Saturday 9 May 2020

ለምን አትነሳም?


ዝምታ መርጠሃል
ርቀህም ቆመሃል
ዓመጽ ሲበረታ



ርኩሰቱ ሲረታ
ፍትህ ድል ሲነሣ
ሞት መንጋጋው ሰፍቶ
ሲያላምጥ ሰልቅጦ
አንተ አልተነሣህም
አይተህ አልራራህም
ለምን? ...
ለምን ነው ዝምታህ
ጀርባህን መስጠትህ!
አውቃለሁ ጻድቅ ነህ
እንከን አይወጣልህ!
ግን ለምን ዝም አልከን
ጀርባህን ሰጠኸን?

ጌታ ሆይ!...
እንዲህ እናምናለን...
ጀርባህን መስጠትህ ቅርታ ቢመስልም
ለእኛ ቆስሏልና አትዘነጋንም!

2 comments: