Thursday 21 May 2020

የሐሰት መምህራን የማይነኳቸው ርእሶች (ክፍል ፭)

Please read in PDF


   ከዚህ ቀደም የስህተት መምህራን የማይነኳቸውን ሦስት ርዕሶችን ማለትም ኀጢአትን፣ ንስሐን፣ የእግዚአብሔርን ፍርድና ቊጣ መመልከታችን ይታወሳል፤ ዛሬ ደግሞ ቀጣዩን ርእስ እንመለከታለን።

4.
ስለ ቅድስና፦ ቅድስና በብሉይም ኾነ በአዲስ ኪዳን ውስጥ እጅግ የከበረ ዐሳብ ነው። በብሉይ ኪዳን በተለይም ከሕጉ መሰጠት በኋላ፣ ከቅድስና ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጠንካራው ቁልፍ ቃል፣ቅድስና ለእግዚአብሔርየሚለው ነው። ይህም በጥሩ ወርቅ በተሠራው አክሊል ላይ፣ እንደ ማኅተም ቅርጽ ተሠርቶ፣ ኹሉም ሰው ሊያየው በሚችል መልኩ፣ በራሱ ላይ አክሊሉን ይደፋዋል፤ (ዘጸ. 3930) በማኅተም ቅርጽ ያለውንቅድስና ለእግዚአብሔርየሚለውን ጽሕፈት ማንም ይሸሽገው ዘንድ አይችልም። ከእግዚአብሔር ጋር በመኾን፣ የተካፈልነውን ቅድስና እኛ ራሳችን እንኳ መሸሸግ አንችልም፤ ልክ ሙሴ የፊቱን ብርሃን መሸፈን እንዳልቻለው፤ (ዘጸ. 3429)

   ሌዋውያን ለታላቁ እግዚአብሔር አገልግሎት፣ በቅድስና ያገለግሉ ዘንድ ተለዩ፤ እስራኤል ኹሉ በስድነት ተለቅቀው፣ የጣዖት ጥጃ በሠሩና ባመለኩ ጊዜ፣ ሌዋውያን ከሙሴ ጋር ወደ እግዚአብሔር ፍጹም በመጠጋጋት፣ ጣዖት አምላክያንን በሰይፍ አስወገዱ፤ (ዘጸ. 3225-29) ሌዋውያን ስለ እግዚአብሔር ቅድስና ማንንም አልተመለከተም፤ እናቱንና አባቱን፤ ወንድሞቹንና ልጆቹን እንኳ አላስበለጠም። ለእግዚአብሔር ብቻ አደላ፤ ለእግዚአብሔር ቅድስና ብቻ ቀና፤ (ዘዳግ. 338) አዎን! ለእግዚአብሔር ተቃራኒ በኾነው ክፋትና ዓመጻ፣ በተቃራኒ መቆም ቅድስና ነው፤ ከዚህ የሚበልጠው ግን ከመቆም እልፍ ብሎ፣ እግዚአብሔር እንደሚወደው ፈቃዱን ማድረግና መፈጸም ደግሞ ታላቅ ቅድስና ነው፤ ሌዊ ያደረገው ታላቁን ቅድስና ነው!

   
በአዲስ ኪዳን ዐሳቡ አድጎ ከክፋት ወደ መልካምነት የመለወጥ ዕድገትን አመለከተ፤ ክርስትና መሠረቱም ጉልላቱም ቅድስና ነው፤ በምንም ስንዝር እንኳ ከክፋትና ከዓመጻ፣ ከኀጢአት ጋር አይተባበርም፤ በክርስቶስ ከኀጢአት አርነት ከወጣን፣ በትክክል ለእግዚአብሔር ባሪያዎች ነን፤ የመጨረሻው ውጤትም ቅድስና ነው፤ ያለ ቅድስና የዘላለም ሕይወትንም አናይም፤አሁን ግን ከኃጢአት አርነት ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ተገዝታችሁ፥ ልትቀደሱ ፍሬ አላችሁ፤ መጨረሻውም የዘላለም ሕይወት ነው።” (ሮሜ 622) እንዲል። ጸድቀናል፤ አርነት ወጥተናል ካልን፣ በሕይወታችን ውስጥ የቅድስናው ፍሬ ሊያብብ፤ ሊያፈራ ሊጀምር ይገባል።

   
ደግሞም፣በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ።” (2ቆሮ. 71) ለዚህም እግዚአብሔር ተላላዎችና እንደ እስራኤል ስዶች እንደዳንኾን፣ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል።” (ዕብ. 1210) ምክንያቱም፣ለርኵሰት ሳይሆን እግዚአብሔር በቅድስና ጠርቶናልና።” (1ተሰ. 47) የተጠራነው ለቅድስናና ለንጽሕና ኑሮ ነው።

   
ስለዚህም በአዲስ ኪዳን ቅድስና፦

1.
የኑሮ ዘይቤ ነው፦ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።” (ዕብ. 1214) ያለ ቅድስና እግዚአብሔር ከማንም ጋር ኅብረትን አያደርግም። ክርስቶስ ለእኛ ሲል ራሱን አሳልፎ የሰጠው፣ እንቀደስና በቅድስና እንመላለስም ዘንድ ነው። ስለዚህም ለአንድ እውነተኛ አማኝ፣ ቅድስና የየዕለት ኑሮው እንጂ የሰንበት ቀን ሥራ ወይም ትእዛዝ አይደለም።

 
ቅድስና የኑሮ ዘይቤ ነው ስንል፣ የምንኖረው የየዕለት ኑሮአችን ነው ማለታችን ነው። በዝሙት፣ በስርቆት፣ በዘፈንየሚኖርና የሚመላለስ ሰው፣ እግዚአብሔር ስለ ቅድስና፤ ስለ ንጽሕና የሰጠውን እውነተኛና ቅዱስ ትእዛዝ ይቃወማል። በዚህም ኀጢአትን የኑሮ ዘይቤው በማድረግ፣መንፈስ ቅዱስን በእናንተ እንዲኖር የሰጠውን እግዚአብሔርን ይጥላል ወይም ፍጹም ይቃወማል (1ተሰ. 48) ስለዚህም አማኞች ለቅድስናና ለንጽሕና ኑሮ ተጠርተዋል፤ የስህተት መምህራን ግን የኑሮ ዘይአቸው መሳትና ማሳት ስለ ኾነ ቅድስና ገንዘብ እንድናደርግ ከቶውንም አይሹም።

 
ከኹሉ በላይ ደግሞ፣ዳሩ ግን፦ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።” (1ጴጥ. 115-16) ያለንን ቅዱስ ጌታ ዘወትር በማሰብ፣ እንዲቀድሰንም በእምነት ዘወትር ወደ ጸጋው ዙፋን መምጣትን መዘንጋት የለብንም።

2.
ቅድስና የዳግም ምጽአቱ ማፍጠኛ ነው፦ይህ ሁሉ እንዲህ የሚቀልጥ ከሆነ፥ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ፥ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤” (2ጴጥ. 311-12) ዘወትር በቅድስና ከተመላለስን፣ እግዚአብሔርን በመምሰል በመንፈስ ቅዱስ ኀይል እንመላለሳለን። ቅድስና የኑሮ ዘይቤ ያልኾነለት አማኝ፣ እግዚአብሔርን ወደ መምሰል አይመጣም፤ ከኀጢአት ያለ መለየት መዘዙ እግዚአብሔርን አለመምሰልና ፍጹም ሞት ነው።

   
የእውነተኛ አማኝ ትምክህቱ፣ ሊወስድ የሚመጣ ጌታና አባት አለኝ ማለቱ ነው፤ ያዳነን፣ የቀደሰን፣ ያጸደቀን፣ በልዩ ክብር እንድናሸበርቅ በብዙ ጸጋውን ያፈሰሰልን ጌታ ይመጣል፤ የሚመጣው ደግሞ በቅዱስ ኑሮ እርሱን በመምሰል የጠበቁትን ልጆቹን ለመውሰድ ነው። ልጆቹ ደግሞ በቅድስና ሲኖሩና ሲመላለሱ፣ የመምጣቱን ቀን እጅግ ያስቸኩላሉ። ቅዱሳን እንኾን ዘንድ ክርስቶስ ሞቶልናል፤ የክርስቶስን ቅዱስ ኑሮ በቅድስና በመኖር እንመስለው ዘንድ ደግሞ፣ መንፈስ ቅዱስ ተሰጥቶናል።

 
እንኪያስ ጌታችን ኢየሱስ እንዲመጣ የምንሻ ኹላችን፣ ከስህተት መምህራን እንርቅ ዘንድ አይገባንምን? ምክንያቱም ሐሰተኛ መምህራን ክርስቶስ እንዲመጣ አይሹም፤ ለዚህም ተግተው የሚሠሩ አይደሉም፤ እዚሁ ተደላድለው መኖርን መርጠዋልና እርሱ በመጣ ጊዜ ክፋትና ስል ዓመጻቸውን በአደባባይ ይገልጠዋልና። ተወዳጆች ሆይ፤ ክርስቶስን በመውደድ፤ እግዚአብሔርን በመምሰል የእግዚአብሔርን ቀን መምጫ ታፈጥኑ ዘንድ፣ ኀጢአትን በመጠየፍ በቅድስና የኑሮአችሁ ዘይቤ አድርጉ፤ ለዚህም ቅዱሱ መንፈስ አለን፤ አሜን።

ይቀጥላል … 

No comments:

Post a Comment