Wednesday 15 January 2014

አድጎ ያፈራ 'ለት


ሳንጀምረው ፈርተን
ሳንቀርበው ርቀን
ሳንሻገር ቆመን
እሾሁን መንጥረን
ኩርንችቱን ነቅለን
ካ'ንድም ሁለት ሶስቴ ሳንጎለጉል ደክመን
እርፍና ሞፈሩን ቀንበርም አጣምደን
የእርሻና የዘር ወራቱን ታግሰን
ብናርስ ብንኰተኩት
በዓላማ በጽናት፤
ለእህሉ ማፋፊያ
አኑረን ፋንድያ
ከዘሩ በኋላ አረሙ ሲመጣ
በማስተዋል ፀጋ ነቅለን ብናወጣ
ፍሬው ተንዥርጐ ፀንቶ ቆሞ ሥሩ
ይበዛ ነበረ ሊታጨድ መከሩ፤

አገልጋይ ይተክላል
ደግሞ ይኮተኩታል
አድጎ እስኪያፈራ ችሎ ይጠብቃል።

ዘርን ዘርቶ ትቶ እግዜር ይየው ማለት
መሆኑን እወቀው የሰነፍ ሰው ብልሃት፤
አንተ እንድትዘራ ደግሞ እንድትኮተኩት
የመከሩ ጌታ ከመረጠህ በውድ
ባላ'ደራ እንድትሆን ከመረጠህ ጌታ
በጊዜያቱ ሁሉ በቅንነት ትጋ
አትታክት አትድከም መከሩን ጠብቀው
አድጎ ያፈራ 'ለት ሠላሳና ስልሳ መቶ ዘለላ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment