Friday 18 March 2022

ምኩራቡ!

Please read in PDF 

ቅዱሳት መጻሕፍት የሚነበቡበት

የሚፈከሩበት የሚሰበኩበት

ምኩራቡ ነበረ ውብ ዓውደ ምሕረት

ኅብስተ ወንጌሉ የሚፈተትበት …

ቀኑ ድንገት ሲባጅ ድንግዝግዝ ሲበዛ

የሌባ ዓይነ ደረቅ በምኩራቡ ገባ!

እናም!

ቃሉ ተከደነ፤ ወንጌሉም ታጠፈ

“ባርከነዋል ያልነው” ዘይትና ውኃ

                 ምኩራቡን ወረሰ!

አቤቱ ጌታችን፤ ስምህ እንዲፈራ

              ቃልህ እንዲከበር

የእኛ ውኃ ተደፍቶ ያ’ንተ ቃል ይነገር!

                          አሜን!

No comments:

Post a Comment