሱስና በቅዱሳን ሐዋርያት፣ በነቢያትም የተሰበከውን እውነተኛ አስተምኅሮን እንዲገልጥ የተጠቀምኹት ነው።)

1 comment:

  1. መናፍቅና ተሃድሶ በስመ ኦርቶዶክስ አይጠራም። ጴንጤ ነኝ ብትል መልካም ነበር ግን ምን ያደርጋል የበግ ለምዱን ማውለቅ አልፈለግህም ልጅ አቤኔዘር!

    ReplyDelete