Saturday 21 March 2020

ደብረ ዘይት - ይመጣል ኢየሱስ

Please read in PDF

ርኩሰት እንዳየለ ሞት እንደ በረታ
ዓመጽ ገደብ አልፎ ኹሉን እንደ ረታ
የደዌ ነጋሪት የሕመም ጉሰማ


ድምጹ ገኖ ገኖ ዳር እንደ ተሰማ
ውድቀት እየናረ ተስፋ ተስለምልሞ
የደከመው ይባስ ዝሎ ተጥመልምሎ
የእውነት ፀሐይ ጠልቃ
የሐሰት ቤቷ ደርታ
ሞት በደጅ አድብቶ
ጻድቅ ፈርቶ ተብቶ
እንዲህማ አይቀርም እንደ ጨላለመ
ኀያል በብርታቱ ፍሞ እንደ ጋመ
አይኾንም ፍጻሜ እንደ በሸቀጠ
የመከሩን ሁዳድ አረም እንደ ዋጠ!
ይመጣል ኢየሱስ እያበራ ደምቆ
በሚያስደንቅ ግርማ በብርሃን ተከቦ
ይመጣል አይቀርም አሜን ማራናታ
በእርሱ ለታመኑ ፀሐይ እያወጣ!
አሜን፡፡

5 comments:

  1. amen amen amen

    ReplyDelete
  2. God bless you

    ReplyDelete
  3. God bless you

    ReplyDelete
  4. Amen amen amen my God bless you dn

    ReplyDelete
  5. እግዚአብሄር አብዝቶ ይባርክህ። በርታ ቀጥል እባክህ

    ReplyDelete