Wednesday 4 March 2020

በማንቂያ ደወል አንቅተንስ … ?!

Please read in PDF

  ባለንበት ወር “የማንቂያ ደወል” የሚሉ ጉባኤያት፣ በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በተደጋጋሚ ከአድባራት እስከ ደብራት ሲደረጉ እያየን ነው። ከተለያዩ ጉባኤያት “መምህራን” አንደበት እንደ ሰማነው፣ የጉባኤያቱ መነሻ ዐሳብ፣ ሕዝቡን ስለ ሃይማኖቱ ማንቃት፣ በተለይ አኹን እየደረሰ ካለው ውጫዊና ውስጣዊ ተጽዕኖ በመከላከል፣ ሃይማኖቱን እንዲጠብቅና ከፍ ሲልም “ሰማዕት” እንዲኾን ማድረግ የሚሉና ሌሎችም ጽኑ አቋሞች አሉት። ነገር ግን ለጉባኤያቱ መደረግ እንደ ሥረ ምክንያት የተነሡትና እንደ ጭብጥ የተያዙት ዐሳቦች፣ ከክርስትና አስተምህሮ እጅግ የራቁና መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ያላቸው አይመስሉም


የማንቃቱ በጐ ተጽዕኖ!

  የብሉይ ኪዳን ነቢያት ሕዝቡ በኀጢአት ሲዘፈቅና ሲዋጥ፣ እግዚአብሔር የተግሳጽና የምክር ቃሉን አስታጥቆ ወደ ሕዝቡ ከኀጢአታቸው እንዲነቁና ንስሐ እንዲገቡ ይልክ ነበር። ከእውነተኞቹ ነቢያት ይልቅ ሐሰተኞቹ ነቢያት አስቀድመው ሰፊውን ስፍራ በመያዝ ስለሚታወቁ በአብዛኛው እውነተኞቹ ነቢያት የመሰማትና የመደመጥ ዕድል የላቸውም፤ ሐሰተኞቹ በቊጥራቸውም ብዙ በመኾናቸው ብዙውንም ሕዝብ ይደርሳሉ፣ እኒህ ሐሰተኛ ነቢያት ኾን ብለው ገንዘብን ፍለጋ፣ አንዳንዶች በፍጹም ስህተት በመጠላለፍ ከገዛ ልባቸው አንቅተው፣ ሌሎች ደግሞ ከአጋንንት ቀጥታ በመስማትና በመቀበል ሕዝቡን ያስቱ፣ ያታልሉ፣ ከእግዚአብሔርም ይነጥሉ ነበር። በዚህ ወቅት ሕዝቡን በእውነተኛ የወንጌል መልእክት ማንቃት ታላቁን ተልእኮ በመፈጸም ለኢየሱስ መታዘዝ ነው።

