Saturday 25 January 2014

ነፃ አወጣን


በራሣችን ፈርደን የሞት ኑሮ ስንኖር፤
በመንፈሰ ደይን ባርያዎች ተብለን፤
በኃጢአት ጭቅቅት ጠረናችን ጠፍቶ፤
የነፍስ ገላዋ በዕድፈት ተበላሽቶ፤
ያልፈጠረን ጌታ በዕዳ ጽህፈት፤
ሲገዛን ሲነዳን በስድብና ንቀት፤
ኢየሱስ አዳኙ በዮርዳኖስ ቆሞ፤
የሚቃወመንን የመውጊያውን ብረት ' ላይ አንስቶ፤
የሞቱን ደብዳቤ በእግሮቹ ረግጦ፤
ነፃ አወጣን ነፃ ልጅ ሆነና እርሱ፤
ልጆች እንድንባል ከአብራከ መንፈሱ፡፡

No comments:

Post a Comment