   አኹን እያየን እንዳለነው፣ እንዲህ ድቅድቅ ሲኾንና አንድም ሃይ ባይ እውነተኛ አገልጋይ ሲጠፋ፣ እግዚአብሔር አንድን ብርቱና ጉምቱ አገልጋይ ያስነሣል፤ በዚህ ወቅት የሚነሡ አገልጋዮች በነፍስ ተወራርደው የሚያገለግሉ ኀያላን፣ ደፋሮች፣ በነፍሳቸው የፈረዱ ጨካኞች ናቸው። እጅግ አሉታዊ በኾነ መንገድ ደግሞ፣ እግዚአብሔር አምላክ፣ የስህተት መምህራኑ በበዙበትና ሕዝቡ በጥቅጥቅና ድቅድቅ ጨለማ በተያዘበት ኹኔታ ውስጥ እንኳ ብርሃን መፈንጠቁን አይተውም።
  በተደጋጋሚ መንገድ፣ በአገራችን ኢትዮጵያ በተደረጉ የታሪክ ክንዋኔዎችን ከተመለከትን የምናስተውለው እውነት፣ ወንጌል እንዳይሰበክ በተከለከለ ማግስት፣ የኢየሱስ ስም አንዳይጠራ ጽኑ ተቃውሞ በተደረገ መጠን፣ ሕዝቡን የማያሳርፉና የማይታወቁ “ሰዎችና ታቦታት ወይም ክንውንና ተአምራት” በማግነንና በማድነቅ የተሰቀለውን ኢየሱስ ለመጋረድ ጨለማው ይበልጥ እንዲሰፋ ባደረጉት መጠን … ወንጌል ነጥሮ፣ አሸንፎ፣ አይሎ፣ ድል ነሥቶ፣ በኀይል ለመውጣቱ እነሆ እኛ ራሳችን ሕያዋን ምስክሮች ነን! ስለዚህ የጨለማው መደቅደቅ አይጨንቅም፤ ብርሃን መፈንጠቁ አይቀርምና፤ የሚሸቃቅጡት፣ የራሳቸውን ጥቅም የሚያሳድዱና እጅግ አታላዮች ግን እኒህ በኢየሱስ የመስቀሉ ሥራ ላይ የሚቆምሩና የሚዘብቱ ናቸው!
  እናም የማንቂያ ደወል ተብሎ ወንጌልን በማይገልጥ፣ የተሰቀለው ክርስቶስን በማይሰብክ መንገድ መከናወኑና መተግበሩ፣ ጨለማው ይበልጥ እንዲበረታ መሰበኩ በራሱ ለወንጌል በጐ ተጽዕኖ አለው። ኹል ጊዜ የሚደነቀው ብርሃን ከመውጣቱ በፊት፣ ዓይንን የሚቆጠቁጥ ጨለማ መውጣቱ እሙን ነው፤ እግዚአብሔር፣ “እኛ እንችላለን፣ ኀይሌ አይደክምም፣ ጥበቤ አይሸነፍም!” ያልንበት ከንቱ ጥረታችን ሙጥጥ፣ ርግፍ፣ ኩትኩት እንክትክት ብሎ እስኪያልቅ ይጠብቃል፤ ከዚያም ደክመን፣ ዝለን፣ ተዝለፍልፈን፣ ተዘርረን አቅላችንን ስተን ስንወድቅ እግዚአብሔር ሊሠራ ይጀምራል።  

የአንቂዎቹ ነቅ!

  እንደ አንቂ ራሳቸውን የሚቈጥሩ ሰዎች ወይም “መምህራን”፣ “የማንቂያ ደወል” በእጃቸው ስላለ ብቻ፣ ራሳቸውን እንደ አንቂ የቈጠሩ እንጂ፣ በራሳቸው ዝግጁና ትክክለኛ የማንቂያ ቃልና ድምጽ ያላቸው አይደሉም። በአጭር ቃል ከፖለቲከኞች በምንም አይለዩም፤ የተከናወነውንና ደረሰብን የሚሉትን ግፍና በደል በማጮኽ፣ ሕዝቡን ለበቀልና ለጥላቻ ያዘጋጁታል እንጂ ለንስሐና ለኀጢአት ሥርየት የሚያዘጋጀውን የመዳንና የጸጋ ወንጌል ሲሰብኩ፣ ሲያውጁ፣ በዚህም ቅዱስ ቃል ሕዝቡን ሲያጽናኑና በጽድቅ እንዲበረታ ሲያደርጉ አንመለከትም።
   አንቂ ነን ያሉቱ ወይም እንደ አንቂ ራሳቸው የሾሙት፣ የሚያነቃ፣ የሚያጠራ፣ የሚቀድስ፣ የሚገርዝ ቅዱስ ቃል የላቸውም፤ ዓውደ ምሕረቱ ስለ ተደላደለላቸው እንጂ የምሕረቱ ባለጠግነት የተገለጠበት ቅዱስ ቃሉን ለመስበክ የተማሩም የታጠቁም አይደሉም። ሕዝቡን ለበለጠ ጨለማ አዘጋጁት፣ ማገዱት፣ አደላደሉት እንጂ ከገጠመውና ካገኘው መከራና ጭንቀት፣ ሕማምና ሰቆቃ፣ ውስጣዊ ጣዕሩ የሚያሳርፍ አንዳች ነገር የላቸውም፤ የገዛ ዐሳባቸውን እንጂ፣ እንደ ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ዐሳብ ፈጽሞ ሳያስቀሩ፣ ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ንስሐንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ማመን የሚናገሩ አይደሉም (ሐዋ. 20፥20-21፡ 27)።

የተነቀፈው ተልዕኮና ግዴታ

   ለሕይወት ግድ የለሾች ነን፤ ምን ዐይነት ኑሮ እንደምንኖር ሳንጨነቅ፣ የተሸቀጠና የወየበ፣ መናኛና ገለባ “ወንጌል” አቅርበን … ሰው ሕይወት አልባና ለማዳ ዓመጸኛ ሲኾን ለምን እንዳልገደደን እጅግ ያስደንቃል። በኢየሱስ የወንጌል ተልእኮ ላይ እየዘበትንና እየዋሸን ቅንጣት ታህል አይሰቀንም፤ ቅዱሱን ወንጌል አፉን ሸብበን፣ እኛ ስንናገር፣ በዓውደ ምሕረቱ ያሻንን ስንዘላብድ የተሰማንና ያወቅን፣ ወንጌልንም የሰበክን መስሎናል። ሕይወታችን ያላወጀውን ወንጌል፣ በመፈክር ማነሣሣት፣ አጃቢና ተከታይ በማብዛት ለመስበክ ማሰብ እንዴት ያለ ተላላነት ነው?!  
   ወንጌላቸው ሾተላይ ተጣብቶታልና አያፈራም፤ የኢየሱስን ወንጌል ንቀው ነቅፈውታልና “ኀይል አልባ በኾነ አምልኮ” እንዲያው ሲጠሩት እንሰማዋለን እንጂ፣ ለእነርሱ ከአርሴማና ከፍጡራን እንደ አንዱ አድርገው ከማቅረብ በቀረ፣ ብቸኛ ቤዛ፣ አንድያ መድኀኒት፣ የመጨረሻው መገለጥ፣ ለኀጥአንም ለጻድቃንም የመጣ አንድ ጽድቅ … እንደ ኾነ ደፍረው አይሰብኩትም፣ ጨክነው አይላኩለትም፤ ይህን ታላቅ ተልእኮ ለመላው ዓለም አይናኙትም፤ አያውጁትም። ስለዚህም ኢየሱስ ለቤተ ክርስቲያን የሰጠው ታላቁ ተልእኮ ፈጽሞ ተልእኮና ግዴታቸው፤ ሕልማቸውም አይደለም!

ተነቃቂዎቹ ነቅተው ምን ይጨብጡ?!

   “እናነቃለን!” የሚሉ አካላት የሚያነቁበት መሣሪያቸው፣ ኢየሱስና ቅዱስ ወንጌሉ አይደለምና ለሚያነቋቸው ምዕመናንና ምዕመናት የሚሰጡት አንዳች ነገር የላቸውም። የወንጌል ዋና ዓላማ፣ ሰዎች ወደ አዳኛቸው እንዲመጡና ከከባዱ የኀጢአት ሸክም በማረፍ ላዳናቸው ጌታ ፍጹም በመታመን ደቀ መዛሙርት እንዲኾኑ ማድረግ ነው። ነገር ግን “በማንቂያው ደወል” ሸንጎ፣ የደመቀውና ዋናው አዋጅ የጌታ ኢየሱስ ቤዛነትና ብቸኛ ፍጹም አዳኝነት አይደለም። ይህን መናገር ካልቻሉ ደግሞ፣ ተነቃቂዎቹ ቢነቁም በዕውር ድንብር ይቅበዘበዛሉ እንጂ ወደ ዋናው መድኀኒት አይመጡም፤ አያገኙትምም!
   እናንት እንድትነቁ የምትወተወቱ ኹላችሁ ሆይ! እንዲህ እንላችኋለን፤ “እኔ ሕያው ነኝና ኃጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኃጢአተኛው ይሞት ዘንድ አልፈቅድም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ተመለሱ፥ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ?” (ሕዝ. 33፥11)።

በጐውን ዕድል ለወንጌል እንጠቀመው!

  ቤተ ክርስቲያን “የማይወሰደውን በጐ ዕድል” ለምዕመናን ዘወትር ማቅረብ አለባት፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል የኾነውን፣ መዳን ያለበትን፣ ለሰዎች ኹሉ የዘላለም ሕይወት የሚሰጠውን፣ ቅዱሱን ቃል ማወጅና መመስከር ይገባታል፤ የምዕመናን በ“አብያተ ክርስቲያናት” የመሰባሰባቸውም ዋና ምክንያትም፣ የጌታ ኢየሱስን ተልእኮ አጥርቶ በመስማት፣ ጨውና ብርሃን አልባ ወደ ኾነችው ዓለም ደቀ መዛሙርትን መላክ ነው። ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የግል ሕይወታቸው እንኳ ባልጠራና እጅግ በሚብስ ጥፋት በተያዙ አገልጋዮች መወረሯን ስናስውል ደግሞ የጌታ ኢየሱስ ተልእኮ ምን ያህል እንደ ተዘነጋ ማስተዋል አይከብድም። ዛሬ ሕዝቡ እኒህን አገልጋዮች የሚሰማው ዕረፍትን ፍለጋ በመቃተት እንጂ የሚሰሙት ተመችቶት ወይም አሳርፎት አይደለም።
   ዛሬ ላይ እጅግ ተርቦ የመጣውን ይህን ሕዝብ፣ ቅዱሱን ወንጌል እንደሚገባው በማስተማር በጎውን ዕድል ለመጠቀም ባንወድድ፣ ይህ ወርቃማ ዕድል ዘወትር አብሮ የሚኖር አይደለም። እናም ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ላይ እንዲህ ለሚጎርፈው ሕዝብ፣ እውነተኛውን ወንጌልና አዋጅ ልታውጂለት ይገባሻል፤ አልያ ግን በደጅ ያለው ዓመጽ ዛሬ ካለው በባሰና እጅግ በከፋ ኹኔታ ማየሉና ዳፍንት ለመኾኑ ተንባይ መኾን አያሻውም! በእንጀራና በወዳጅነት ታስራችሁ፣ ወንጌል ከመስበክ ተሸብባችሁ ያላችሁ ሆይ! ኢየሱስ በመጣ ጊዜ እንጀራና ወዳጅነት ቤዛና አለኝታ አይኾናችሁምና ነቅታችሁ ወንጌልን ብትሰብኩ አይበጃችሁምን!?
ማጠቃለያ

  ቤተ ክርስቲያን ከቅዱስ ቃሉና ከመንፈሱ የተቀበለችውን እውነተኛ የማንቂያ ደወል ወደ ሕዝቡ ልታመጣ ይገባታል። ቀኑ ተዋግዶአል፣ ዓመጻው እያየለና ክፋቱ እጅግ እየባሰ ነውና፣ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛውን የማንቂያ የኢየሱስን የወንጌል ደወል አሰምታ ልትናገር ይገባታል፤ በቃል ከመናገር በዘለለም፣ በሕይወትም ጭምር ልትመስክር ይገባታል! ለዘመናት ቤተ ክርስቲያን ለአብ አንድያ ልጅ ክብርን የማያመጣ እጅግ የሚያሳዝኑ ተግባራትን ስትሠራ ኖራለች፤ ነገር ግን ዛሬም እንዲኹ በትላንቱ መንገድ እየባሰች፣ እንኳን መንፈሳዊ እሴት፣ ማኅበራዊ እሴትን የማያከብሩ “አገልጋዮች” በማሠማራት ከደነደነች አገልግሎቷ በፍርዱ ዙፋን ፊት ቀርቦ መልስን ትሰጥበታለች። እናም ቤተ ክርስቲያን ሆይ! ለእግዚአብሔር ክብር ያልሞከርሽውና ያላደረግሽው ብዙ፤ እጅግ እልፍ ነገር አለና እባክሽን ተነሺ!
“የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ።” (ኢሳ. 54፥2)
ጸጋና ሠላም በክርስቶስ ኢየሱስ ይብዛላችሁ፤ አሜን።

48 comments:

  1. ante yematreba

    ReplyDelete
  2. እኔ የሚገርመኝ እኛ ከእንቅልፋችን በነቃን የመናፍቁ መቃጠል ነው!

    ReplyDelete
  3. ምሥሉም ለባሹም የኛ ናቸው የሠሞኑ የማንቂያ ደውል እላያቹ ላይ የተደበቀውን አጋንት ቀሠቀሠው ልመዱት ምን ይደረጋል!

    ReplyDelete
  4. ያላዋቂ ነህ ምን ለምን መጠቀም እንዳለብ እራሱ በመጀመሪያ ጠንቅቀህ እወቅ የማናቸውን ምስል ከዚህ ጋር ምን አገናኘው ሞኝ ስለ መፅሀፍ ቅዱስ ሳታቅ ጥላቻ ብቻ ለመስበክ ፀሀፊ አትምሰል

    ReplyDelete
  5. Tew tew misemak yelem yemtsihaf kedusen kal lerasek endimechi argek atletefew!!!! Lalochi hayalan yetewahedo legochi endineku teri myaderg sebaki wengal nw eshi!!!!!!

    ReplyDelete
  6. Menew geremehe egna eko yepasetor photo yeteletefebete yetashege weha tsebele new tebelene alegezaneme sare mebelateme egna ga yeleme gebito

    ReplyDelete
  7. Ye protestant emnet ena yene anditua ye tsegure zelela mizan lay biwetu yene anditua tsegur mizan tidefalech......

    ReplyDelete
  8. Minew tekaxelachu demosi iyesusin yeti abaki takiwalew dedebi hula zimi bilachu sarun gaxuti inamite kebiti hula

    ReplyDelete
  9. ሰይጣን ሁሌም መነሻውም መድረሻውም ግራ ነው ማንቂያው ካልገባህ እውነቴን ነው አንተ በድን ነህ

    ReplyDelete
  10. እኔ ከመናፍቅ የሰለቸኝ ቢኖር ጌታ እሚለው ውሽት ወይምማስመሰል እና ጥቅስ እሚሎት ነገር

    ReplyDelete
  11. ምን አገባህ

    ReplyDelete
  12. ውይ መናፍቆቾ አናተ አስስቶች

    ReplyDelete
  13. Like እወድሀለሁ ወንድሜ ተባረክ

    ReplyDelete
  14. አንቴ እስካሁን እየቴቃጠልክ ነው ?አሁንም አልበረድልህም?ተው በቃ አትችላቼውም ይቅርብህ

    ReplyDelete
  15. Eski ewbet bel, eddddd, ewketh endet mituk new,tadlehal belegn

    ReplyDelete
  16. በጣም የምደግፍልሕ ሐሳብ አለኝ እሡም ; ይሕ ሰው የወንጌል ትምሕርት አስተማሪ ቢሖንም ሁሉ የእሡን ፎቶ እየለጠፉ መፎከር ቂልነት ነው ምክንያቱም ሁሉም የሚድነው በስራው ነው እንጅ ፎቶ በመለጠፍ አይደለም። ነገር ግን አንተ አንድ ነገር ላይ ተሳስተሐል እሱም ; ሰውየው ያሻውን ያድርግ አንተ በእሱ መሰናከል የለብሕም እሱ ቢያጣፋም የጥፋቱን ቅጣት ያገኛል አንተ ግን በእሱ ላይ መፍረድ አትችልም።

    ReplyDelete
  17. እስኪ ልብ ግዛና በውነተኛው መንገድ ሂድ.....ልብ ይስጥህ አቦ....!

    ReplyDelete
  18. Antena meselothh ortodox lematfat kaseratthut sera memenun keshefenatthubn mekera lemankat newu zm bleh kemtawera agenazb

    ReplyDelete
  19. እዉነት ነው ልክ አንዳተ ከሀዲ ባለበትና ቤተከርስቲያን ውስጥ ተሸሽገው ልክ እንዳተ አቁስለዋት አሳዝነዋት ለሚከዷት መምህራን ደሞ እርግጠኛ አይደለንም ክርስቶስን መከተል ይሻለናል።

    ReplyDelete
  20. ባክህ ወጊድ ፋራ !! እሱ ማንም አልነካውም አይነኩትምም ።
    አንተም ከምትፎክር ወንጌል ለህዝብ አስተምር ። ፉከራ እግዚአብሔር አይወድም !!

    ReplyDelete
  21. ቀኑብሽ?

    ReplyDelete
  22. እዉነት ነው ልክ አንዳተ ከሀዲ ባለበትና ቤተከርስቲያን ውስጥ ተሸሽገው ልክ እንዳተ አቁስለዋት አሳዝነዋት ለሚከዷት መምህራን ደሞ እርግጠኛ አይደለንም ክርስቶስን መከተል ይሻለናል።

    ReplyDelete
  23. ፎቶና የተቀርጸ ምስል ለይተህ የማታውቅ ሰው ካንተ ጋራ ማን ያውራል??

    ReplyDelete
  24. አርቶዶክስ ላይ ፊጥ አትበሉ ዛሬ አፋችሁ አንዳመጣላችሁ የምትናገሩት አርቶዶክስ ስላለች እንደሆነ አዳሜ እወቂ የማንቂያ ደውልን ስለምትከታተሉ እናመሰግናለን ግን ከልባችሁ ውስጣችሁ ቤት የሰራውን ዲያቢሎስን አስመጥታችሁ ድንግል ማርያምን ከነልጅዋ አስገብታችሁ ይሁን

    ReplyDelete
  25. አሁን አንተም ሀይማኖት አለኝ ብለክ ነው የምታስበው? ደግሞ ጌታ ጌታ ይላል እንዴ።።

    ReplyDelete
  26. ተነቅቶብሃል !የሌላ ስም አታጥፋ ወይም አታጥፊ

    ReplyDelete
  27. ለማያውቅ ሰው እንዲህ ነው ማለቱ በድንጋይ ላይ ውሀ እንደመድፋት ነው።። እንስሳት ነህ በል

    ReplyDelete
  28. Baxiraqaa huluu midiraa manafiqii huluu tancacuu

    ReplyDelete
  29. ወዳጄ፣ይሄ፣እኮ፣ከነምህረተአብ፣ጋር፣የዘመኑ፣ነጋዴ፣ነው፣የማህበረቅዱሳን፣ደግሞ፣አካፍይ፣አጉርሰኝ፣ላጉርስህ፣ቤተክርስቲያናችን፣ለነዚህ፣ወሮ፣በሎች፣እንኳ፣ተላልፋ፣ተሰጥታለች፣የሚታደጋት፣አባትም፣ጠፋ፣ለምን፣ሁሉም፣ክብሩን፣ፈሌጊ፣ነው፣የማነቃቂያ፣የቢዝነስ፣ደወል፣ከተደወለ፣ቆይተዋል፣አባቶችም፣አልነቁም፣እነሱም፣አልጠገቡም

    ReplyDelete
  30. ለምን እራሳቹን አችሉም መናፍቅ ሁሉ

    ReplyDelete
  31. አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል።አርፋችሁ ተቀመጡ መናፍቃን።

    ReplyDelete
  32. አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል።አርፋችሁ ተቀመጡ መናፍቃን።

    ReplyDelete
  33. ከኦርቶዶክስ ላይ ውረዱ

    ReplyDelete
  34. ምን ማለት ፈልገህ ነው?

    ReplyDelete
  35. አስመሳይ ፅሁፍ መካሪ መስሎ ገፍታሪ

    ReplyDelete
  36. ከኦርቶዶክስ ላይ ውረዱ

    ReplyDelete
  37. መናፍቆች ቀናችሁ እንዴ ኑ ተማሩ

    ReplyDelete
  38. .ሁሉም ስራው ያውጣው

    ReplyDelete
  39. አንተን ብሎ መካሪ

    ReplyDelete
  40. ምነው እላያ ላይ የሰፈረው ጸበል ነካብኝ አልክሳ

    ReplyDelete
  41. ለምን እራሳቹን አችሉም መናፍቅ ሁሉ

    ReplyDelete
  42. At abenezere ye Luter telalaki denkoro banda

    ReplyDelete
  43. Ante demo yeman dikala neh dikunakim yehaset(yedablos) mehon alebet. Memihirun lemetechet ante man nek? Wengel minamin tilalek ende yediablos dekemezmur.

    ReplyDelete